ኢትዮጵያ መሬት ጠቧት ወደሱዳን ግዛት ለመስፋፋት እየሞከረች ናት ሲሉ በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር አላገጡ

በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር ኦስማን ናፊ Assayha ለተሰኘ አረብኛ ጋዜጣ የሰጡት ቃለመጠይቅ አስገራሚ ነው። ኢትዮጵያ መሬት ጠቧት ወደሱዳን ግዛት ለመስፋፋት እየሞከረች ናት ሲሉ ከሰዋል። የጉዌንን መስመር ተግባራዊ እንዲሆን ከንጉስ ሃይለስላሴ ጋር ስምምነት መደረሱን: ሱዳን በቅንነት መሬቷን ለኢትዮጵያውያን ገበሬዎች መፍቀዷን: በምላሹ የኢትዮጵያ ገበሬዎች የራሳቸው አድርገው በመስፋፋት ከዚያም ባለፈ የሱዳንን ዜጎች በመግደል ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው ይሄን የሚያደርገው ማእከላዊውን መንግስት የተቆጣጠረው የትግራይ ገዢ ሳይሆን የአማራ ክልል መንግስት ነው ብለው ተናገሩ። የዘር ክፍፍል ጨዋታውን እንደ ህወሀት ይችሉበታል። ከሁሉ የገረመኝ የህወሀትን አፈጣጠር የገለጹበት መንገድ ነው። ኢትዮጵያን የሚመራው ገዢ ቡድን ከካርቱም ማህጸን የወጣ ነው አሉና አረፉት ። እኛ ከትግራይ ማህጸን የወጣ ነው ብለን ይሄን ሁሉ ዘመን ቆይተን ከባእድ ማህጸን መፈጠሩ ሲነገረን አጃኢብ አልና ዝም ። ለነገሩ ህወሀት ከትግራይ ማህጸን ቢፈጠር ኖሮ እንደዚህ አረመኔ: ጸረ-ኢትዮጵያ አይሆንም ነበር። …የሱዳኑ አምባሳደር “የድንበሩ ጉዳይ የእኛ የትኩረት አጀንዳችንም አይደለም” ማለታቸውም አስገራሚ ነው። ህወሀት እንዲህ አጣድፎ መሬታችንን ለማስረከብ ለምን ፈለገ ይሆን?

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s