አዲስ ዜና ሀብታሙ አያሌው ነገ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው

የመጨረሻው ደውል's photo.

የቀድሞው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወጣት ሀብታሙ አያሌውና ሌሎች የፖለቲካ አመራሮች የልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት ከተመሰረተባቸው ክስ በነፃ ካሰናበታቸው በኋላ ነገ በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተለይ ሀብታሙ አያሌው እንደሚቀርብ ባለቤቱ ወ/ሮ ቤተልሔም ገለፀች፡፡
ቤተልሔም እንደተናገረችው ባለቤቷ በነፃ እንዲሰናበት ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከወሰነ በኋላ ባልታወቀ ሁኔታ እስርቤቱ አለቅም ማለቱንና ላልተለቀቀበት አግባብ ምንም አይነት ግልፅ ማስረጃ እንዳልተሰጣቸው አብራርታለች፡፡
ይህንን ህገወጥነት በመቃወምም ለባለፉት 15 ቀናት ልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በእስርቤቱ ላይ ክስ መስርታ ስትከታተል እንደነበረና ባለቤቷ በነፃ ከተሰናበተ በኋላ የፍድ ቤት ትዕዛዝ ሳይከበር ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ እስካሁን ታስሮ እንደሚገኝ በመግለፅ ፍርድቤቱ ብያኔ እንዲሰጣት መጠየቋን ተናግራለች፡፡
በዚህም መሰረት የልደታው ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ እስር ቤቱ ለምን ሀብታሙን እንዳለቀቀ ማብራሪያ እንዲሰጥ በመወሰን ነገ ከጠኋቱ 2፡30 ልደታ ከፍተኛው ፍ/ቤት ሀብታሙ አያሌው እንደሚቀርብ ገልፃለች፡፡ በማያያዝም ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና ሌሎች የሲቪክ ተቋማት እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታው ሁሉ በመገኘት ችሎቱን እንዲከታተሉ መልዕክቷን አስተላልፋለች – የሀብታሙ አያሌው ባለቤት ወ/ሮ ቤተልሔም፡፡

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s