Monthly Archives: June 2014

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን ባለሥልጣናት እገታ ላይ መሆኑን በማስመልከት የወጣ መግለጫ

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን ባለሥልጣናት እገታ ላይ መሆኑን በማስመልከት የወጣ መግለጫ ሰኔ 23 ቀን 2006 ዓ.ም የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓም ለሥራ ጉዳይ በየመኒያ አየር መንገድ አይሮፕላን ተጉዞ በትራንዚት … Continue reading

Posted in Uncategorized | Leave a comment

እውነት ኦሮሚያ የሚለው ስም በታሪክም በተረትም የማይታወቅ የህልም ዓለም ስያሜ ነው?

(ኢልማ ኦሮሚያ) በትምህርትም ሆነ በሀብት ቀና የሚሉ የኦሮሞ ሕዝብ ልጆችን በተለያዩ የፀረ- መንግሥት እንቅስቃሴዎች በመፈረጅ ሲያሳስሩና ሲያስገድሉ የኖሩ የኦሮሞ ፍራቻ-ጥላቻ በሽታ ህመምተኞች በሚያከሂዱት ፀረ- ኦሮሞ ፐሮፓጋንዳ “ኦሮሚያ የህልም ዓለም ስያሜ ነው፤እስላሞችና ኦሮሞዎች የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ይጠይቁ፤ ስለኦሮሞ ሕዝብ ጨካኝነት የአገር … Continue reading

Posted in Uncategorized | Leave a comment

ኢትዮጵያዊው-ኖርዌጂያን ኦኬሎ ኦካይ ኦቻላ ”ሞት ሊበየንበት ይችላል” -በሽብርተኝነት ክስ ሞት ተፈርዶባቸው ሞታቸውን የሚጠባበቁ 127 ሰዎች ኣሉ

በኖርዌይ ሃገር ውስጥ በኖርዌጂያንኛ የሚታተመው ዳግብላደት የተባለው ጋዜጣና ድረ-ገጽ ”ኢትዮጵያዊው-ኖርዌጂያን” ኦኬሎ ኦካይ ኦቻላ በሚቀጥለው ሳምንት ሞት ሊበየንበት ይችላል” ሲል ኣውጥቶኣል። ”ባለፈው ሳምንት ለማወቅ እንደተቻለው ዕድሜው 52  የሆነና  ኦኬሎ ኦካይ ኦቻ  የተባለ ኖርዌጂያን ኢትዮጵያ ውስጥ በሽብርተኝነት ተከሶ በእስር ላይ ይገኛል።” tiltalt for terror በማለት የጀመረው … Continue reading

Posted in Uncategorized | Leave a comment

መዝገቦቹ መልሰው ተቀራረቡ የእምነት ክህደት ቃል በኃይል አስፈርመዋቸዋል

መዝገቦቹ መልሰው ተቀራረቡ የእምነት ክህደት ቃል በኃይል አስፈርመዋቸዋል ጽዮን ግርማ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በስድስቱ ጦማሪያንና በሦስቱን ጋዜጠኞች ላይ የፌደራል ፖሊስ የተለያየ ምክንያት እየሰጠ ቀጠሮ የሚያራዝመውን ሁለት መዝገብ አንዴ ሲያቀራርበው መልሶ ደግሞ ሲያራርቀው ቆይቶ አሁን ደግሞ … Continue reading

Posted in Uncategorized | Leave a comment

ውርርድ በእግር ኳስ ጨዋታ

የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዶቻችን በአሁን ሰዓት በመካሄድ ላይ ያለውን የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር የበለጠ አጓጊ ለማድረግ የወሰኑ ይመስላል። የእግር ኳስ ጨዋታ ውድድር ከመጀመሩ በፊት በቡድን ሊመለከቱ በታደሙ ሰዎች ዘንድ ዛሬ የትኛው ቡድን ያሸንፋል? ስንት ለስንት ይለያያሉ? የሚሉት ጥያቄዎች የተለመዱ … Continue reading

Posted in Uncategorized | Leave a comment

ጥንታዊዉ የጀርመን ገዳም በዓለም ቅርስነት

ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት በ«UNESCO» ዘጠኝ መካነ ቅርሶችን እና አንድ የማይዳሰስ ቅርስን፤ በአጠቃላይ አስር ታሪካዊ ቅርሶችን አስመዝግባለች። ጀርመን ደግሞ ከስፔን እና ከጣልያን ለጥቃ 39 ቅርሶችን በዓለም ቅርስነት በማስመዝገብ ሶስተኛዋ የዓለም ሀገር ናት። ትናንት የተጠናቀቀዉ የተባበሩት መንግስታት … Continue reading

Posted in Uncategorized | Leave a comment

የኢራቁ ጦርነትና የጀርመን ኩባንያዎች

የኢራቁ ውጊያ ዜጎችን ብቻ ሳይሆን በሃገሪቱ የተሰማሩ የውጭ ኩባንያዎችንም ከሃገር እያስወጣ ነው ። በጦርነቱ ሃገር ለቀው እንዲወጡ ከተገደዱት ውስጥ የጀርመን ኩባንያዎች ይገኙበታል ። ከሁለት ሳምንት ወዲህ ውጊያ ተጠናክሮ ከመቀጠሉ በፊት ኢራቅ የውጭ ባለሃብቶች ተስፋ የጣሉባት ለውጭኩባንያዎች በርዋን በሰፊው ከፍታ የምትጠብቅ ሃገር ነበረች ። ተረጋጋች ተብሎ የአሜሪካን ወታደሮች ሃላፊነቱን ለኢራቅጦር ኃይል አስረክበው ምርጫም ተካሂዶ መንግሥት ቢመሰረትም የሰላሙ ተስፋ ተስፋ ሆኖ የቀረ ነው የሚመስለው ።እንደገና ያገረሸው ጦርነት የዜጎችን ህይወት ከቀድሞው በባሰ ሁኔታ ማመሰቃቀሉ ቀጥሏል ። እስከዛሬ በዚህች ምድርያለቀው ህዝብ ሳያንስ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብዙዎች ተገደልዋል ተሰደዋል። የኢራቅ ሰላም መደፍረስ ሃገሪቱን ከሌላአቅጣጫም እየጎዳ ነው ። ባለፉት ዓመታት የውጭ ባለሃብቶች በኢራቅ የነበራቸውን ተስፋ በሃገሪቱም መታየትየጀመረውን ለውጥ ከነአካቴው ደብዛው እንዲጠፋ እያደረገ በመሄድ ላይ ነው ። ሰላም ከሌለ ሰርቶ መግባት ያለ ሰላምልማት አይታሰብምና በሃገሪቱ ሰላም መልሶ እንዲሰፍን ዜጎች ብቻ ሳይሆን በሃገሪቱ በተለያዩ ስራዎች የተሰማሩ የውጭባለሃብቶችም ምኞት ነው ። «በአሁኑ ጊዜ በኢራቅ የሚሆነው እጅግ አሳዛኝ ነው ። በበኩሌ በአንድ ወቅት ላይ የሰከነሁኔታና ሰላም ይሰፍናል ብዮ ተስፋ ማድረግ ብቻ ነው የምችለው ። እናም ያኔ ሃገሪቱ በእርግጠኝነት መልካም እጣፈንታ ይገጥማታል ።» ኢራቅ ውስጥ በግንባታ ስራ የተሰማሩት የምዕራብ ጀርመን የኢንዱስትሪ ማዕከል የሆነችው የቬስል ከተማ ባለሃብትኤርስት ዮአሂም ትራፕ ናቸው ። ስለ ኢራቅ የሚናገሩት ከልብ ተነክተው ነው ። የኤፍራጥስና የጤግሮስ ምድር በሆነውበኢራቅ እጎአ ከ1950 ዎቹ አንስቶ ከልጆቻቸው ጋር የሚያስተዳድሩት የቤተሰብ ኩባንያ አላቸው ። ትራፕ መጀመሪያ ኢራቅ የሄዱትእጎአ በ1952 ነው ። ያኔ የ17 ዓመት ጎረምሳ ነበሩ ።በወቅቱም ኢራቅ የሄዱት የአባታቸው አስተርጓሚ ሆነውነበር ።ከዚያን ጊዜ አንስቶ በጊዜ ሂደት እየጠበቀ ያደገውግንኙነት በኢራቅ ለመሰረቱት ኩባንያ ንግድ እጅግጠቃሚ ነበር ። « በቀጣይነት እጅግ ጠቃሚው ጉዳይ በሃገር ውስጥየሚያውቅህ ጥሩ አጋር ማግኘቱ ነው ። በሃገር ውስጥያለው ሥልጣን በሼኮቹ እጅ ነው ። ይህ ደግሞ ለምዕተ ዓመታት እና አሁንም በዚያ መንገድ ነው የሚካሄደው ። ስለዚህአንድ ሰው ከሼኮቹ ጋር ጥሩና የሰከነ ግንኙነት ካለው ንግዱ ም አስተማማኝ ይሆናል ። » በዚህ አግባብ ነበረ የትራፕ የግንባታ ኩባንያ በምዕራብ ኢራቅዋ የአንባር ክፍለ ግዛት አንድ ፕሮጀክት የጀመረው ።ኩብንያው ፕሮጀክቱን የጀመረው የተነገረውን ምክር በመስማት ነበር ። የ77 ዓመቱ ትራፕ እንደሚሉት አሁንያጋጠማቸው ግን ፍፁም ያልተጠበቀ ጉዳይ ነው ። «ከሁለት ዓመት በፊት እዚያ ስንጀምር ሶሪያ ድንበር አቅራቢያ የሚገኘው ይህ አካባቢ ደህንነቱ የተረጋገጠ ነው ተብለንነበር ። ይሁንና አሁን መንግስትን የሚወጉት ISIS በመባል የሚጠሩት የሱኒ አማጽያን ተቆጣጥረውታል ።» ኩባንያቸው የሚያካሂዳቸው ግንባታዎች በተለየ አሠራር በኢራቃውያን ሠራተኞች ቀጥሏል ። ጀርመናውያን መሃንዲሶችግን በፀጥታ ችግር ምክንያት ከአካባቢው ወጥተዋል ። ዚመንስና ሌሎችም ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ሠራተኞቻቸውንደህንነታቸው አስተማማኝ ወደ ሆኑ ስፍራዎች አሽሽተዋል ፤ አለያም ኢራቅን ለቀው እንዲወጡ አድርገዋል ። አንባርበአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ ግጭት ከሚካሄድባቸው ሶስት ክፍለ ግዛቶች አንዷ ናት ። የተቀሩት ሁለቱ ኔኔቭ ና ሳላዲን ናቸው።ሽቴፈን ቤህም በጀርመን የኢንዱስትሪና የንግድ ምክር ቤት የመካከለኛው ምስራቅ ና የሰሜን አፍሪቃ ጉዳዮች አዋቂይህንኑ አረጋግጠዋል ። ምክር ቤታቸውም በነዚህ አካባቢዎች የሚሰሩ የጀርመን ኩባንያዎች የጥንቃቄ እርምጃዎችንእንዲወስዱና ሠራተኞቻቸውንም እንዲያስወጡ እየመከረ ነው ። «ህንዳውያንና ቱርካውያን ሠራተኞች መታገታቸውን የሚገልጹ ዘገባዎች አሉ ። ይህም አካባቢው በአሁኑ ጊዜአስተማማኝ እንዳልሆነና በማናቸውም ጊዜ አደገኛ ሁኔታዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ በጣም ግልፅ ምልክት ነው ።» የጀርመን የኢንዱስትሪና የንግድ ምክር ቤት ኢራቅ ውስጥሁለት ቢሮዎች አሉት ። አንዱ የራስ ገዝዋ የኩርዶች ግዛትዋና ከተማ በሆነችው በኤርቢል ሌላው ደግሞ በዋናከተማይቱ በባግዳድ ነው የሚገኘው ። ኤርቢል በርካታየጀርመን ኩባንያዎች የሚገኙባት ከተማ ናት ። የምክር ቤቱኢራቃውያን ጠበብት የጀርመን ኩባንያዎች አስተማማኝየንግድ አጋር ሲፈልጉ እገዛ ያደርጉላቸዋል ።የጀርመን የውጭጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤትንም በፀጥታ ጉዳዮች ላይበቅርበት ያማክራሉ ።የጀርመን የኢንዱስትሪና የንግድ ምክርቤት እንደሚለው በአሁኑ ወቅት በማዕከላዊ ኢራቅ ወይም በባግዳድ አለያም በባዝራ ቁጥራቸው 30 የሚሆን የጀርመንኩባንያዎች አሉ ። በሰሜኑ የኩርድ ግዛት ደግሞ 40 የጀርመን ኩባንያዎች ይገኙበታል ።ሽቴፋን ቤም እንደሚሉትኩባንያዎቹ በተለይ በዋነኛት በመሰረት ልማት አገልግሎት ማለትም በግንባታ ሥራዎች በጤና አገልግሎት በኤሌክትሪክማመንጨትና ማሰራጨት ዘርፍ ነው የሚሰሩት ።የጀርመን ኩባንያዎች ኢራቅ ውስጥ በብዛት መሰማራት የጀመሩትምከዛሬ ስድስት ዓመት ወዲህ ነው ። በቅርቡ ደግሞ ቁጥራቸው እየቀነሰ ነበር ። « እና ያየነው ምንድነው የጀርመን ባለሃብቶች ኢራቅ ውስጥ የመስራት ፍላጎታቸው እያደገ የመጣው እጎአ ከ2008አንስቶ ነው ። ኢራቅ ላይ ይበልጥ ማትኮራቸው ቀጥሎ በጣም ጥሩ ውጤትም አስገኝቶ ነበር ። ሆኖም ባለፉት ሁለትዓመታት የፀጥታው መደፍረስ እየተባባሰ በመሄዱ ፍላጎቱ ቀንሶ ነበር ።» ሌሎች የአረብ አገራት ጋር ሲነፃፀር በጎርጎሮሳውያኑ 2013 ኢራቅ ጀርመን በብዛት የውጭ ንግድ ገበያ የምታካሂድባትስድስተኛዋ ሃገር ነበረች ። በዚሁ ዓመት ጀርመን ወደ ኢራቅ የላከችው የውጭ ንግድ 1.3 ቢሊዮን ዩሮ ወይም 1.77ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ።ይህ ጀርመን በዚሁ ዓመት ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ገበያ ካቀረበችው የ10 ቢሊዮን ዩሮንግድ ወይም ወደ ሳውዲ አረቢያ ከላከችው የ9 ቢሊዮን ዩሮ ገበያ ጋራ ሲነፃፀር ግን ያን ያህል ብዙ የሚባል አይደለም ።ሆኖም ቤም እንደሚሉት በረዥም ጊዜ ሲታይ ኢራቅ የጀርመንን ትኩረት የሚስብ ገበያ የሚገኝባት ሃገር ናት ። ይህም በርሳቸው አስተያየትሃገሪቱ የጀርመን ባለሃብቶችን ትኩረት የሳበችውበነዳጅዘይት ሃብት ከዓለም በሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሃገርበመሆንዋ ብቻ አይደለም ። « ኢራቅ 80 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ምንዛሪክምችት አላት ። ይህ ገንዘብ የተያዘው በመሠረተ ልማትመስክ ለሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ነው ። ለጊዜው ግንይህን ገንዘብ ሥራ ላይ ማዋል ። ምክንያቱም የኢራቅምክር ቤት በሃገሪቱ የጎርጎሮሳውያኑ 2014 ዓመተ ምህረት በጀት ላይ መግባባት አልቻለምና ። » በዚህ የተነሳም ባለፉት ጥቂት ወራት የተገነቡት ካለፉት ዓመታት የተገፉ ና ያላለቁ ፕሮጀክቶች ናቸው ። በሃገሪቱብሄራዊ በጀት ላይ መስማማት ከተቻለ ግን በርካታ ፕሮጀክቶች ሥራ ላይ መዋል ይጀምራሉ ። በዚህ ጊዜም የጀርመንኩባንያዎች እጅግ አትራፊ የሆኑ ውሎች ያገኛሉ ። ይህን እድል የሚያገኙት ግን በአሁኑ ወቅት ራሳቸውን አመቻችተውያስቀመጡት ብቻ ናቸው ። « አሁን በሃገሪቱ ውስጥ የሚገኙት ማለትም ስራው በቆመበትም ጊዜ እዚያው የቆዩት ሁኔታው በተወሰነ ደረጃ ሲረጋጋወዲያውኑ መመለስ ይችላሉ ። አዳዲሶቹ ግን በፀጥታው ችግር መባባስ ምክንያት ወደ ኋላ ማለታቸው ይቀጥላል ብዬነው የምጠብቀው ።» ወደ 62 ዓመት ኢራቅን የሚያውቋት እርነስት ዮአሂም ትራፕ ቤም ያሉትን ነው የሚደግሙት ።ወደፊትም በኢራቅ ይሄሊሆን ይችላል ብለው መተንበይ አይፈልጉም ። … Continue reading

Posted in Uncategorized | Leave a comment