አቶ ዓሊ ሱሌይማን፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽነር በሙስና ላይ በገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ቁርጠኛ የሆነ አመራር አለመሰጠቱን ገለፁ

Ali

አቶ ዓሊ ሱሌይማን፣ የፌዴራል የሥነ  ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽነር

ባለፈው ዓርብ መስከረም 7 ቀን 2008 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽነር አቶ ዓሊ ሱሌይማን፣ ከጋዜጠኞች ከተነሱላቸው ጥያቄዎች መካከል አንዱ መንግሥታዊው ሥርዓት በሙስና ውስጥ መዘፈቁን በግልጽ እየተናገረ፣ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ግን በመናኛ ጉዳዮች ላይ አተኩሯል የሚል ነው፡፡ የፖለቲካና የሕግ ቋንቋ የተለያዩ መሆናቸውን የተናገሩት አቶ ዓሊ፣ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዕርምጃ የሚወስደው በማስረጃ ላይ ተመሥርቶ ነው በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ጉባዔ ወቅት በሙስና ላይ ቁርጠኛ የሆነ አመራር አለመሰጠቱና ሙስናን መታገል አለመቻሉ ቢገለጽም፣ እከሌ ሙሰኛ ነው ተብሎ መረጃ ባለመቅረቡ ወደ ሕግ ለመሄድ አይቻልም ብለዋል፡፡ መንግሥት አሁንም ሙስናን ለመታገል ቁርጠኛ መሆኑንና እሳቸውም የተረዱት በዚህ መንገድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ‹‹የመንግሥት አመራር በሙሉ ሙስና ስለፈጸመ ስብስብ አድርጋችሁ የምታደርጉትን አድርጉ የሚል መልዕክት አልደረሰኝም፤›› ያሉት አቶ ዓሊ፣ ከሙስና ጋር በተያያዘ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች የሰጡዋቸው ምላሾች በ ቢዝነስና ኢኮኖሚ ገጽ ላይ ተስተናግደዋል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s