የላይ አርማጭሆ ገበሬዎች በህወሓት አገዛዝ ፌደራልና ልዩ ኃይል ፖሊሶች በገፍ እየታፈሱ ወደ እስር ቤት እየተጋዙ ነው

Armachiho

የላይ አርማጭሆ ገበሬዎች በህወሓት አገዛዝ ፌደራልና ልዩ ኃይል ፖሊሶች በገፍ እየታፈሱ ወደ እስር ቤት እየተጋዙ ነው፡፡ ዘረኛው እና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከልዩ ኃይል እና ከመከላከያ ተመርጦ የተውጣጣ ሰራዊት በላይ አርማጭሆ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች ማለትም በሙሴ ባንብ በጃኒካው፣ በገንበራ እና በሌሎች በርካታ አካባቢዎች ያሰራጨ ሲሆን ከሦስቱ ክፍሎች የተጣመረው ኃይል በየገበሬው መንደር ተሰግስጎ በማሸበር በመሳሪያ ገፈፋና በአፈሳ ተግባራት ላይ በሰፊው ተሰማርቶ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በላይ አርማጭሆ ገንበራ ቀበሌ ብቻ • አቶ አራጋው አበራ(የሚሊሻ ኮማንደር የነበረ) • አቶ አወቀ ጎሉ • አቶ ተቀባ ብርሃን • ወጣት ቴዎድሮስ ሙሉ • ወንድሙ ሙሉ እና • ወይዘሮ ደብሬ የኔዓለም የተባሉ ገበሬዎች ታፍነው ተወስደዋል፡፡ እነኚህን ስማቸው የተዘረዘሩትን ጥቂት ድሃ ገበሬዎች ጨምሮ በአገዛዙ የታጠቁ ኃይሎች በየቀኑ ከቀያቸው እየታፈኑ የሚወሰዱት ሰዎች በትክል ድንጋይ ልዩ ኃይል የጦር ካምፕ ውስጥ ታጉረው እደሚገኙ ተገልጿል፡፡ Source – ESAT Radio

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s