በረሃብ አደጋ ላይ ላሉት ኢትዮጵያውያን ምግብ ለማመላለስ ኤርትራ ወደቦቼን ተጠቀሙበት አለች

ከዳዊት ሰለሞን
14 ሚልዮን የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን እስከ ፈረንጆቹ አዲስ አመት ከዝናብ አለመኖር ጋር በተያያዘ ለርሃብ በመጋለጥ እንደሚቸገሩ ተገምቷል ።
food
የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ ነፃነት አስፋው ለሮይተርስ በሰጡት ቃል በቅርበት የሚገኘውን የጎረቤታቸውን የአሰብና የምፅዋ ወደቦች የመጠቀም ፍላጎት እንደሌላቸው አረጋግጠዋል ።
“የወደብ ችግር የለብንም ።ችግራችን በቂ የሆነ ምግብ ወደ አገር ውስጥ የምናጒጉዘው አለማግኘታችን ነው “በማለት ወይዘሮዋ ለሮይተርስ በስልክ ነግረውታል ።
ወደብ አልባዋ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የጂቡቲንና የሱማሌላንድን ወደቦች ትጠቀማለች ።
የእርዳታ ድርጅቶች የኢትዮጵያን የወቅቱን ቀውስ ለመፍታት ከ1.5 -2 ሚልዮን ቶን የሚገመት የምግብ እህል ወደ አገሪቱ መግባት እንዳለበት እየተናገሩ ነው ።
ሁለቱ አገራት ምንም እንኳን በ1991 ደም አፍሳሽ ጦርነት ውስጥ ከገቡ በኋላ ግኑኝነታቸው እንደሻከረ ቢቆይም ኤርትራ ወደብዋን ኢትዮጵያ እንድትጠቀምበት ፈቃደኛ መሆንዋን አስታውቃለች ።
የኤርትራ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ የምትገኘውን ኢትዮጵያን ለመርዳት ያለበትን ግዴታ መንግስታችን ስለሚያውቅና የኢትዮጵያ ህዝብ መንግስት በፈፀመው ጥፋት መቀጣት ስለሌለበት ወደቦቹን እንዲጠቀሙበት ፈቅደናል ብልዋል ።
ኤርትራም ከ1970ዎቹ በኋላ መጥፎው በመሆን በተመዘገበው ድርቅ በመታትዋ ከህዝብዋ ግማሽ ያህሉ 1.4 ሚልዮኑ ችግር ውስጥ ይገኛል ።
የኤርትራን ሁለት ወደቦች ከጦርነቱ በፊት ኢትዮጵያ ስትጠቀምባቸው ቆይታለች ።ከወደቦቹ ወደ አዲስ አበባና ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የሚወስዶ መንገዶችም በአግባቡ ተገንብተዋል ።
በኤርትራ ደቡባዊ ክፍል የሚገኘውን የአሰብ ወደብን ከጦርነቱ በፊት ሙሉ ለሙሉ ትጠቀምበት የነበረችው ኢትዮጵያ ብቻ በመሆንዋ በአሁኑ ወቅት ወደቡ ያለ ጥቅም ይገኛል ።
በጦርነቱ ወቅት ኢትዮጵያ በድርቅ በመታትዋ ኤርትራ በወደቡ እንድትጠቀም መፍቀድዋን አስታውቃ የነበረ ቢሆንም ኢትዮጵያ እንደስላቅ በመቁጠርዋ ሳትቀበለው ቀርታለች ።
የኢትዮጵያ መንግሥት ረጂዎቹ ለእርዳታ ጥሪው ፈጣን ምላሽ ባለመስጠታቸው ወቀሳ እያቀረበ ይገኛል ።
“ከአገሪቱ ክፍሎች እየደረሱን የሚገኙ አዳዲስ ሪፖርቶች በርሃብ ምክንያት ሰዎች እየሞቱ መሆኑን ነው ።ያለ ፈጣን የምግብ እርዳታም የብዙ ሰዎች መሞት የሚጠበቅ ይሆናል “በማለት የኢትዮጵያ መንግሥት ለረጂዎች በላከው መግለጫ አስጠንቅቋል ።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s