በኦሮሚያ በሚገኙ የክፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ባሉ የአማራ ልጆች ጉዳይ ከቤተ አማራ የተሰጠ ማሳሰቢ

በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በሚገኙ የክፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ባሉ የአማራ ልጆች ጉዳይ ከቤተ አማራ የተሰጠ ማሳሰቢያ

መላው የኦሮሞ ህዝብ በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ አገዛዝ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ማሰማት ከጀመረ ውሎ አድሯል። ህወሓት የመብት ጥያቄ ባነሱ ንፁሃን ላይ የሚያደርገውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ቤተ አማራ አጥብቆ ይቃወማል፡፡ ከዘህ በፊት በደረሰው ኢሰብአዊ ድርጊትም የተሰማውን ልባዊ ሃዘን መግለጹ ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሞ ክልል ባሉ የዩንቨርስቲ ተማሪ አማሮች ላይ እየደረሰ ያለው ከመጠን ያለፈ እንግልት፤ ለአብነትም በሁለት የአማራ ተማሪዎች ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ  እና ሴት አማራ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመው አስገድዶ መደፈር ቤተ አማራን እጅግ አሳዝኗል። ከኦሮሞ አመፅ ጋር ምንም ግንኙነት በሌላቸው ንፁሃን የአማራ ወገኖቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለው መከራ በጠቅላላው እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡ እንደ ቤተ አማራ እምነት ከዚህ ድርጊት ጀርባ ሙሉ ለሙሉ ለማለት በሚያስደፍር መልኩ የህወሓት የደህንነት ቡድን እጅ አለበት። በኦሮሞ ተወላጆች የመብት ጥያቄ ተወጥሮ የተያዘው ህወሓት አንዳንድ የስርአቱ ታማኝ አገልጋይ ኦሮሞዎችን በመጠቀም በአማራ ልጆች ላይ ግድያ እና ድብደባ እያካሄደ ነው። በዚህም እኩይ ተግባር የኦሮሞን አመፅ ገልብጦ ሙሉ ለሙሉ የኦሮሞ እና የአማራን ህዝብ የዘር ግጭት ውስጥ ለማስገባት የታለመ እንደሆነ ለመገመት ከባድ አይደለም፡፡

በመሆኑም ቤተ አማራ ለአማራ ተወላጆች እና ለሚመለከታቸው አካላት የሚከተሉትን ማሳሰቢያዎች ያስተላልፋል፡-

1ኛ) በኦሮምያ ክልል ውስጥ ባሉ ዩንቨርስቲዎች ያላችሁ የአማራ ተማሪዎች ህብረታችሁን አጠንክራችሁ እርስ በእርሳችሁ በንቃት እንድትጠባበቁ፣ መረጃዎችን በፍጥነት እንድትለዋወጡ እና ፈፅሞ የተናጠል እንቅስቃሴ እንዳታደርጉ

2ኛ) በአማራ ክልል ውስጥ እንዲሁም በአዲስ አበባ የምትገኙ የአማራ ዩኒቨርሲቲዎች እና የመሰናዶ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የወገኖቻችሁን ሁኔታ በንቃት እንድትከታተሉ፣ አስፈላጊ እና አመች በሆነ ጊዜም ለወንድምና እህቶቻችሁ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም አጋርነታችሁን የሚያሳዩ እንቅስቃሴዎችን እንድታሳዩ

3ኛ) በመላው አማራ የሚገኙ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ የንግድ ተቋማት እና ሰራተኞቻቸው፣ ፖለቲከኞች እና ማህበራት በአማራ ተማሪዎች ላይ በሕወሓት አጋፋሪነት እየደረሰ ያለውን መከራ በጥብቅ ታወግዙ ዘንድ ቤተ አማራ ጥሪውን ያስተላልፋል

4ኛ)  መላው የኦሮሞ ህዝብ በተለይ የኦሮሞን የመብት ጥያቄ በማስተባበር ፊት ለፊት ያላችሁ ፖለቲከኞች የአማራ ህዝብ በሕወሓት የዘር አፓርታይድ ስርአት በከፍተኛ ሁኔታ እየማቀቀ ያለ ህዝብ መሆኑን ተረድታችሁ፣ ህወሓት እያቀነባበረው ባለው ወጥመድ ውስጥ እንዳትጠለፉ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ ቤተ አማራ አበክሮ ያሳስባል። 

ድል ለአማራ ህዝበ! 
ድል ለቤተ አማራ!

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s