ባህርዳር ላይ እስረኞች ተቃውሞ አሰሙ

ባህርዳር ከተማ ማረሚያ ቤት የሚገኙ እስረኞች የሚደርስባቸውን በደል በመቃወም ከትናንት ታህሳስ 9/2008 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ቤቱ የሚዘጋጀውን ምግብ እንደማይበሉ ማሳወቃቸውንና ጩኸት በማሰማት ተቃውሟቸውን መግለፃቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልፀዋል፡፡ በትናንትናው ዕለት በማረሚያ ቤቱ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ያመልጣሉ በሚል በእግር ብረት ታስረው እንደሚገኙ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን እስረኞቹ በርካታ በደሎች እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡

በተለይ በሽብር ሰበብ የታሰሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ከሚደርስባቸው ድብደባ ባሻገር ህክምና እንደማያገኙም ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ባሻገር በእስር ቤቱ የሚቀርበው ምግብ ለበሽታ የሚያጋልጥ በመሆኑ ከትናንት ጀምሮ እስር ቤቱ የሚያቀርበውን ምግብ አንበላም ማለታቸውና የተቃውሞ ጩኸት ማሰማታቸውም ተገልፆአል፡፡

በባህርዳር ማረሚያ ቤት የሚገኙ እስረኞች ከትናንት ታህሳስ 9/2008 ዓ.ም ጀምሮ ተቃውሞ በማሰማታቸው በዛሬው ዕለት ቤተሰቦቻቸው እንዳይጠይቋቸው እንደተከለከሉም የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልፀዋል፡፡

This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a comment