የጎንደር ገበሬዎች ሽፍቶች ናቸው

“ተቆርሶ የተሰጠ መሬት የለም። በመሬት ዙሪያም የተደረገ ድርድር የለም። ድንበር ኮሚሽኖች አሉ፣ ሪፖርት ሲያቀርቡ ሕዝብ ተወያይቶበት ነው ዉሳኔ የሚወሰነው …” ያሉት አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በፓርላማው የሱዳን መሪ ነበር የመሰሉት።

ከኛ አካባቢ እየሂዱ በርካታ ሱዳናዊያንን እየገደሉ የሚመለሱ ሽፍቶች አሉ። እነዚህ ሽፍቶች በሚፈጥሩት ችግር በሱዳን እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል መልካም ግንኙነት ባይኖር ኖሮ፣ ጠንካራ ወዳጅነት ባይኖር ኖሮ በዚህ ምክንያት ሁለቱ አገሮች ወደ ግጭት ሊገቡ የሚችሉበት ሁኔታ ሁሉ ነበር” ነበር ያሉ አቶ ኃይለማሪያም በዚያ አካባቢ መሬታቸውን የሚከላከሉ የጎንደር ገበሪዎች “ሽፍቶች” የሚል ስያሜ ሰጥተዋቸዋል።

የተናገሩት ንግግር በመቃረን፣ የድንበር ኮሚሽን ሪፖርት ሳይሰሙ፣ ህዝቡ ሳይወያየበት የኢትዮጵያ አርሶአደሮች የሚያርሱበትን ቦታ የሱዳን እንደሆነም በይፋ ተናግረዋል።

“በርካታ ኪሎሜትሮች ሱዳን ዉስጥ ገብተው የሚያርሱ እኛም የምናውቃቸው፣ ሱዳኖችም የሚያወቁዋቸው የኛ ባለሃብቶችና ዉስን አርሶ አደሮችም ጭምር አሉ ” ያሉት አቶ ኃይለማሪያም ” ይሆንን የማካለል ሥራ እስከምንሰራ ድረስ እባካችሁ እነዚህ አርሶ አደሮቻችንን አትንኩብን፣ ባለሃብቶቻችንን አትንኩብን ፣ ብለን እሺ አንነካም ብለው በወዳጅነታችን ምክንያት ዝም ያሉዋቸው አርሰው የሚበሉ በርካቶች አሉ” ሲሉ የጎንደር ገበሪዎች የሱዳኖች ተመጽዋቾች እንደሆኖም በመገልጽ ነበር ኩሩ የሆነውን ቴዎርድስ አገር ፣ የጎንደርን ህዝብ፣ በፓርላማ፣ በአደባባይ ያዋረዱት።

አቶ ኃይለማርያም በፓርላማ የተሰጠ መሬት የለም ይበሉ እንጂ፣ ህዝብ ሳያወቁ ስምምነት ተደርጎ እንደተወሰነ የሚታወቅ ነው። በዚህም ምክንያት የሚነሳ ችግርን ለመቁዋቁዋም በሱዳን እና በወያኔ በኩል ከፍተኛ የወታደር ኃይል እንደተሰማራም መረጃዎች ይጠቁማሉ። አቶ ኃይለማሪያም ራሳቸው የኢትዮጵያና የሱዳን የመከላከያ ሰራዎት በዚያ እንደተሰማራም ተናግረዋል።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s