የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም የተነሳው ተቃውሞ ወደ ቱሎ ቦሎና ወሊሶ አካባቢ ተዳረሰ

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በመቃወም እንደገና በምዕራብ ወለጋ የተቀሰቀሰው የተማሪዎች ቁጣ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች እየተዛመተ ይገኛል:: የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች እንደሚሉት በተለይ ፖሊስ በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች ላይ የፌደራል ፖሊስ ግድያ ከፈጸመና ካቆሰለ በኋላ ይበልጥ ቁጣው እየናረ መጥቷል::

በተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች እየተዳረሰ የሚገኘው ተቃውሞ ዛሬ በቱሉ ቦሎና በወሊሶ አንዳንድ አካባቢዎች ደርሷል:: በነዚህ አካባቢዎች አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በመቃወም ወጣቶች ድምጻቸውን ሲያሰሙ ውለዋል:: በባሌና በወለጋ አካባቢዎች አሁንም ውጥረቱ እንዳለ የሚጠቁሙት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ጉዳዩ አፋጣኝ እልባት ካላገኘ ወደ አስከፊ ደረጃ ሊደርስ እንደሚችል ያላቸውን ስጋት ጨምረው ገልጸዋል:: በተለይም እስከ ትናንት ድረስ በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ የሞቱት ተማሪዎች ቁጥር 3 የነበረ መሆኑና አሁን ደግሞ ወደ 4 ከፍ ማለቱ ጉዳዩን አጡዞት ይገኛል:: ይህ በ እንዲህ እንዳለም ዛሬም በ ም ዕራብ ወለጋ ጉሊሶ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ሲካሄድ መዋሉም ተዘግቧል:: አካባቢውን የፌደራል ፖሊስ ቢወረውም ሕዝቡ ተቃውሞውን በአደባባይ እየገለጸ አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እየተቃወመ ነው::

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s