ህወሃት ኢህአዴግ:ጠቅላ ሚኒስቴር ሃይለማርያምን ሳያሽቀነጥራቸው አይቀርም!!!

ከመጀመርያውኑ በአቶ ሃለማርያም ደሳለኝ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት መሾም ያልተዋጠላቸው ከፍተኛ የኢህአዴግና ህወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ አባት እንዲሁም ብዛት ያላቸው ነባር የድርጅቱ መስራች ታጋዮች በአሁኑ ሰአት የፈነዳባቸውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በድርጅቱ ውስጥ ለሁለት የተከፈለ አቋም በመያዝ በተደጋጋሚ እንደመንስኤ ችግር ከተወያዩባቸው ጉዳች አንዱ አዲስ የስልጣን መዋቅር በመፍጠር አሁን እየሞተ የሚገኘውን የኢህአዴግ ሃያልነት ዳግም ነብስ ለመዝራት የድርጅቱን የሃይል ገፅታ የማይወክሉ አባላትን የማፅዳት ሂደት ሲሆን በአብላጫው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ዙርያ ሚስጥራዊ ስብሰባዎችን በማካሄድ ላይ እንደሚገኙ መረጃው በመጠቆም ላይ ይገኛል፡፡በተከፋፈለው ሃሳባቸው መሰረትም በዚህ በድብቅ ሲካሄድ በሰነበተው ሚስጥራዊ ስብሰባቸው ላይ መረጃው ስማቸውን ለመጥቀስ ባይደፍርም አንድ የህወሃት ከፍተኛ አመራር እንዲህ ሲሉ ተደምጠዋል በማለት ይሄንን ልኮልናል‹‹‹‹እኛ ኮ በመጀመርያ ማወቅና መረዳት ያለብን መለስም ራሱ በተደጋጋሚ ሲናገር የነበረው ጉዳይ..የመተካካት ሂደቱ እኛ ከርቀትና ከቅርብ ልንመራቸው ወይም መንገዱን ልናሳያቸው በምንችልና ኢህአዴግ በሚያስቀምጥላቸው ፖለቲካዊ መስመር ራሳቸውንና ድርጅቱን ይዘው መጓዝ በሚችሉ አዲስና ህዝቡ ባልሰለቻቸው አባላት ነው መካሄድ ያለበት….ያም ሆኖ ግን ህዝቡ በሂደት በነዚህ አዲስና ተተኪ ባለስልጣናት ያለማመን አዝማሚያና ሁኔታ ካሳየ ወይም የግለሰቡ ብቃትና የአመራር ችሎታ ማነስ የሚፈጠርበት አጋጣሚ ካለ ይህ ትልቅ አደጋ ነው፡፡በመሆኑም ባፋጣኝ ያንን አካል ከዛ ቦታ በማንሳት በሌላ አነጋገር ከስልጣን በማስወገድ የህዝቡን አመኔታና ዋስትና በቦታው ላይ ማስገኘት የሚችል ፖለቲካዊ ብቃትና ድርጅታዊ አቋም ባለው አባል የመተካካት ሂደቱን ማረም ይገባል..›››ይህ የማይሆን ከሆነ የኢህአዴግን የወደፊት እጣ ፋንታ አደጋ ላይ ከመጣልም አልፈን ትልቅ ክህደትን በድርጅቱ ላይ እየፈፀምን ነው፡፡ህዝቡ አሁን በስልጣን ላይ ባለው መንግስታው መዋቅር ውስጥ በሚገኙ አንዳንድ ባለስልጣናት ላይ ፈፅሞ እምነት የለውም ከነዛም መካከል ጠቅላይ ሚሊስትሩ አንዱ ናቸው በመሆኑም የህዝቡን ድጋፍና እምነት መልሶ ለማግኘት በህዝቡ ዘንድ ተወዳጅነትና ተሰሚነት ያላቸውን ነባር ታጋዮች ወደ ስልጣን ቁንጮው ለማምጣት መሞከር ነው፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ለህዝባዊ ንግግርና ሚዲያዎች በቀረቡ ቁጥር ስጋት የሚውጣቸው አባላት እየበዙ መምጣታቸው ራሱ የድርጅቱ ውስጣዊ አመራርም ጭምር መለስን የመሰለ አቅጣጫ ጠቁዋሚ መሪን ካጣ በኋላ የመለስን ሌጋሲ አስቀጥላለሁ በሚሉት ጠቅላይ ሚኒስቴር ሃይለማርያም ደሳለኝ የመምራትና ፖለቲካዊ አቅጣጫን የመቀየስ ብቃት ላይ ያላቸው ስጋት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል፡፡ይለናል መረጃው

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s