በጎንደር እስር ቤት ተቃጠለ * እስረኞች እያመለጡ ነው * የሞቱም የተጎዱም አሉ ተብሏል

በጎንደር ከተማ የሚገኘው ትልቁ እስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ የ እሳት ቃጠሎ ተነስቶ እስረኞች እያመለጡ መሆኑ ተሰማ:: የዘ-ሐበሻ የጎንደር ምንጮች እንደዘገቡት በከተማዋ ከፍተኛ የጥይት ድምጽ ይሰማል:: በጎንደር ከተማ የሚገኘው ባህታ የተሰኘው ወህኒ ቤት የተነሳው የ እሳት ቃጠሎ መነሻ ያልታወቀ ሲሆን ቃጠሎው በወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ በርካታ እስረኞችን እንዲያመልጡ ምክንያት ሆኗቸዋል:: በተለይ ከግድያ ወንጀል ጋር በተያያዘ ተፈርዶባቸው የነበሩ እስረኞች ማምለጣቸው በተለይ በቂም በቀል በሚፈላለጉ ቤተሰቦች ላይ ትልቅ የሆነ ፍራቻን እንደሚፈጥር አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ:: ፖሊስ እያመለጠ የሚገኘውን እስረኛ ለማስቆም በሚተኩሰው ጥይት ከተማዋ በከፍተኛ ሁኔታ መረበሿን የሚጠቁሙት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች እስካሁን ወደ 380 የሚጠጉ እስረኞች ማምለጣቸውን ገምተዋል:: ፖሊስ በሚተኩሰው ጥይት የተጎዱ እስረኞች በአካባቢው በሚገኙ የጤና ጣቢያዎች ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን ቁጥራቸው ያልታወቁ እስረኞችም ሊያመልጡ ሲሉ መገደላቸው ተሰምቷል: በሌላ በኩል በእሳት ቃጠሎው ምክንያት ከእስር ክፍላቸው መውጣት ያልቻሉ እስረኞች የቃጠሎ ጉዳት እንደደረሰባቸው ምንጮቻችን ገልጸዋል::

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s