ጥቁሩ ብላቴና (ሄኖክ የሺጥላ)

Henok

ጥቁሩ ብላቴና
ያገሬ ጠበቃ
ተይዣለሁ እኔ
ባንተ ጥበብ ሲቃ ።

በፍቅር ባንድነት ፣ በእኩልነት ቋንቋ
ሼ መንደፍር ቴዲ
የቴዲ ሙዚቃ !

ክራር ሲከረከር
አምባሰል ትዝታ ፣ ባንተ ሲቆረቆር
እሪኩም ድናግዴ ፣ ፈሶ ሲንቆረቆር
አንቺ ሆዬ ከትሞ
ባድዋ አታሞ
ሚኒልክ ሲነሳ
መቃብር ፈንቅሎ
አረ ባቲ ባቲ
አረ ወሎ ወሎ ።

ቴዲ እንደ ዳዊት
ዘይት በቀንድ ዋንጫ
ቀብቶታል አምላክ ፣ ለብርሃን መውጫ !

ከተራራው ጫፍ ላይ ፣ አይዝልም ጉልበቱ
ይወጣል ፣ ይቆማል ፣ ይቀብራል እትብቱን !

እዮሃ መስከረም ፣ አዲስ ዓመት መጣ
አበባዮሽ አለ ፣ ቴዲ ቃል አወጣ !
እንደ ምስራቅ ብርሃን ፣
እንደ ሰብዓ ሰገል
ወገግ አለች ምድር ፣ ጥበብ ሲገላገል !

ላምባዲና ቴዲ
አንተ ያገር ኩራዝ
የተስፋ መለከት
የይቅርታ መቅረዝ !

የውነት አቦጊዳ
በሰባ ደረጃ
እንደ-ቦይ ለፍቅር
ነህ አንተ መውረጃ
አስራ ሰባት መርፌ -ያስተስርያል ጃ !

እዮሃ ቴዎድሮስ ፣ እዮሃ ለፍቅርህ
አደይ ላንተ ይሁን ፣ አደይ ለጥበብህ ።

ለቴዲ አፍሮ ( ቅጽበታዊ ግጥም ) መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልህ አንተ ቀና ሰው

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s