ኢትዮጵያ ታስራለች!

የዘመኑ ገዥዎች ‹‹ኢትዮጵያ የብሄሮች እስር ቤት ነበረች፡፡ አሁን ብሄሮች ነፃ ወጥተዋል›› ይላሉ፡፡ እውነታው ግን ተቃራኒ ነው፡፡ በትናንትናው ዕለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ‹‹ከእስር ነፃ ወጥተዋል፡፡›› የተባሉትን ‹‹የብሄር ብሄረሰቦች›› ቀን አክብሩ ተባሉ፡፡ በየተራም ተጠሩ፡፡

ታዲያ! ‹‹አሁን ተራው የኦሮሞ ነው!›› ተብሎ ተማሪዎች ትርዒት እያሳዩ እንዲያልፉ ሲጠየቁ ተማሪዎቹ ወደተባለው ቦታ ሳይሆን ከተቀመጡበት ተነስተው ትርዒት እያሳዩ በዓሉ ይከበርበታል የተባለውን ቦታ ለቀው ወጡ፡፡ ያሳዩት ትርዒትም ‹‹ያሰራችሁንስ አሁን ነው! ታስረናል!›› የሚል ምልክት ነበር፡፡

ይህ ምልክት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጥያቄያቸውን ሲያቀርቡ ሲያሳዩት የቆዩት ምልክት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች በየሰልፉ ሲያሳዩት የነበርና አሁንም የሚያሳዩት ምልክት ነው፡፡ አይ ኤስን ለማውገዝ በተጠራው ሰልፍ ላይ ኢትዮጵያውያን ያሳዩት ምልክት ነው፡፡ አሁን ደግሞ ተማሪዎች ‹‹ኢትዮጵያ የብሄሮች እስር ቤት ነበረች፡፡ አሁን ነፃ ወጥተዋልና በዓል እናክብር›› ሲባሉ ‹‹የለም! የታሰርነው አሁን ነው!›› ብለው ምልክቱ አድርገውታል፡፡ የጭቁን ኢትዮጵያውያን ሁሉ ምልክት ሆኗል!

እውነት ነው! ኢትዮጵያ ታስራለች! ጭቁኖች ምልክታቸውን ካወቁ ምን ማድረግ እንዳለባቸውም አይከብዳቸውም!ያኔ ኢትዮጵያ ገዥዎቹ ሳይወዱ በግድ ትፈታለች!

Getachew Shiferaw's photo.
Getachew Shiferaw's photo.
Getachew Shiferaw's photo.
Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s