ትውልድን በማሰር ነፃነትን ማሰር አይቻልም

አምባ ገነኑ የወያኔ መንግስት በተከታታይ የሚወስዳቸው የአፈና፣ እስርና ግድያ እርምጃዎች ትግሉን ወደ ተሻለ ህዝባዊ ንቅናቄ ከማሳደግ በቀር የነፃነት ተጋድሎውን ፈፅሞ አያደበዝዘውም። ላለፉት 25 ዓመታት በበሳል ፓለቲካዊ ሳይንሳዊ ትንታኔ ስርዓቱን እየተገዳደሩ ያሉት ዶ/ር መራራ ጉዲና ታስረዋል የሚል ወሬ እየተናፈሰ ነው። “ወያኔ ከጫካ ወጣ እንጂ ጫካው ከወያኔ አልወጣም” እና ” ይህ የተራበ ህዝብ መሪዎቹን ቢበላ ተጠያቂ አይደለንም” በሚሉት ወርቃማ አባባሎቻቸው የሚታወቁትን የፓለቲካ ምሁር ወያኔ አያስራቸውም ብሎ መገመትም የወህነት ነው።
ወያኔ ባለፉት አመታት “በህዝብ የተተፋ ቅርሻት” መሆኑን ቢያውቅም የሰራው የዘር ማጥፋት ወንጀል፣ የአገር ክህደት ወንጀል፣ የአገሪቱን ሃብት የመዝረፍ ወንጀልና ሌሎችም ወንጀሎቹ ቀንና ሌሊት እረፍት ስለሚነሱት አጥፍቼ ልጥፋ ብሎ በመንደፋደፍ ላይ ይገኛል። መሰረታዊው እውነት ግን ወያኔ ዳግም ላይነሳ በቅርብ ተሰባብሮ ይወድቃል። በመከራ ውስጥ ያሉ ህዝቦችም ሁለንተናዊ ድልን ይቀዳጃሉ። ሰዎችን ማሰር ይቻላል፣ በውስጣቸው ያለውን የነፃነት ጉልበት ግን ፈፅሞ ማሰር አይቻልም።
ድል ለአገራችን ህዝቦች!”
ሞት ለወያኔና ግብረ አበሮቹ!!

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s