ሰበር ዜና – የምዕራብ አፍሪካዊቱ ሀገር የቡኪና ፋሶ መንግስት ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ተደረገበት።

በአዲሱ መፈንቅል አድረጊ ወታደሮች የታገቱት ጊዚያዊ ፕሬዝዳንት ካፋንዶ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሌ/ኮ/ ኢሳቅ ዚዳ

የቡኪና ፋሶ ፕሬዝዳንታዊ ዘብ ከሰአታት በፊት መንግስቱን መቆጣጠሩን እና በድንገቱም አስር ሰዎች መሞታቸውን ለማወቅ ተችሏል።ቢቢሲ ወታደሮቹ የመንግስቱን የቴሌቭዥን ጣቢያ መቆጣጠራቸውን እና የእድገት እና የዲሞክራሲ ምክርቤት ፓርቲ መሪ ፕሬዝዳንት ብሌር ካምፓዌሪ ( B. Compaore) የቅርብ ሰው ጀነራል ግልበርት ዴንደረ ( Gen Gilbert Diendere) የሀገሪቱ መሪ እንደሚሆኑ ወታደሮቹ ማስታወቃቸው ተዘግቧል።

ጊዜያዊ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ፕሬዝዳንት ሚቸል ካፋንዶ ( Michel Kafando) እና ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሳቅ ዝዳ (Isaac Zida) ቀደም ብለው በካቢኔ ስብሰባ ላይ ሳሉ ድንገት ዘው ብለው በገቡ ወታደሮች መታገታቸው እና የአስር ወራትን ያስቆጠረ ጊዜያዊ መንግስታቸው መፈፀሙ እንደተነገራቸው ተሰምቷል።የቀድሞ የቡኪና ፋሶ ቅኝ ገዢ ፈረንሳይ ድርጊቱን ተቃውማለች።

የአፍሪካ መሪዎች ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን በአግባቡ መዘርጋት ሲያቅታቸው የጦር ሰራዊቱ ሃገራቱ ”ወደ ባሰ ትርምስ ከመግባታቸው በፊት”በሚል ሰበብ የስልጣን ኮርቻውን ሲቆጣጠሩት ይታያል።በቅርቡ በምስራቅ አፍሪቃዊቷ ሀገር ቡሩንዲ ተመሳሳይ ያልተሳካ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ መደረጉ እና ከእዚያን ጊዜ ወዲህም የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ካለፈው ለመማር አለመቻላቸው ሌላው አስገራሚ ጉዳይ ነው።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s