የአዲስ አበባን ማስተር አዲሱን ማስተር ፕላን በመቃወም በመላው የኦሮሚያ ክልል የቀጠለው ተቃውሞ በአዲስ ከተሞችም እንዲሁ እየተቀጣጠለ እንደሚገኝ ተዘገበ::
መንግስት 2ኛ ሳምንቱን በያዘው የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ ከ7 የማያንሱ ሰላማዊ ዜጎችን ተቃውሟቸውን ለማብረድ ሲል ገድሏል:: ይህም የተማሪዎቹን ጥያቄ ከማስተር ፕላኑ በተጨማሪ ግድያውን የማውገዝም ጭምር እንዲሆን አድርጎታል:: ዛሬ በአዳባ ታውን በተደረገው የተማሪዎች ተቃውሞ ላይ ከተማሪዎች በተጨማሪ እንዲሁ የመንግስት ሠራተኞች እና ሌሎች የማህበረሰቡ አባላት መሳተፋቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል:: ፖሊስ የተማሪውን ስብስብ ለመበተን የሃይል እርምጃ ቢወስድም አሁንም ቁጣው እንዳየለ ምንጮች ዘግበዋል:
Advertisements