የቤኒሻንጉል ህዝብ ጉሙዝ ተወላጆች ለከፋፋዮቹ እና ዘራፊዎቹ ወያኔዎች ግልጽ ማስጠንቀቂያ ሰጡ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ / መተከል ዞን /አልመሃል ከተማ የጉሙዝ ተወላጆች በከፋፋዩ ወያኔ ላይ ከፍተኛ ጭንቀት ፈጥረዉበታል:: የጉሙዝ ተወላጆች ለከፋፋዮቹ እና ዘራፊዎቹ ወያኔዎች ግልጽ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል:: “በአባይ ግድብ ስም የምታደርጉትን ዝርፊያ አቁሙ እንዲሁም ኢትዮጵያዉያንን እርስ በእርስ ለማጫረስ የምትሰሩትን ዘረኛና ከፋፋይ ስራችሁን በፍጥነት አቁሙ” የሚለዉ ግልጽ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል::
-በተለዬም ሰሞኑን አንድ ወያኔ የአባይ ግድብ አካባቢን እመነጥራለሁ በሚል ሰበብ ኮንትራት በመዉስድ 46 ሚሊዮን ብር አለአግባብ በጥቂት ቀናት ዉስጥ እጁ እንዳስገባ ህዝቡ ስለሰማ ከፍተኛ ቁጣ ዉስጥ ገብቷል
-በአካባቢዉ ሁሉንም የንግድ ስራዎች ማለትም ለቅርጻ ቅርጽ የሚያመቹ ዉድ ዛፎችን፣ፎቅ መደገፊያ መስሪና ዉድ የሆኑ ወደ ዉጭ ሀገር ኤክስፖርት የሚደረጉ ሀብቶችን በሙሉ የወያኔ አባላት ብቻ ተቆጣጥረዉት መገኘታቸዉ ብሎም ሌሎች ማህበረሰቦች ወደዚህ ስራ ሊገቡ ሲሞክሩ በሩ ሁሉ መዘጋቱ ህዝቡን እያስቆጣ ነዉ:: በአካባቢዉ ማዕድን ለማዉጣት: ሌላዉ ቀርቶ የቡልዶዞር ማከራዬት ስራ እንኳን ለመስራት ወያኔ ያልሆነ ሰዉ አይችልም:: በመሆኑም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝብ ከፍተኛ ምሬት ዉስጥ ገብቷል::
– የቤኒሻንጉል ህዝብ የአማራ ህዝብ ጠላት እንደሆነ በማድረግ እራሳቸዉ ወያኔዎች የአማራን ህዝብ እየገደሉና እየጨፈጨፉ የቤኒሻንጉል ህዝብ ነዉ አማራዉን እያፈናቀለና እየገደለ ያለዉ ብለዉ መግለጫ በእኛ ስም ማዉጣታቸዉ ለእኛ ያለቸዉን ንቀት ያሳያል ሲሉ የአካባቢዉ ተወላጆች ወያኔን በገሃድ እየተቃወሙ ነዉ::
– በመሆኑም የቤኒሻንጉ ተወላጆችል ከሌሎች ማህበረሰቦች ማለትም ከአማራዎች: ኦሮሞዎች: ሺናሻዎች: ጉሙዞች እና አገዎች ጋር በመሆን ጠላታችን በዝባዡና ከፋፋዩ ወያኔ ብቻ ነዉ:: እኛ ኢትዮጵያዊ ነን:: እርስ በእርሳችን አታባሉን በማለት በከተማዋ ያሉ የወያኔ ንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት እየፈጠሩ ነዉ::
-የቤኒሻንጉል ህዝብ “እኛ ኢትዮጵያዊ ነን: ለማንም ህዝብ ጥላቻ የለንም:ጠላታችን ኢትዮጵያዊነትን በእርስ በእርስ ጦርነት ሊያጠፋ የተነሳዉ ወያኔ ብቻ ነዉ” ሲል አቋሙን መግለጹ ወያኔዎችን ስላሰጋቸዉ ህዝቡን እንደለመዱት በዘር የመከፋፈል ስራ ለማከናወን እየተዘጋጁ መሆኑም ታዉቋል::

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s