ትግሉን በአሸናፊነት ለመጨረስ መወሰድ የሚገባቸው ዋና ዋና ነገሮች – ለሰአሊ አምሳሉ ላወጡት ፁሁፍ መልስ

ከኢልማ ኦሮሞ

የዚህ ፁሁፍ ዋና ሃሳብ በ13/01/2016 ሰአሊ አምሳሉ የሚባሉ ግለሰብ በሳተናው ድህረ ገፅ ላይ  ለወቅታዊ ጉዳዮች አስመልክተው ላወጡት ፁሁፍ መልስ ልሰጥ ነው ።

Amsalu  pic -  satenaw
ሰአሊ አምሳሉ

ለፁሁፋቸው የሰጡት ርዕስ “ለኦነግና ኦነጋዊያን “  ያስተላለፉት መልዕክት ነው ከርዕሱ እንደምንረዳው በመላው ኦሮሚያ ተቀጣጥሎ እስከ አሁኑዋ ሰአት ድረስ ለመቶዎች የህይወት እልፈት ለሺዎች መታሰርናበከፍተኛ ደርጃ ተደብድበው በየሆስፒታል መገኘት በግንባር ቀደምትነት በአለማችን ላይ ተበትነው ባሉት ኦሮሞ ኢትዮጵያዊያን የተቃውሞ ሰልፎች ምክንያት የሆነው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንና በፊንፊኔ ዙሪያ ያሉትን የኦሮሚያ ልዩ ዞኖችን ሊያጠቃልል ታልሞ የተዘጋጀ ማስተር ፕላን ተቃውሞ የእንተባበር ጥሪ እንደማይሰራ ነገርከን የእቀረብካቸውን ምክንያቶች በዝርዝር ከማየታችን አስቀድሜ ርዕስህ ላይ አስተያየት ልስጥ
እንዳልከው ይህንን ተቃውሞ ያደረጉት ኦነግና ኦነጋዊያን ከሆኑ ድፍን ኦሮሚያ የኦነግ ደጋፊ ነው እያልከን ነውና ኦነግ ያነሳው ጥያቄ በኦሮሚያ ገዢ ሃሳብ ነውና ከዚህ የፖለቲካ ሃይል ጋር እንዴት መደራደር እንዳለባችሁ አስቀድማችሁ ልታውቁበት በተገባ ነበርግን እንደአለመታደል ሆኖ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ዳይናሚክስ ለመረዳትአልቻላችሁም እንደገና ተቀምጣችሁ ልታስቡ ይገባል። ይህንን ሀሳብህን የሚጋሩ እጅግ ብዙ ሰዎች ስላሉ ነው ለዚህ ፁሁፍህ መልስመስጠት የፈለኩት እንጂ እንደ ሌላው የወያኔሀሳብ  ነው ብዬ መግፋት ያልፈለኩት እንግዲህ ወደ ዋናው ሀሳብህ ልግባ

1. ይህ ተቃውሞ በአንተ ግምገማ ምንም ውጤት እላመጣም ወደ ፊትም ለውጥ አያመጣም ብለሀል ይገርማል በጣም በዚህ ድምዳሜ ላይ መድረስህ የፖለቲካ ስብህናህን እንድመዝነው እድርጎኛል ምክንያቱም ይህ ተቃውሞ በይዘቱም ቢሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ከተደረጉት ተቃውሞዎች ማጋነን ባይሆን በግምባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው እዚህም ላይ ደግሞ ልዩ የሚያደርገው ገዢው መንግስት 100% አሸነፍኩ ብሎ የፈለገውን ነገር ማድረግ በሚችልበት ሰሃትመሆኑ ልዩ የደርገዋል ወዳስገኘው ውጤት ስንመለስ ልክ እንደ ሁለቱ የንዋይ ልጆች መንግስቱና ገርማሜ ንዋይ ፍርሀትን ጠራርጎ ዛሬም በህዝባዊ ተቃውሞ መንግስትን መገልበጥ ይቻላል መንፈስን አሰርፆ ያልፈ ሂደት ነው፤ በተለይ በኦሮሞዎች ዘንድ ቀጥተኛ መልዕክት አስተላልፎዋል ከዚህምባሻገር በተቃዋሚው ዘንድ ይበልጥ ኢሳትንና ኦ.ኤም.ኤን ንአቀራርቦዋል ይህበተቃዋሚው ጎራ እንደ ትልቅድል የሚቆጠር ነው እንግዲህ የጠበከው ውጤት ምን እንደነበር አንተ ታውቃለህ ይህ የኦሮሞ ህዝብ ወያነ ለ25 አመት የሰራውን ስራ ሲያፈርስበት ከማየት ውጪ ሌላ ውጤት መጠበቅ በራሱ የሀገሪቱዋን ነባራዊ ሁነታ ካለመገንዘብ የሚመነጭ ግምገማ ይመስላል

2. ያልካቸው ኦነግና ኦነጋዊያን በሚያሳዝንህ ሁኔታ ስርነቀል ለውጥን ያለመፈለጋቸውን በሁለት ምክንያቶች ልታሳየን ሞክረሀል እነርሱም

ሀ.የማስተር ፕላኑ ጉዳይ ጥያቄው የመላው ኢትዮጵያ ጥያቄ ሆኖ ሳለ የኦሮሞ ጥያቄ ሆኖ እንዲታሰብ በመደረጉ መንስኤው ላይ ሳይሆን ውጤቱ ላይ በማትኮራቸው

ለ. መስራት የሚገባቸውን የቤት ስራ ሳይሰሩ ሰለቀረቡና መስራት ስላልፈለጉ
እስቲ በሁለቱ ምክንያቶችህ ላይ ልሂድበት በእንድ ማህበረሰብ ውስጥ ሁልጊዜም ጥያቄ ሲነሳ የማህበረሰቡን ወቅታዊ ችግር ያገናዘበ ሆኖ ነው የሚጀምረው ስለዚህ በወቅቱ ምንም እንኩዋንይህ ህዝብ ብዙ ጥያቄዎች ቢኖሩትም የተቃውሞው ማጠንጠኛ እጅግ ቀላልና አካባቢያዊ ገፅ ይዞ ነው የሚነሳው ተቃውሞውን ከአካባቢያዊ እይታ ሊያወጣው የሚችል ንቅናቄውን የጀመረው አካል ሳይሆን የንቅናቄውን አድማስማስፋት ያለበት ንቅናቄውን የሚቀላቅል ሌላኛው የህብረተሰብ ክፍል ነው ለምሳሌ ኦሮሞ በማስተር ፕላይ የጀመረውን አማራው አካባቢያዊ ጥያቄውን ለምሳሌ ለሱዳን የተሰጠውን መሬት በምቃወም ጋምቤላው  መሬቱን ደቡቡ ለምሳሌ ሲዳሞው የራሱን አካባቢያዊ ጥያቄ ቢያነሳ ንቅናቄው ሀገራዊ ወደ መሆን ያድጋል። ዋናው ነገርኦነግ ያላሰበውን ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ነው ካልክ ሌላላው ጥያቄ እንኩዋን ባይኖርብህየኦሮሞ  ተማሮዎች ጥያቄ የእኔም ጥያቄ ነው ብሎ ቢወጣ ኢትዮጵያዊነትን መስበክ ለእኔ ይህ ነው የጋምቤላው ህመም ህመሜ ሳይሆን የጎንደር እስረኞች ችግር ችግሬ ሳይሆንኢትዮጵያዊ መሆን የምችል አይመስለኝም ይህንን የምልህ ለፖለቲካል ኮሬክትነስ አይደለም

መስራት ያለባቸውን የቤት ስራማ ጠንቅቀው ሰርተው ነበር ነገር ግን ቅን ማህበረሰብ ስላልነበረ እንዲህ ሆንን ይህም የሆነበት ዋናው ምክንያት መግባባትና የምንፈልገውን ነገር ብግልፅ መረዳት ባለመፈለግ የመጣ ችግር ነው የማየው ኦሮሞ በቅርበት እንደምከታተልው ከሆነ ሁሉም የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች ግልፅ የሆነ ራዕይ አላቸው ኦነግን ጨምሮሁሉም ማለት በሚቻል ደረጃ በማንም ቀዬ ላይ የማንንም አለቃነት አንቀበልም እራስ በራስ ማስተዳደር ይህ ካልተቻለ ግን የራስን መንግስት መመስረት ነው የሚሉት ይህ ደግሞ ሌላ አጀንዳ ከለለህ በስተቀር ተገቢና ሌጂትመንት የሆነ ጥያቄ ነው ።  የብሄርን ስምይዞ መደራጀት የብሄሩን መብት ለማጠበቅ ነው ምክንያቱም እንደ ኢትዮጵያ ባለ ሀገር ውስጥትገቢና ትክክለኛ አደረጃጀት ነው

3. ደጋግመህ ለመግለፅ እንደሞከርከው ተቃውሞው ብስለትና ትክክለኛነት የጎደለው የጅል ለቅሶ እንደሆነ ነው ግንህዝባዊ ትግልን እንዲህ በድፍረት ለማጣጣል መሞከር የሚገርምና ተመጣጣኝ በሆነ ንቃተ ሂሊና ላይ ላለመሆናችን  ትልቅ ማሳያ ነው ይህን የምልህ በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው

ሀ. ከላይ ለማለት እንደሞከርኩት ማንኛውም  ተቃውሞ ሲነሳ አካባቢያዊና የህዝቡን ሳይኮሎጂካል መክእፕ ባገናዘበ ነውየሚጀመረው ነገር ግን ሌላው ማህበረሰብ ተቃውሞውን ሲቀላቀል ትግሉን ያሳድጋል

ለ. አሁን ያለው ለ25 አመታት በገዢው መንግስት ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ የኖረ በ አንድ ለ አምስት ተጠፍንጎ ያለ ትውልድ ነው ተዲያ ይህንን ህዝብ ገና ከጅማሬው ኢትዮጵያ ብለህ ውጣ ብትለው የሚሰማህ አይኖርም ስለዚህ ሌላው ሀይል መጥቶ እስኪቀላቀል ድረስ ተቃውሞውበመጣበት መንገድ ምሄዱ ተፈጥአዊ ነው

4.በተቃውሞው ላይ ተነሱ ያልካቸው የኦነግን የትግል ግብ ያነገቡ ናቸው አልከን
አየህ ወዳጄ እንዲህ ባልክ ቁጥር እያስረገጥክልን ያለሄው የኦነግ ሃሳብ በክልሉ ገዢ ሃሳብ ነው እያልከንነው አንድ ሃሳብ ኦነግ ስላነሳው ብቻ  ስህተት የሚሆንበት ምክንያትሊገባኝ አይችል። በእውነት ከሆነ የምንነጋገርው በዚህ ተቃውሞ ውስጥ የኦነግ ድርሻ እጅግ አናሳ ነው።  እንዲህ ስልፈፅሞ ውስጥ የለም ለማለት ማናችንም አንደፍርም የኦሮሞ አክቲሺስቶች እናንተ መስማት የምትፈልጉትን ካልነገራችሁ ሁሌም ጠላቶቻችሁ እንደሆኑ ማቅረብ ካለመብሰል የሚመነጭ እንጭጭ ሀሳብ ነው ። በዚህ አጋጣሚ ትልቅ የቤት ስራ ይጠብቃችሃል ዘመን ያለፈበት አሮጌ አስተሳሰብ ይዘህ ሀገርን የሚያክል ትልቅ ፕሮጀክት መስራት አትችልም ። አየህ የኦሮሞ ህዝብ አንተ እንዳከው ደንቆሮ ህዝብ አይደለም የሚፈልገውን ጠልቅቆ የሚያውቅ ህዝብ ነው ይህንን ወርቃማ አጋጠጣሚ የልተረዳሄው አንተና መሰሎችህ ናችው

5. ለላውእንድንነግር የፈለከው ከወያኔ ጋር ልዩነታችንን ነው

አየህ ወዳጄ ከወያኔ ጋር የሚለየን ብዙ ነገር አለ እስቲ ጥቂት ልዘርዝርልህ
. ኦሮሞ እንደ ማህበረሰብ በምስራቅ አፍሪካ  እጅግ ብዙ ህዝብ የሆነ በኢትዮጵያ   ከግማሽ በላይየሆነ ምንም አይነት ኮምፕሌክስ የለለው በኢትዮጵያ ውስጥ እውነተኛ ዲሞክራሲን ለማስፈን ብቃቱን ያለው የሀገሪቱዋ የኢኮኖሚ ማዕከል የሆነ እርሻ ቢሆን ቡናው ቢሆን ወርቁ ቢሆን በሃገራችን ኢኮኖሚ ላይ ከ80% በላይ ኮትሪቢዩት የሚያደርግ እስከዛሬ በነበሩት መንግስታት የበይ ተመልካች የሆነ ይቅር ባይ ቻይ ግሩም የሆነ ህዝብ ነው
. ወያኔ ግን በተቃራኒው አናሳ  የሆነ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ምንም ኮንትሪቢዩት የማያደርግ በበታችነት ከዕምፕሌክስ የሚሰቃይ ተራ ወንበዴ ነው እንደትስ አድርገህ ነው የምታወዳድረን እኛን እንደ ጥፋት ሃይል ማየት የቤት ምሶሶን ነቅለህ ግርግዳውን እንደ ማሰማምር ነው የምናየው  ይህ ግን ሊገባህ ስለማይችል አንብበው የሚረዱ አይጠፉም ብዬ ነው በዝርዝር አየሄድኩበት ያለሁትኝ

6.በመጨረሻም እንደ ማስጠንቀቅም ይቃጣሃል በዚህ አጋጣሚ አንድ ነገር አስረግጬ ልንገርህየኦሮሞህዝብ ከዳር እስከ ዳር በታቃውሞ ሲነሳ እንኩዋንስ እማራና ለላው ህዝብ ትግሬዎችን እንኩኻን ከለላ አድርጎላቸው አንድም ክፉ ነገርሳያደርግባቸውነበር  ተቃውሞውንበገዢው ፓርቲ ላይ ብቻ ያደረገው የኦሮሞ ህዝብ ልክ ከ እንዳንተ እይነቱ ጅል ጋርም የጎንዮሽ ትግል እያደረገ ወደ ግቡ አንደሚሄድ አትጠራጠር ትግሉን የምትቀላቀለው ኦሮሞን ወደ ስልጣን ለማምጣት ነው ብለህ የምታምን ከሆነ ይህ አካሄድህትግሉን በጣም ውስብስብ ከማድረጉም በላይ የምትፈራው እንዳይደርስብህ ስጋ
ወያኔ እንድ ነገር በግልፅ የገባው ይመስላል ያውምከዝህ ቦሃላ  ይህን የኦሮሞን ህዝብ እንደከዚህ ቀደሙ መግዛት እንደማይቻል  ደደብ ካልሆኑ በስተቀር ደርሶዋቸዋልስ ስለዚህ ሊያደርጉት የሚችሉት መላምቶች ልንገርህ

ሀ. እስከተጠየቁበት ጫፍ ድረስ ሄደው የኦሮሞን ጥያቄ ለመመለሰ ይጥራሉ
ለ. ያንን በማድረጋቸው ኦሮሞና እማራ  ለዘላለም እንዳይግናኙ የደርጋሉ
መ. ከዚህ ብሃላ ተሰደው ውጪ ሀገር መኖር ስለማይፈልጉ ሀገሪቱዋን ብበመከፋፈል ህልማቸውን ትግራይ ገብተው ይኖራሉ አማራን ብቻውን እይፈሩትም ኦሮሞን ከአማራ መነጠል በጣም ቀላል ነው  ።  አማራ እንደ የሞተች ካርታ ይዞ ነው ያለው  ጌሙን ከኦሮሞ ጋር ሆኖ ካልተጫወተው ትልቅ ሽንፈት ይገጥመዋል
ይህንን ነው አማራ  ሊሂቃን መረዳት ያቃታቸው ይህ እንዳይሆን የተከፈለ ዋጋ ከፍላችሁ ከኦሮሞ ጋር ማበሩ ይጠቅማል ። ካልሆነ ግን ይህ ትምክህት  ዋጋን ያስከፍላችሃል

ፁሁፌን ለማጠቃለል  የኦሮሞ የትግል ትብብር መጠየቅ በአንዳንድ የአማራ ሙሁራንዘንድ የተዛባ አመለካከት ከመፍጠሩ የተነሳና ትብብሩን ወደ ባሰ ጫፍለመውሰድ የሚደረገውን ሂደት ቢቻል ከሀዲዱ ሳይወጣ እንደ አንድ ኦሮሞ የሚሰማኝን ለማለትና በዚህ የትብብር ስራ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ለማስገንዘብ ጭምር ነው
ሁላችንም ስለ ትብብር ስናነሳ ሁለት መሰረታዊ ነገሮችን በማሰብ ይመስለኛል *.የወቅቱ የትግል ስልት ተወደደም ተጠላ የሚጠይቀው ትግሬን ጨምሮ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍ ያለውን መንግስት ተብዬውን የወያኔ ኢህዲግ አምባገነን ቡድን ቢቻል ለማስወገድ ባይቻል ግን አስገድዶ የህዝብን ጥያቄ እንዲመልስ ለማድረግ ይመስለኛል

*ወደፊት የሚመሰረተውን መንግስት ዲሞክራሲያዊ ለማድረግና በዚህ ትግል ውስጥ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣና በኦሮሞ ህዝብ የተጀመረውን ትግል ከግብ ለማድረስ እብሮ ማበርና መተባበር ወቅታዊና በአገራችን ነባራዊ ሁኔታ የግድ ልንተባበርና ጥቃቅን መለያየቶችን ወደፊት በሚደረገው ትግል በይደር አልፎ ትልቁን ዘንዶ አስወግደን በመነጋገርና በሰጥቶ መቀበል መርህ በድርድር ለንፈታቸው ይመስለኛል እንጂ ከአማራው ጋር የነብረንን የፖለቲካ ትግል ምንም እንዳልተፈጠረ አድርገን አይደለም:: ሁላችንም እንደምናውቀው ይህ ሰዎችን ከቄያቸው ማፈናቀል ዛሬ ወያኔ የጀመረው አይደለም ከአፄ ምንልክ2ኛ ጀምሮ የነበረ እስከ ዛሬም ቀጥሎም ያለ ነው ለዚህ ማስረጃው ፊንፊኔ ውስጥ ከዛሬ 130 አመትበፊት የኦሮሞ ቁጥር ከ99.8 በመቶ የነበረ ዛሬ ላይ 19 በመቶ ኦሮሞ የዛሬይቱዋ አአ ውስጥ ይኖራል:: ስለዚህ እንተባበር ስንል በእውነተኛ ዲሞክራቲክ ኢትዮጵያ ውስጥ የኦሮሞ ህዝብ ተጠቃሚ ይሆናልሁላችንም በአሸናፊነት እንወጣለን በማለት እንጂ አንዳንዶች እንደምታስቡት የትግሬውን አምባገነን አስወግደን የአማራውን ቡድን ወደ ስልጣን ለማምጣት በማሰብ አይደለም

ድል ፍትህ ለሚሻ

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s