ዜና ወልቃይት: የህወሓት ካድሬዎች የወልቃይትን አማሮች በየከተማው እየሰበሰቡ የማስፈራራት ስራ እየሰሩ ይገኛሉ

ኮሚቴዎቻችን ቅስቀሳቸውን አጠናቀው ወደ ጎንደር ከተማ ከተመለሱ በኋላ በእነሱ እግር  ተተክተው የህወሓት ካድሬዎች የወልቃይትን አማሮች በየከተማው እየሰበሰቡ
የማስፈራራት ስራ እየሰሩ ይገኛሉ።ኮሚቴዎች ያሏችሁን ነገር እንዳትሰሙ ፣መከራ  ሊያመጡባችሁ ነው፣ በሰላም መኖር ይሻለናል… የመሳሰሉት አይነት ማስፈራሪያ መሰል
ስብሰባዎች እዬተካሄዱ ነው።
ዛሬ በዳንሻ ከተማ በምዕራባዊ ዞን አስተዳዳሪ ተብየ በአቶ ኢሣያስ መሪነት የማስፈራርያ  ስብሰባ ሲደረግ ውሏል። ነገር ግን ስብሰባው በከፍተኛ ተቃውሞ እና በወልቃይት  አይበገሬነት ተጠናቋል። የወልቃይት አማሮች ደጋግመው እንደተናገሩት ለአማራነታቸው  አስፈላጊውን መስዋዕትነት ለመክፈል በሚገባ ተዘጋጅተው ጨርሰዋል። ከእንግዲህ ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ መመለስ የለም ብለዋል። ጠገዴ ጠለምት እና አርማጭሆ የወልቃይትወገኖቹን ጥያቄ በንቃት እዬተከታተለ ነው። በወገኖቹ ላይ አንዲት ክፉ ነገር ብትፈፀም አፀፋ ለመመለስ ወደ ኋላ አይልም። እንዲሁም ቀሪው የአማራ ህዝበ ከመቸውም ጊዜ
በበለጠ የወልቃይትን የአማራነት ጥያቄ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየተከታተለ ይገኛል።
የወልቃይት አማራነት ይለምልም!!
ድል ለመላው አማራ!

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s