የእንግሊዝ ቪዛ የተከለከሉት ፕሮፌስር መስፍን ወ/ማርያም አሜሪካ ገቡ

ወደ እንግሊዝ ሃገር የሚያስኬዳቸውን ቪዛ ተከልክለው ወደዚያው ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ የተስተጓጎለባቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ፕሮፌሰር መስፍን ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ መግባታቸውን በስፍራው የሚገኙ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታወቁ:: በቅርቡ ‘አዳፍኔ’ የተሰኘ ‘አወዛጋቢ’ መጽሐፍ ለንባብ ያበቁት እኚሁ ፕሮፌሰር ዛሬ ዋሽንግተን ዱሉስ ኤርፖርት ሲደርሱ ወዳጆቻቸው ሞቅ ያለ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታውቀዋል:: ፕሮፌሰር መስፍን በአሜሪካ ቆይታቸው አዲሱ መጽሓፋቸውን በዋሽንግተን ዲሲ በሸራተን ፔንታጎን ሲቲ እሁድ ሴፕቴምበር 13, 2015 ዓ.ም ከ2 ሰዓት ጀምሮ ያስመርቃሉ:: በዚህም ወቅት የሕዝብ ጋር ወቅታዊ ውይይት እንደሚያደርጉ አዘጋጆቹ ለዘ-ሐበሻ ከላኩት ፍላየር (በራሪ ወረቀት) መረዳት ተችሏል:: ፕሮፌሰር መስፍን እንግሊዝ ሃገር በተለያዩ ጊዜያት ቢመላለሱም ዘንድሮ ቪዛ መከልከላቸው ብዙዎችን አነጋግሩዋል። የእንግሊዝ መንግስት ቪዛ የከለከለበት ምክንያት በዚያው ሊቀሩ ይችላሉ በሚል ነው።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s