(የሳዑዲ ጉዳይ) ኢትዮጵያቷ ሀጃጅ እስከዛሬ አልታወቀችም ነበር – ኢትዮጵያ 13 በላይ ሞተውባታል ፣ 26 ቆስለውባታል ከ204 በላይ ጠፍተውባታል ፣ ፍለጋው ቀጥሏል

nebyu sirak

የማለዳ ወግ…አድካሚው ስራ ፣የጠፉትን ሀጃጆች ፍለጋ ! ኢትዮጵያ … * ኢትዮጵያ 13 በላይ ሞተውባታል ፣ 26 ቆስለውባታል ከ204 በላይ ጠፍተውባታል ፣ ፍለጋው ቀጥሏል * ጅጃ ከተላለፉት ቁስለኞች ኢትዮጵያዊ የለም * ጅዳ ማህጀር የተላፈው ሬሳ ማንነት ገና አልተጣራም * ከማህጀሩ ሬሳ የአፍሪካውያን አለበት ተብሏል * ኢትዮጵያውያን መካ ላይ ለፍለጋው በግል ተደራጅተዋል * ማፈላለጉን በሁሉም ሆስፒታሎች መከዎን ገዷቸዋል * ቤተሰብ ወይም የኢንባሲ ውክልና አምጡ ተብለዋል * በመካው ክሬን የተጎዳች ኢትዮጵያዊት ሀጃጅ ተገኘች * ኢትዮጵያቷ ሀጃጅ እስከዛሬ አልታወቀችም ነበር * ልክ የዛሬ ሳምንት መሞቷ ተጠቁሟል ህንድና ፖኪስታን … * በማፈላልጉ የሳውዲ መንግስት አፋጣኝ እርዳታ ተጠየቀ * የህንድን ፖኪስታን ቆንስሎች መግለጫ ሰጥተዋል * ህንድ 46 ሞቶባታል 62 ቆስለዋል 82 ጠፍተውባታል * ፖኪስታን 46 ሞተውባታል ፣ 8 ቆስለዋል 42 ጠፍተውባታል የጠፉትን ፍለጋና ጭንቅ ድካሙ … ====================== ተቀማጭነታቸውን ሳውዲ ያደረጉ ፣ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ፣ በሀጅ ጸሎት ከአደጋው የተረፉ ሀጃጆችና ቤተሰቦቻቸው በሚና ጀማራት አደጋ የጠፉና የሞቱትን ሰዎች ለማፈላለግ ሌት ከቀን ወደ ሚና ፣ ጀማራትና መካ በመመላለስ አድካሚ የጭንቅ ሳምንት መግፋታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው። የጠፉ ሃጅ ቤተሰቦች በግሩኘና በተናጠል ቢያፈላልጉም በርካታዎች እንዳልተሳካላቸው ይናገራሉ ። በአደጋው የሞቱ ኢትዮጵያውያን ቁጠር ገና ከአደጋ ቀን አንስቶ ከአምስት በላይ መሆኑ ግልጽ እያለ በኢትዮጵያ ኢንባሲ ፣ ቆንስልና የሀጅ ኮሚቴ የሚደረገው ፍለጋ የተቀናጀ ባለመሆኑ ዝርዝር መረጃው ቀርቶ የሞቱና የቆሰሉትን ዙሪያ ትክክለኛ መረጃ አልቀረበም ነበር ። ከብዙ ጉትጎታ በኋላም ትክክለኛውን መረጃ ለህዝብ ለማድረስ በርካታ ቀናት ወስዷል ። አሁንም በኢትዮጵያ ተወካዮች በኩል ቀናት የወሰደው የሞቱና የቆሰሉትን የማሳወቅ መረጃ ቅበላ ከቀናት በፊት ይፋ ቢደረግም አሁንም ቁጥሩ እየጨመረ ከመጣው የሟቾቸ ብዛት አንጻር የመረጃ ክምችቱን የማሻሻል ስራ እየተሰራ አይደለም ! ጉዳዩ ያሳሰባቸው በመካ ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መካ ላይ በሚገኙ በ13 ሆስፒታሎች ፍለጋ ተደራጅተዋል ጀምረዋል ። ያም ሆኖ መሊክ ፈይሰል ፣ ሄራ ፣ ጀበለር ኑርና መሊክ አብደላ በተባሉ ሆስፒታሎች ቢከለከሉም በቀሩት አንዳን ሆስፒታሎች ማፈላለግ ችለዋል። ማፈላለጉን በተወሰነ መልኩ ማሳለጥ ችለው 15 ያህል ቁስለኞችን አግኝተዋል። ነገር ግን የተጠቀሱት ሆስፒታል ሃላፊዎች የቤተሰብ ወይም የኢንባሲ ውክልና አምጡ በማለት የተከለከሉት ወጣቶች ከሀጅ ኮሚቴ ጋር ተቀራርበው ለመስራት የሚየሰደርጉት ሙከራ አለመሳካቱን ገልጸውልኛል! ውክልናውን ወይም መታወቂያ ይሰጣቹሃል ቢባሉም እስካሁን ከኮሚቴው መልስ ባለመሰጠቱ ጥረታቸው መሰናክል እንደገጠመው አንድ የገላጊው ቡድን አባል ገልጸውልኛል ! በአንጻሩ የመሳሳይ ችግር ያለባቸው የአንዳንድ ሀገራት የመንግስት ተወካዮችና ዲፕሎማቶች ነዋሪዉን ለበጎ ስራና በማቀናጀትና በማቀዳጀት በሽዎች የሚቆጠሩ ልዩ የፈላጊ ግብረ ሃይል አቋቁመው በመካ ፣ ሚናና ጀናራት አሰማርተዋል ። የነዋሪውንና የሀጃጆችን ጭንቀት በመረዳትም የቆሰሉትንና የሞቱትን ፎቶ መረጃዎች ከሳውዲ መንግስት በመውሰድ ለዜጎቻቸው አቅርበዋል። በሳምንት የአደጋው አድሜ በዋናነት አሳሳቢ የሆነው ቁርጡ የታወቀው የሞቱትና የቆሰሉት ዜጎች አልሆነም። ሞተው ፎቷቸውና ቆሰለውም ከሆነ ዝርዝራቸው ያልተገኙት ጉዳይ ብዙ ዜጎችን በመንፈስ እያስጨነቀና እያንገላታ ይገኛል። መዳረሻቸው ” ጠፋ” ከሚባሉት መካከል በደረሰው አደጋ ፊታቸው መለየት ያስቸገረ ይገኙበታል የሚል ጥርጣሬ ቢኖርም የሟቾችን ሬሳ ለመለየት የተለያዩ እርንጃዎች ቀርበዋል። ሀጃጆች በገቡበት አሻራ ለመለየት እየተወሰደ ያለው ማጣራት ረዠም ጊዜ መውሰዱ ተቃውሞ እየቀረበበት መሆኑ ይጠቀሳል ። የሳውዲ መንግስት የየጤና ጥበቃና የፖስፖርት ክፍል ኃላፊዎች ስለመለየቱ ስራ ሲናገሩ በሶስት መንገድ እንደሚከወን ያስረዳሉ ። እስካሁን መለየት ያልተቻለውን ሬሳ ለመለየት የቀረቡት ዘዴዎችም 1ኛ / በገቡበት አሻራ 2ኛ / በገቡበት ፎቶ መለየት እና 3 ኛው / የስጋ ዘመድ ቤተሰቦቻቸው እየቀረቡ DNA በመስጠት መለየቱ እንደሚከወን ይናገራሉ ! አሻራቸው የተነሱ ሬሳዎች ውጤት በከነገ ጀምሮ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ቢጠበቅም የተረጋገጠ መረጃ እስካሁን አላገኘሁም ! የሳውዲ መንግስት የጠፉትን በማፈላለግ ሂደቱን እብዲያፋጥንና የዜጎቻቸው እጣ ፈንታ እንዲያሳውቅ ህንድና ፖኪስታን የሳውዲ መንግስት አስቸኳይ እገዛ እንዲያደርግ በተለያዩ መንገዶች ተማጽኗቸውን በማቅረብ ላይ ናቸው ! ይቀጥላል … ነቢዩ ሲራክ መስከረም 20 ቀን 2008 ዓም

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s