ዳሪና ቀባሪ (ወለላዬ ከስዊድን)

weddingd23 -satenaw

ዳሪ

ወዳጄ እንደምነህ  – ውዱ  ጎረቤቴ

ባለህበት ቦታ – ይድረስህ መልክቴ

የልጄ ሰርግና – የሟች ልጅህ ቀብር

አንድ ላይ መሆኑ  – ፈጥሮብኛል ችግር

መቼም ይገባሃል – ግልጽ ነው ነገሩ

ብዙ ነው ማዕረጉ –  የሠርገኛ ክብሩ

ስለዚህ አደራ – የልጄን ታላቅ ሠርግ

በደስታ በሆታ – እንዳሳልፍ በወግ

በዛ ቀን ተነስተህ – ልጅህን ስትቀብር

ስዎችን ሰብስበህ – አታብዛ ግርግር

እንደውም ጨርሶ – ከሞት ላታድናት

በሳቅ በደስታ – በ`ልልታ ቅበራት

ለለቅሶኛው ሁሉ – ይኼን ንገርልኝ

ነገ ማታ ድረስ – መልስህን ላክልኝ

      ቀባሪ

ክቡር አስተዳደር- የላኩልኝ መልዕክት

እጅግ አስገራሚ  – ድንቅ ነው በእውነት

ታስራ ተገንዛ  –  ልጅ ልትቀበር

ተሞሸረች አሉኝ – የርስዎ ልትዳር

ለክብርዎ ሲባል – ለርስዎ ወግ ማዕረግ

እንድስቅ አዘዋል – ለቅሶዬን በመንፈግ

እንደዚህ አድርጎ – ቀኑ ከከበደ

በርስዎ አስተዳደር – ታምር ከወረደ

ሀዘንና ደስታ – መውጣቱ መውረዱ

አንድ ስለሆነ – ሁለቱም መንገዱ

መቼም ምን ይደረግ – በእልልታ ልቅበራት

እርስዎም ልጅዎን –  በለቅሶ ይዳሯት

ወይም ደስታ ሀዘን – እንዳይቀያየጥ

ስምምነት አ’ርገን – ቤት እንለዋወጥ

እግረ – መንገዱንም –  በዚህ – አዲስ መንገድ

መከራን ይቅመሱ – እኔም ደስታ ልልመድ

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s