የኦሮሞ ወጣቶችን ተቃውሞ በመጠቀም ገዢው መንግስት የኦሮሞን ሕዝብ ከሌላው ሕዝብ ለማጋጨት የሚያደርገውን ሴራ ሕዝቡ በንቃት እንዲመለከት ተጠየቀ

የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን በመቃወም በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች እስከ
ሰው ህይወት ማለፍን ያስተከተለ ተቃውሞ በመካሄድ ላይ መሆኑን ተክትሎ ገዢው መንግስት
የተማሪዎቹን ጥያቄ የሃገር አንድነትን ከመበታተን ጋር በማያያዝ በብሔር ለመከፋፈል
የሚያደርገውን ሴራ ሕዝቡ በንቃት እንዲከታተለው ተጠየቀ::
በተለያዩ የሶሻል ሚዲያዎች ላይ በተለይም የኦሮሞ ሕዝብ ደጋፊና ተቆርቋሪ በመምሰል ሰሞኑን
ተማሪዎቹ እያደረጉ ያሉትን ተቃውሞ በመደግፍ ሌላውን ብሔር የመሳደብ እና የማጥላላት ዘመቻ
መጀመሩን ተከትሎ ይህን የሚያደርጉት መንግስት ያሰማራቸው ካድሬዎች በመሆናቸው ሕዝቡ
በንቃት እንዲከታተለው ተጠይቋል::
ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ የተነሳውን ተቃውሞ እነዚሁ መንግስት ያሰማራቸው
የሶሻል ሚዲያ ካድሬዎች ጥያቄው ወደ ሌላ ብሄር ጥላቻ እንዲሸጋገር በማደረግ ከፍተኛ ሥራ ላይ
እንደተሰማሩ የታወቀ ሲሆን ይህም እንዲደረግ የተወሰነበት ምክንያት የኦሮሞ ተማሪዎች ጥያቄ
የማስተር ፕላን ጥያቄ ሳይሆን የሌላ ብሄረሰብ ጥላቻ እንደሆነ ተደርጎ እንዲወሰድ ነው ተብሏል::
መንግስት የራሱን ካድሬዎች በማሰማራት በኦሮሞ ተወላጆች ስም ሆን ብሎ ሌላውን ብሄረሰብ
በመሳደብ የተማሪዎቹን ጥያቄ ለማፈን የሚያደርገው ጥረት ከዚህ ቀደምም የተሞከረ እንደነበር
ያስታወሱት የፖለቲካ ተንታኞች ባለፈው ዓመት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኙ የአማራ
ተወላጅ ንብረት የሆነ ቤትን በማቃጠል እነዚሁ ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች እንዳቃጠሉት
በማስመሰል ለፕሮፓጋንዳና ለብሔር ግጭት የሚጋብዝ ሴራ ቢጠነሰስም ሕዝቡ የገዢው መንግስት
ሴራ መሆኑን በመረዳት ማክሸፉ ይታወሳል::
በአንዳንድ የኦሮሚያ ክልሎች ተማሪዎቹ ሰላማዊ ጥያቄ ሲያቀርቡ በመሃላቸው መንግስት
ያሰማራቸው ካድሬዎች ሕዝቡ ጋር በመመሳሰል ሌላውን ብሄር የሚሳደቡ መልዕክቶችን አብረው
እንዲናገሩ በማድረግ ሴራ ላይም የተሰማሩ እንዳሉ የጠቆሙት ተንታኞች ተማሪዎቹ ከእንደዚህ
ያሉ ተኩላዎች መጠቀሚያ ሳይሆኑ በሰላማዊ መንገድ ሌላውን ሳይነኩ ጥያቄያቸውን አጠናክረው
እንዲቀጥሎ የፖለቲካ ተንታኞች ምክራቸውን ይለግሳሉ::
ከኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መስሪያ ቤት በሶሻል ሚድያዎች በተለይም በፌስቡክ በኦሮሞ ተወላጆች
ስም ህዝብን ከሕዝብ የሚያቃቅሩ መልዕክተኞች የተሰማሩ መሆኑን የሚጠቁሙት ምንጮች እነዚህ
ሰዎች የሚያስተላልፏቸውንና ብሄርን ከብሄር ሊያጋጩ የሚችሉ መል ዕክቶችን በንቃት
እንዲከታተሏቸው ተጠይቋል።”

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s