“ቴዲ አፍሮ ከሀገር ተሰደደ የሚል መራር ዜና ልንሰማ የምንችልበት ጊዜ እየቀረበ እንደሆነ ይሰማኛል” – (ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን)

የኢሳቱ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ቀጣዩን ስጋቱን በፌስቡክ ገጹ እንዲህ ነበር የገለጸው:: ተካፈሉት:: ህወሀት ቴዲ አፍሮን ከልክ በላይ እየገፋው ነው:: ለቴዲ የህወሀት ኢትዮጵያ አላስቀምጥ ብላዋለች:: ምናልባትም ቴዲ ከሀገር ተሰደደ የሚል መራር ዜና ልንሰማ የምንችልበት ጊዜ እየቀረበ እንደሆነ ይሰማኛል:: በግሌ በተለይ ሰሞኑን የሚደርሱኝ መረጃዎች የህወሀትን የዕብሪት ለከት ማጣት የሚያሳዩ ቴዲንም ከሚወደው ህዝብና ከሚሳሳላት ሀገሩ እንዲለያይ የሚገፋፉ ናቸው:: ቴዲ መሰደድ እንደማይፈልግ የትኛውንም በደል ተቋቁሞ በሀገሩ መኖር ለምርጫም የማይቀርብ ጉዳይ እንደሆነ ባውቅም ትዕግስትም ልክና ድንበር አለውና የሰሞኑ ግፊትና ግፍትሪያ ከመራር ውሳኔ ሊያደርሰው እንደሚችል አምኜአለሁ:: ቴዲ ከእናቱ ቤት መሀል አዲስ አበባ እሱ ወደ ሚኖርበት ሲ ኤም ሲ በየጊዜው ሲመላለስ በደህንነቶች ታጅቦ: በመንገድ ላይ እያስቆሙ መከራውን አሳይተው በሚፈትሹት የህወሀት ሰዎች ተንገላቶ መሆኑ አስገራሚ ነው:: ቤቱ በደህንነቶች እጅ ላይ ወድቋል:: ዙሪያውን ይቆጣጠሩታል:: እንዳሻቸው እየጠሩ ያስፈራሩታል:: ከተቃዋሚዎች ጋር ትገናኛለህ በሚል ክብረ ነክ ምርመራ ያደርጉበታል:: በቅርቡ ባለቤቱ ታማ ወደ ኬኒያ ይዟት ሊሄድ ሲል መንቀሳቀስ የጀመረን አውሮፕላን እንዲመለስ አድርገው እንደ ወንጀለኛ በተሳፋሪ ፊት እየገፈተሩ ወስደውታል:: በተደጋጋሚ የውጭ ጉዞዎቹ እንዲሰረዙ አድርገዋል:: በርካታ ሌሎች ጥቃቶችን ፈጽመውበታል:: ለፊታችን አዲስ ዓመት በላፍቶ ያዘጋጀው ኮንሰርትም ሊሰረዝ እንደሆነ ከውስጥ ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል:: በአዲስ አበባ ለህወሀት የሚጮሁ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች የላፍቶው ኮንሰርት የሚሰረዘው በስፖንሰር እጦት ነው በሚል ቢያራግቡም እውነታው ግን የምንመርጥልህን እንጂ የመረጥካቸውን ዘፈኖች አታቀርብም ብለው ጣልቃ በገቡ የደህንነት ሰዎች ግፊት ነው:: ቴዲን ህወሀት ከሀገር ገፍትሮ ሊያስወጣው እየሞከረ ነው:: መንፈሰ ጠንካራ የሆነው ቴዲ እስከአሁን በትዕግስት እየመከተ ነው:: ሰው ነውና መንግስትን የሚያክል ሃይል ተነስቶበት ብቻውን ይመክታል ማለት አይቻልም:: ከጎኑ መቆም ግድ ይላል:: ህወሀት ቴዲ ላይ አይደለም ሰይፍ የመዘዘው:: ትውልዱ ላይ ነው:: ኢትዮጵያዊነት ላይ ነው::

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s