ወጣቱ ፖለቲከኛ ዮናታን ተስፋዬ ለሰአታት ከታፈነ በኋላ ማዕከላዊ እስር ቤት ታስሮ እንደሚገኝ ታወቀ

yonatan Tesfaye

በምርጫ 2007 የሰማያዊ ፓርቲ የወረዳ 17 ዕጩ ተወዳዳሪ ሆኖ የቀረበውና በቅርቡም ከሰማያዊ ፓርቲ ራሱን ማግለሉን የገለጸው ወጣቱ ፖለቲከኛ ዮናታን ተስፋዬ ለሰዓታት ባልታወቁ ሰዎች ታፍኖ ከተወሰደ በኋላ በመጨረሻም ማዕከላዊ የተባለው እስር ቤት እንደሚገኝ የመጡ መረጃዎች አመለከቱ::

እንደ  ምንጮች ከሆነ ዮናታን ተስፋዬን ሕወሓት የሚመራው መንግስት የኦሮሞ ተማሪዎች ሰሞኑን ካነሱት ሕዝባዊ ጥያቄ ጋር ተያይዞ ሊከሰስ እንደሚችል ገልጸዋል::

በማዕከላዊ ከተወሰደ በኋላ ከፍተኛ ድብደባ እንደደረሰበት የተገለጸው ይኸው የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ቤቱም ሲበረበር መዋሉ ተሰምቷል::

“ህዝቡ ነጻ አውጪዎችን መጠበቅ ሳይሆን ራሱን ነጻ መውጣት አለበት” በሚል ሲታገል የቆየው ዮናታን በአንድ ወቅት እስከታሰረበት ድረስ ስለሚያምንበት ሰላማዊ ትግል የሚክተለውን ብሎ ነበር:-

“ሕዝብ የስልጣን ባለቤት ቢሆን ግን በጋምቤላ ፣ በኦሮሚያ ፣ በሶማሌ፣ በአማራው አካባቢ ያሉ አይነት ግጭቶች ውስጥ አይገባም ። ይሁንናም ግን በሰላማዊ ትግል የሚመጣ ስልጣን “እምቢኝ አሻፈረኝ ፤ከተቀመጥኩበት ወንበር አልነሳም” ለማለት አይመችም ። ወደ ስልጣን መውጫ ብቻ ሳይሆን መውረጃውንም ቀድሞ ያበጀ ስርዓት ነው የሚመጣው ። ኢሕአዴግን በሰላማዊ ትግል ከስልጣን ያወረደ ሕዝብ ቀጣዩንም በተመሳሳይ ለማውረድ የሚከለክለው ሀይል አይኖርም ። በ1997 ትልቅ ንቅናቄ ተፈጥሯል፡፡ ግን በትግል የመጣ አልነበረምና ካሸፈ ። ሕዝብ በትግል መውጣት አለበት ። የግድ በሚሊዮኖች መቆጠር የለበትም ።አምስትና አስር ሺህ ሆኖም በህዝብ የበላይነት ፣ በሕግ የበላይነት ስርዓቱን እየፈተነ ፣ የስርዓቱን አገልጋዮች እያሸመደመደ ምንም ማድረግ እንዳይችሉ ምክንያት የሚያሳጣ ሀይል መፍጠር ይችላል ። ይህ ኢትዮጵያ ውስጥ አልተሞከረም ። በ1997 ያን ያህል ሕዝብ አይተን እንደረካነው አሁን ደግሞ በትግል ራሱን ችሎ የሚመጣ ሀይል እንፍጠር ነው አያልን ያለነው ። ሰላማዊ ትግል ሲባል ፖለቲካና ፓርቲ ላይ የታሰረ ይመስላል ፡፡”

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s