“አጼ ቴዎድሮስ ማን ናቸው?”

By: አማራ ልበ ብርሃን
አፄ ቴዎድሮስ፣ ከአፄ ልብነ ድንግል ጀምረን ስንቆጥር 11ኛው
ትውልድ ላይ በክብር ተቀምጠው እናገኛቸዋለን። ይህም ሀረግ
በአባታቸው በኩል ያለው ሲሆን፣ ከአፄ ልብነ ድንግል ጀምሮ
የተዘረጋው የዘር ሰንሰለት የሚከተለው ነው፦
1.አፄ ልብነ ድንግል
2.አቤቶ ያዕቆብ፣
3.ገራም ፋሲል፣
4.አፄ ሱስንዮስ፣
5.አፄ ፋሲል፣
6.እመቤት ሰብለ ወንጌል፣
7.ደጃዝማች አንስጤ፣
8.ደጃዝማች ኤልፍዮስ፣
9. ደጃዝማች ወልደ ጊዮርጊስ፣
10.ጌታው አቶ ኃይሉ፣
11. አፄ ቴዎድሮስ!
ይህንን የአባት ሀረግ፣ ኢ/ር ታደሰ ብጡል እና ሌሎች ምሁራን ምንጭ እያጣቀሱ ከመፃፋቸውም በላይ፤ አፄው ራሳቸው “የኮሶ ሻጭ ልጅ እንጂ የነገስታት ዘር አይደለም” የሚለውን አሉባልታ ለማረም፤ ራሳም ለተባለው የእንግሊዝ ልዑክ የነጋሲ ዘር-
ሀረጋቸውን መዘውለታል። ጳውሎስ ኞኞም፣ በጥልቅ የታሪክና የባህል ትንታኔ ተመርኩዞ፥ ካሳ የኮሶ ሻጭ ልጅ የተባሉት በእናቱ ጠላቶች የፈጠራ ወሬ እንደነበር በመፅሀፉ አስፍሯል። የአቶ ገሪማ ታፈረ መፅሐፍም የካሳ እናት (ወ/ሮ አትጠገብ) እንኳን ከድሀ ቤተሰብ ልትወለድ ጭራሽ የገዢ መደብ ልጅ መሆኗን ጠቁመዋል። ባጭሩ ካሳ በእናቱ በኩልም የራስ ወዳጆ
(የአትጠገብ አያት) ዘር ነው። ስለዚህ፥ ካሳ በናቱም ባባቱምcየገዢው መደብ ሐረግ እንጂ፣ ዛሬ የህወሓት ቡችሎች እንደሚሉት “የጭቁኑ የኮሶጌ ቅማንት” ዘር አልነበረም!
:
ይህንን የሚያጠናክር አንድ የፈረንጅ ማስረጃ ጣል ላድርግላችሁና
ልሰናበት!’ሆርሙዝ ራሳም የተባሉ የአፄው እስረኛም በመፅሀፋቸው እንዲህ ይላሉ፦
“አስተርን እንደፃፈው እናትየዋ ኮሶ ሻጭ መሆናቸውን ለማጣራት ሞክሬ ነበር። አንድም ሰው ኮሶ ሲሸጡ አይቻለው የሚል ምስክር አላገኘሁም። ያነጋገርኳቸው ሁሉ የሚነግሩኝ የባላባት
ዘር መሆናቸውን፡ አባቶቻቸውም የአማራ ሳይንት ራስ
መሆናቸውን ነው…በአበሻ ውስጥ ታላላቅ ከሚባሉት ሰዎች ዘር መወለዳቸውን ነው ያጣራሁት።”
*
*
*
ምንጮች፦
1). ኢንጂኔር ታደሰ ብጡል፡ “አፄ ቴዎድሮስ እና ልዑል
አለማየሁ፤ ገፅ 9”
2). እርቅይሁን በላይነህ፡ “የኢትዮጵያ ታሪክ፡ ከኢማም አሕመድ
እስከ ዐጤ ቴዎድሮስ፤ ገፅ 44”
3). ጳውሎስ ኞኞ፡ “አጤ ቴዎድሮስ”
4). ገሪማ ታፈረ፡ “አባ ታጠቅ ካሳ የቋራው አንበሳ”
5). Rassam H. “Narrative of the British Mission to
Theodore, King of Ethiopia.”

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s