አጭበርብረው ለስብሰባ የጠሩት ህዝብ አያገባንም ብሎ ስብሰባውን ረግጦ ወጣ።

የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በአጠቃላይ በቀጠና በቀጠና በመከፋፈል ቤት ለቤት በመሄድ የጥሪ ካርድ በማደልና በእድሮች ጡሩምባም ጭምር ጥሪ በማድረግ አስተዳደሩ የነዋሪውች መኖሪያ ቤት ካርታ ሊታደል ስለሆነ በአሰጣጡ ላይ መወያየት አስፈላጊ ሆኖ በማግኘቱ እንዲሁም ህጋዊ ያልተደረጉ የመኖሪያ ይዞታዎችን ጨረቃ ቤቶችንም ጨምሮ ወደ ህጋዊነት አዙሮ ለሁሉም ባለይዞታዎች ህጋዊ የሚሆንበትን ሂደትም ለማስረዳትና የቤት ካርታቸውን ሊሰጣቸው ስለሆነ በየአካባቢው በሚገኙ የቀበሌና የህዝብ አዳራሽዎች ውስጥ እንዲገኝ ያልተገኘና ስሙን ያላስመዘገበ ከባድ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድበትና ካርታ የማግኘት እድሉም እንደሚመክን በማስፈራራት ጭምር ከሌሊቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ ለቀን 7፡00 ሰዓት እንዲገኙ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ያም ሆኖ ግን ነዋሪዎች በየአዳራሹ በጣም በአነስተኛ ቁጥር የተገኙ ሲሆን በአንዳንድ ቦታም ከአካባቢው ካድሬዎች በስተቀር ሊገኙላቸው አልቻሉም። ባለው ሰው ውይይቱን የጀመሩት ካድሬዎችም የጠራናችሁ በመኖሪያ ቤት ካርታ አሰጣጥ ላይ ለመነጋገር ቢሆንም አሁን አገሪቱ ካለችበት አጣብቂኝ አደጋ ምክንያት በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ነው የምንወያየው ፀረ ልማት የሆኑ የጥፋት ኃይሎች ጠባብ ፍላጎታቸውንና የትምህክት ፍላጎታቸውን በሻብያ አዝማችነት ግንቦት 7 እና ኦነግን ጨምሮ በአገር ወስጥ በተለይም በኦሮምያ ክልል ባደራጇቸው የጥፋት መልዕክተኞች አገሪቱን አተራምሶ ለመበታተንና መንግስት እያካሄደ ያለውን ፈጣን ልማት እንቅልፍ ስለነሳቸው ለማስተጓጎል በኦሮምያ ክልል ብጥብጥና አመፅ አስነስተዋል። በዚህም ምክንያት እናተን ሰብስበን ከመንግስት ጋር ሆናችሁ እነዚህን የጥፋት መልክተኞች እንድታጠፉና እናንተም ሆናችሁ ልጆቻችሁ በዚህ ድርጊት እንዳትሳተፉና ልጆቻችሁንም እንድትመክሩ ለማሳሰብ ነው። የሚል ዲስኩር ቢያሰሙዋቸውም ተሰብሳቢው ህዝብ እኛ የመጣነው ስለ መኖሪያ ይዞታችን ስለ ካርታው ጉዳይ ለመወያየት እንጂ አሁን ስለምትሉት ጉዳይ የምናውቀው ጉዳይ ስለሌለ እናተ አሁን ከምትነግሩን ውጪ ምንም የምንወያየው ነገር የለም ልጆቻችንም ቢሆኑ እኛ ተቆጥተን ከምንም ነገር ልናግዳቸው የምንችልበት እድሜ ላይ አይደሉም። ስለዚህ ይሄ ጉዳይ የእኛ ጉዳይ ስያሆን የራሳችሁ ስለሆነ እዛው ጨርሱ እኛን የሚመለከትን ነገር የለም በማለት ተሰብሳቢዎቹ ስብሰባውን በብዙ ቦታ ላይ ጥሎዋቸው ወጥቶ ወደእየ መኖሪያው ተመልሶዋል።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s