የ “ሀ” ን ዘር የ “ከ” ዘር እያጠፋው ነው:: – ይገርማል ታሪኩ

Amharic2በወያኔ የተቀነባበረ ሴራ አልፎ ተርፎም ቀጥተኛ ግድያ አማሮች እያለቁ ቁጥራቸውም እየተመናመነ በመሄድ ላይ መሆኑን ሁሉም ያውቃል:: የአማራ ዘር ብቻ ሳይሆን የአማራ ባህል: ቅርስና ትውፊት ናቸው ተብለው በሚታመኑት የረጅም ጊዜ የታሪክና የእምነት አሻራወቻችን ላይም የማጽዳት እርምጃ በተለያየ መንገድ እየተወሰደ ነው:: ዛሬ አማራንና ኦርቶዶክስ ሀይማኖትን ለያይተው ማየት የተሳናቸው ግብዞች ኦርቶዶክስ ሀይማኖት አማራው የፈጠረውና የአማራ መሸሸጊያ እንደሆነ አድርገው በመስበክ: ቤተክርስቲያናቱን በማቃጠል: መጽሀፍቱንና የአምልኮ መገልገያ መሳሪያወችን ባህር እያሻገሩ በመሸጥ: ቤተክርስቲያን በነጻነት መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳትሰጥ ካድሬወችን በመሰግሰግ የወያኔ ጉዳይ ፈጻሚ በማድረግ: ጊዜ የማይሽረው በደል እየፈጸሙ ነው::

እንደሚታወቀው የአማራ ክልል የሚተዳደረው በዋናነት አማራ ሳይሆኑ አማራ ናቸው ተብለው በተቀመጡ የሌላ ብሄርና የሌላ ሀገር ሰወች ነው:: ከታች የተኮለኮለው አማራ ነኝ ባይ የአህያ ባል ሆኖ የመጣውን እየተቀበለ አድርግ የተባለውን እያደረገ የሚኖር ስለክልሉም ሆነ ስለ ህዝቡ የማይጨነቅ ለከርሱ ብቻ የቆመ ተራ ስብስብ ነው::

ቀደምት አማሮች በአራቱም ማእዘን በመዝመት አጥንታቸውን ከስክሰውና ደማቸውን አፍስሰው በየትኛውም የጥቁር ህዝቦች ታሪክ ያልታየ ገድል በመፈጸም በምስራቅ ከጣሊያኖችና ከፈረንሳዮች በደቡብና በምዕራብ ከእንግሊዞች ጋር ድንበር ተካለው ኢትዮጵያን ለእኛ አስረክበዋል:: ያ ባይሆን ኖሮ ዛሬ ላይ በምስራቅ ያለው ኢትዮጵያዊ ከፊሉ ከጅቡቲ ቀሪው ደግሞ ከሶማሊያ ጋር: በደቡብ ያለው ኢትዮጵያዊ ከኬንያ ጋር: የሰሜኑ ከኤርትራ የምእራቡ ደግሞ ከሱዳን ጋር የመሆንና ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር በታሪክ ብቻ የምትታወስ ሆና በቀረች ነበር::

የአፍሪካም ሆነ የኤዥያ ሀገሮች እንደሀገር የቆሙት በቅኝ ግዛት ጊዜ በነበራቸው አብሮነት መሰረት በመሆኑ በተለያዩ አገሮች በቅኝ ግዛትነት ተይዘው የቆዩት አንድ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝቦች ተበታትነው በተለያዩ ሀገሮች የመኖር እጣ ደርሶባቸዋል:: እኛ ግን አያት ቅድመአያቶቻችን ባደረጉት የመረረ ተጋድሎ ረጅም ታሪክ ያላት ጥንታዊቷ ሀገራችን ኢትዮጵያ የጥቁር ዘር የነጻነት ፋና የልጆቿ መመኪያ በመሆን ከዘመን ዘመን ተሻግራ ለእኛ ተላለፈች:: ዛሬ ባለጊዜ ወያኔወች እንደፈለጋቸው የሚያደርጓት: ብዙሀኑም ፍዳ የሚያይባት: “ኢትዮጵያ” የምትባል ሁላችንንም ሰብስባ የያዘችዋ ሀገር ነጻነቷን አስጠብቃ ለእኛ እንድትደርስ የተከፈለው ደምና አጥንት ከ-እስከ የሚባል አይደለም::

ታዲያ እነዚያ ጠላት አይደፍረንም ብለው በቀዳሚነት ደምና አጥንት የከፈሉት ኢትዮጵያውያን ልጆች ዛሬ ላይ ራሳቸውን እንኳ ማስከበር አቅቷቸው በመጥፎ መንፈስ በተሞሉ የወያኔ ተኩላወች ፊታውራሪነት ለፈርጀ ብዙ ጥቃት ተጋልጠው ያለ አለሁ ባይ በየአካባቢው እየወደቁ ነው:: ከሁሉ ከሁሉ የሚገርመው ደግሞ ተጣመው የተፈጠሩና ነፍስ ያላወቁ ከራሱ ከአማራው አብራክ የተገኙ ጥቂት ጉዶች ለወያኔ አድረው የጠላት መሳሪያ በመሆን እንወክለዋለን የሚሉትን ሕዝብ ከአዋራጆቹ ጋር ተስማምተው እያዋረዱት: ከአሳዳጆቹ ጋር እያሳደዱት: ከገዳዮቹ ጋር ተባብረው እየገደሉት በወገናቸው ላይ የሚደርሰው ግፍና ሰቆቃ ሳይጎረብጣቸው በድርጊታቸው ተኩራርተውና ረክተው መቀጠላቸው ነው:: በአማራው ላይ የሚደርሰውን ሁለንተናዊ ግፍ የሚቃወሙትን ፈጥነው በማጥፋት “ጎሽ” ለመባል የሚተጉት እኒህ ትንሽየ እንኳ እንጥፍጣፊ ህሊና የሌላቸው እፍኝ የማይሞሉ የእንግዴ ልጆች ያማራውን ክልል ለማስከበርና የህዝቡን ደህንነት ለማስጠበቅ መስራት ሲገባቸው መሬቱን በውጪ ለሱዳን: በውስጥ ደግሞ ለተለያዩ ክልሎች እያስቦጠቦጡ ከጊዜ ወደጊዜ መኖሪያውን እያጠበቡ ተስፋውን እያጨለሙበት ነው:: በየዳር ድንበሩ በውትድርና ዘምቶ በዚያው ሀገሬ ብሎ ከአካባቢው ህዝብ ጋር ተጋብቶና ተዋልዶ ለረጅም ጊዜ በኖረው ህዝብ ላይ የወያኔ የጥላቻ በትር ሲያርፍበት ለምን ብሎ እንደመከራከርና መብቱን እንደማስከበር “ከክልሉ የወጣ አማራ ጉዳይ አይመለከተንም” በማለት ወገኖቻችን በየሄዱበት ወድቀው እንዲቀሩ ድጋፋቸውን አበረከቱ:: እኒህ ከወያኔ ጉያ ተወሽቀው በሚያገኙት ዳረጎትና በወገናቸው ላይ በሚደርሰው ዘግናኝ ግፍ ተደስተው ሰላም አግኝተው የሚኖሩ የብአዴን ሰዎች የሚቆጭ ህሊና የሌላቸው ለሆዳቸው ብቻ የተፈጠሩ ትናንሽ ሰወች ለመሆናቸው ተግባራቸው ይመሰክራል::

በመሆኑም አማራው በክልሉም ሆነ ከክልሉ ውጭ እንደዜጋ መብቱ ተከብሮ ለመኖር ያልቻለ: በስውርና በግልጽ ደባ ቁጥሩ የተመናመነ: በቤተሰብ እቅድ ስም በርሱ ላይ ብቻ ያተኮረ የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈጸመበት ሆኗል:: የዚያ ታሪክ ሰሪ ህዝብ ልጆች ራሳቸውን መከላከል ከማይችሉበት ደረጃ ላይ ወድቀው ያም ያም እንደፈለገው የሚያደርጋቸው እርካሾች ሆነው ሲታዩ እንዴት ያማል::

ወደርዕሴ ስመለስ.:- በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የአሁኑ ትውልድ የሀን ዘር በከ ዘር በመተካት የሀን ፊደል ከፊደል ገበታ ለመሰረዝ በጉዞ ላይ ነው:: ፊደሎችን ካለወህል መጠቀም እንዴት ያስቀይማል! በተለይ ይህን የሚያደርጉት የስነጥበብ ሰዎች ሲሆኑ ደግሞ ከማስቀየም አልፎ ህመሙ ይጠዘጥዛል:: ጥሩ የታሪክ አወቃቀርና ፍሰት ያለው ድራማ/ፊልም ላይ ፊደላት ያለቦታቸው ሲገቡ ለሰሚ ይቀፋሉ: ታሪኩንም ያደበዝዛሉ:: አንድ ወይም አንዲት የአርት ሰው መሰረታዊውን የቃላት አወቃቀር በመቀየር እንዴት ነክ: እኔ እምልክ: የት ነክ: ወዘተ እያለ/እያለች ሲናገር/ስትናገር ለሰማ ጆሮን “ኩ-ር” ያሉት ያህል ይሰቀጥጣል::
የዱሮ                                                   የአሁን
ምን አደረግሁ                                              ምን አደረኩ
ማን ነህ                                                     ማን ነክ
የት ነህ                                                      የት ነክ
እኔ የምልህ                                                 እኔ የምልክ
ታምራለህ                                                   ታምራለክ
ተውበሀል                                                   ተውበካል
አምሮብሃል                                                 አምሮብካል
…….                                                       ———
በአንድ ወቅት ት/ቤት እያለሁ አንድ መምህር የተናገሩት ምን ጊዜም አይረሳኝም:: አንድ ተማሪ should የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል “ሹልድ” እያለ ሲያነብ ሰምተው በጣም ተቆጡና “ስማ! አንተ ሹድ ተብለህ ተምረህ ሹልድ እያልህ መጣህ የአንተ ልጆች ደግሞ ሹልዳ እያሉ ይመጣሉ”
ተከታዩ ትውልድስ የቱን የአማረኛ ፊደል ይገድፍ ይሆን!

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s