የነጻነትና ሰልፍ ተጠርቱዋል ፤ ሰልፉ የሁላችንም ነው – የሚሊዮኖች ድምጽ

 

“ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሳሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው” ይላል የሕግ መንግስቱ አንቀጽ 30። በዚህ መሰረት በአገሪቱ ተቀባይነት ያላቸው መድረክ እና የሰማያዊ ፓርቲ በጋራና በትብብር ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተዋል። በሕጉ መሰረት ለአዲስ አበባ አስተዳደር አስፈላጊ የእውቅና ደብዳቤ ስገብተዋል። አስተዳደሩም ደብዳቤውን ተቀብሉዋል። መኢአድም ሰልፉን ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ ሰልፍ የአንድ ብሂረሰብ አባል የሆኑ ወገኖች ሰልፍ አይደለም። ይሄ ሰልፍ ለመብት፣ ለነጻነት፣ ለፍትህ የተጠራ ሰልፍ ነው። ይህ ሰልፍ ደርጅቶች በትብብር የጠሩት ሰልፍ ነው። ይህ ሰልፍ የብዙ ብሄረሰቦች ከተማ በሆነቸው አዲስ አበባ የምንኖር በሚሊዮኖች የምንቆጠር ኢትዮጵያዊያን ድምጻችንን የማናሰማብት ሰልፍ ነው። ይህ ሰልፍ እየንዳንዳችን ዘር፣ ሃይማኖት ሳይለያየን በጋራ የምንቆምበት ሰልፍ ነው። ይህ የሕዝብ ሰልፍ ነው።

አገር እያለን ተሰደናል፤ ወገን እያለን ብቸኞች ሆነናል፤ ምግብ እያለን ተርበናል፤ ክብር እያለን ተዋርደናል። ምክንያቱም እኛ ኢትዮጵያዉይን ዝምታን በመምረጣችን፣ በፍርህት በመያዛችን ነው። ግፍን በቃ ባለማለታችን ነው። አሁንስ ይበቃ፤ የፍርሃት ሰንሰለት ይበጠስ፣ ድምጻችንን በጋራ እናሰማ። የሕዝብ ኃይል ምን እንደሆነ እናሳይ። ታህሳህስ 17 ቀን ከፒያሳ ኩባ አደባባይ እንገናኝ። እነርሱ ጥቂቶች ናቸው። እኛ ሚሊዮኖች ነን።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s