ባልተገኘበት እና ባልተካሄደ ጦርነት ተሸንፈሃል ተብሎ የተወሰነበት የአማራ ነገድ እና ኢትዮጵያዊነት – አበበ ተድላ

ባልተገኘበት እና ባልተካሄደ ጦርነት ተሸንፈሃል ተብሎ የተወሰነበት የአማራ ነገድ እና ኢትዮጵያዊነት – አበበ ተድላ

Share7  1503  2

Share2Amharaእንደምናውቀው ትህነግ (ወያኔ) ትግራይ የተባለውን ክፍለሃገር ከተቆጣጠረ በኃላ፤በተለይ አማራውን መስዋእትነት አስከፍሎ፤ ወደሌላ የኢትዮጵያ ክፍለሃገሮች ተሻግራ፤ ደርግን ከ 25 አመት በፊት ገደማ ማሸነፏ ይታወሳል። እውነቱ፤ ደርግ ማለት ትግሬን ጨምሮ የተለያዩ የኢትዮጵያ ነገዶች የተሳተፉበት ሰው በላ አምባገነን ወታደሮች መንግስት ነበረ። ነገር ግን፤በምን ስሌት እንደሆነ ባይታወቅም፤ ደርግን ሲላቸው የአማራ መንግስት በማለት አማራን አሸንፍን ሲሉ ይሰማል፤ እንዲያ ሲላቸው ደግሞ አንድ ትውልድን ያጠፋ የኢትዮጵያ ጠላትን ደርግን ስላሸነፉ ብቻ፤ ኢትዮጵያዊነትን አሸነፍን ይላሉ። እስከምናውቀው፤ ደርግ የአማራን ትውልድ፤ አድሃሪ እና ሌላ ሌላ ስም እየሰጠ ከጨረሱት መካከል ነው፤ምንም እንኳን የትህነግን ያህል አማራን ባያጠፋም። ጎንደር እኮ እንዲህ ነው ያለው ለደርግ ባለስልጣን፦

መላኩ ተፈራ የእግዜር ታናሽ ወንድም፤

ያሁኑን ማርልኝ ሁለተኛ አልወልድም።

ታዲያ እንዴት ነው ደርግ የአማራ መንግስት ነበር የሚባለው?

Amhara yበከተማዎችም ደርግ ከማንም በላይ አማራውን ነው የጨረሰው። መሪው መንግስቱም ቢሆን በአባቱ ኦሮሞ ነው። ይሄ ሁሉ እውነት ሆኖ ሳለ፤ ደርግ አማራን እንደሚወክል አድርገው፤ ደርግን ከአማራ ጋር ሆነው ካሸነፉ በኃላ፤ አማራን እንዳሸነፉት አድርገው፤ ስንት የስድብ ቃላት እና ጥቃት አማራው ላይ ሲወርድ አይተናል። ችግሩ፤ አማራው ሳይደራጅ ስለሆነ ከትህነግ ጋር ሆኖ ደርግን ለመጣል ደሙን ያፈሰሰው፤ ውጤቱ መገደል እና ምንም እንዳላደረገ መሰደብ ነው የሆነው። ይሄ የአማራው ሳይደራጅ ህይወቱን መስጠቱ ጥፋት መሆኑን ነው የሚያሳየው እንጂ፤ እነታምራት ላይኔ ደርግን ለመጣል ስንት የአማራን ልጅ ደም እንዳስፈሰሱ ይታወቃል።

ይሄ ብቻ አይደለም። አንዳንዴም የደርግን መሸነፍ የኢትዮጵያዊነት መሸነፍ አድርገው ይቆጥራሉ ትህነጎች እና አጋሮቻቸው። ልብ በሉ ደርግ አንድ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያሰባሰበ አምባገነን መንግስት ቢሆንም፤ ሌሎች ደርግን የሚቃወሙ ነገር ግን በኢትዮጵያዊነት የሚያምኑ በርካታ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ነበሩ አሁንም አሉ። ትህነግ (ወያኔ) በምእራባዊያን እርዳታ በጦርነት ያሸነፈችው፤ስልጣን ላይ የነበረውን ደርግን ብቻ ሆኖ ሳለ፤ልክ ኢትዮጵያዊነትን እንዳሸነፉ አድርገው ነው የሚደሰኩሩት። ለዚህም ፕሮፓጋንዳ ተባባሪዎቻቸው ደሞ እነ ኦነግና ሌሎች ነፃ አውጪ ግንባር ነን ተብዬዎች ናቸው። የረሱት፤ከኢትዮጵያዊነት ሃሳብ አራማጆች መካከል ተሳስቶ ኢትዮጵያን ወደጥፋት የገፋውን የወታደሮች ስብስብ ደርግን አሸነፉ ማለት፤ ኢትዮጵያዊነትን አሸነፉ ማለት፤ እንዳልሆነ አለመገንዘባቸው ነው።

ይሄንን ከላይ ደርግን ስላሸነፉ ብቻ አማራን እና ኢትዮጵያዊነትን እንዳሸነፉ ያስባሉ ያልኩበት ምክንያት መረዳት ከፈለጋቹ፤ ይሄ አሁን ህገመንግስት ተብዬውን ህገ አራዊት ሲያፀድቁ የተገኙት ነፃ አውጪ ግንባር ተብዬዎች ብቻ እና አማራን ሳይጨምር በሺ የሚቆጠር አባላት ያላቸው ትንንሽ ሌሎች ብሄሮች ተወካዮችን ጨምሮ ሲሆን፤ በዚህ ኢትዮጵያ ላይ “ህገ መንግስት” በሚል ሽፋን የተላለፈው “የሞት ውሳኔ” ስብሰባ ላይ አንድም አማራ እና አንድም በኢትዮጵያዊነት አምናለው የሚል ድርጅት እንዳላሳተፉ ልብ ማለት ነው። አንድ ለእናቱ ፕ/ር አስራት ወልደየስ በዛ የኢትዮጵያ የጥፋት ስብሰባ ላይ ተጋብዘው ነበር። እሳቸው ይሄ ሸፍጥ ገብቷቸው መቃወማቸውን እናውቃለን። ነገር ግን ብዙ አጋር ባለማግኘታቸው ህይወታቸውን አሳጣቸው ነፍስ ይማር ብለናል። ይህ የሚያሳየው ምንም እንኳን ትህነጎች ደርግን ቢሆንም ያሸነፉት፤ አማራ ስላልተደራጀና ስላልተናገረ ብቻ አሸንፈንዋል ቀብረንዋል እንዳይነሳ አድርገን አከርካሪውን ሰብረንዋል በማለት በሃገሪቱ በተደረጉ በማንኛውም ውሳኔዎች ላይ እንዳይገኝ አደረጉት። አማራን ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት የሚያምኑትን ድርጅቶችን ጭምር ኢትዮጵያዊነትን አሸንፈናል ስላሉ እንዳይገኙ አደረጉ የነሱ አሽከር በወቅቱ ኢህዴን የሚባለውን ካልጠራቹ በስተቀር። ግን መቼ ነው አማራውን ጦርነት ገጥመው ያሸነፉት? አማራው ኢትዮጵያዊነት በሚለው ስሜት የበለጠ ስለሚያምን (ምናልባት የመንግስት ቓንቓ አማርኛ መሆኑ ጠቅሞታል ካላላቹ በስተቀር አማራ ከኢትዮጵያዊነት ከሌሎች የተለየ ምንም የተጠቀመው ነገር ባይኖርም) አማራነቱን የተለየ ቦታ ሳይሰጥ በአማራነቱ ስላልተደራጀ እና ራሱን ለማዳን ሳይደራጅ በመቅረቱ ሳይዋጉት አሸነፍነው ብለው ትህነጎች ደመደሙ። ይሄ አማራውን አንገቱን ለማስደፋት ሆን ተብሎ የሚደረግ የስነ አእምሮ ጦርነት እንደሆነ እንዳትዘነጉ። ደርግ፤ ከሁሉም ኢትዮጵያዊ የተውጣጣ ትግሬንም ጭምር የሚያካትት ሆኖ ሳለ፤ እንዲሁም ደርግ ራሱ ዋና አማራን ያጠፋ ሆኖ ሳለ (የትህነግን ያህል የከፋ ባይሆንም)፤ ደርግን ስላሸነፉ ብቻ አማራን አሸነፍነው ማለት፤ ምንም ሚዛን የማይደፋ ሃሳብ ነው። ነገር ግን እንዲህ የሚሉት እውነቱ ጠፍቷቸው ሳይሆን፤ አማራ አሁንም በአማራነት ስላልተደራጀ፤ ሳይነቃ ሆን ተብሎ አማራን አንገቱን ለማስደፋት የሚደረግ ተንኮል ነው።

ደርግን ማሸነፍ በራሱ ብቻ ኢትዮጵያዊነትን ማሸነፍ እንዳልሆነ ትህነጎች መረዳት የሚችሉት በተከታታይ በኢትዮጵያዊነት በሚያምኑ ወገኖች አሁንም ድረስ በሚነሳባቸው አመፆች ነው። ለዚህም ይመስለኛል 1997 ኢትዮጵያዊነት ሞቷል ከዚህ በኃላ ህዝቡ እኛ ባሰመርንለት አፓርታይድ ክልል ብቻ ነው የሚያስበው ብለው የልብ ልብ ተሰምቷቸው ምርጫ ገብተው ኩም ሲደረጉ፤ አሻፈረኝ ብለው ስልጣን አንለቅም ብለው የስንት ደሃ ንፁህ ደም አፍስሰው እስካሁን ስልጣን ላይ ቆዩ። አሁንም ድረስ በኢትዮጵያዊነት የሚያስቡትን እነ እስክንድር ነጋ፤ እነ አንዱአለም አራጌ ወዘተ ላይ ከሌሎቹ የብሄርተኛ ድርጅቶች ተቃዋሚዎች በላይ የከፋ ቅጣት እንዳስተላለፉባቸው አይተናል፤ አማራነታቸው የበለጠ ቅጣታቸውንም መጨመሩ እንዳለ ሆኖ።

የሚያሳዝነው ግን፤ አሁንም ኢትዮጵያዊ ነን ብለው የተደራጁት፤ የአማራን በደል፤ ያውም አማራን ነው የምትወክሉ እየተባሉ እየተብጠለጠሉ ጭምር፤ ገሸሽ ማድረጋቸው ነው። ግን አማራው ራሱን ነው እንጂ ማዳን ያለበት ሌሎች ተደራጅተው እንዲያድኑት ሊጠብቅ አይገባም። እያደረገውም ነው መደራጀቱ ተጀምርዋል፤ይቀጥላል። የበፊቱ ይቅርና አሁን ስላለው እስቲ ላውራ። እስቲ የትኛው በአንድነት ስም የተደራጀ የፖለቲካ ድርጅት ወይንም ሚዲያዎቻቸው ናቸው አማራን ከትግሬ ጋር አብሮ ኦሮሞን እና ሌላውን ኢትዮጵያዊ እየበደለ ነው ብለው ቢቢሲ እና አውሮፓ ህብረት ዜና እና መግለጫ ሲያወጡ፤ ድምፁን ከፍ አድርጎ ተዉ አማራ ተበዳይ ሆኖ ሳለ፤ የዘር ማጥፋት እየደረሰበት ሳለ ፤መልሳቹ በዳይ አትበሉት ያለው። ቢቢሲም፤ አውሮፓ ህብረትም ትህነግን ማውገዛቸው እሰየው የሚያሰኝ ነው። ነገር ግን አማራን ያለሃጢያቱ መወንጀላቸው የሚያሳዝንም ፤የሚያስጠይቅም ነው። ሲጀመር በብሄር ፖለቲካ አናምንም የምትሉ ለትህነግ ጥፋት ትግሬ ሁሉ መጠየቅ የለበትም ትላላቹ ብዬ ነበረ እኔም አምናለው ለትህነግ ጥፋት ሁሉም ትግሬ መጠየቅ የለበትም፤ ምንም እንኳን ከጥቂት ትግሬዎች በስተቀር፤ ትህነግን እና ትግሬ አንድ አድርጋቹ አትዩ ሲሉ ባይሰሙም። ይሄ አልበቃ ብሎ ምንም አማራ ስልጣን ላይ ሳይኖር (አሻንጉሊቶቹ ብአዴን ዋና ዋና መሪዎች እንኳን አማራ እንዳልሆኑ እናውቃለን)፤ አማራ ተበዳይ ሆኖ መድረሻ አጥቶ እየተንከራተተ አብሮ ከትግሬ ጋር ሲወነጀል ዝም ያሉ በተይ የአንድነት ሃይል ነን የሚሉ ብዙ አስተዛዝቦናል። እነ ኢሳትም ያቺን አማራን ያለሃጢያቱ ከትህነግ (ትግሬ) ጋር የምትወነጅለውን አረፍተ ነገር ያላነበቡ ይመስል ሌላውን የትህነግን መወገዝ ብቻ አስተጋብተው ዝም ማለታቸውም ውስጣችንን አሳዝንዋል።

የሚያሳዝነው አማራው ባልተገኘበት ውጊያ ተሸንፈሃል ተብሎ፤ በሌለበት የተከለለውን የአፓርታይድ አከላለል፤ በብሄር የተደራጁትም ሆኑ በኢትዮጵያዊነት የተደራጁት ፤ካልተቀበልክ ከአማራ ጋር አንደራደርም ይሉታል፤ አልፎ ተርፎም የድሮ ስርአት ናፋቂ ይሉታል፤ አማራው ከድሮ ስርአት የተጠቀመ ይመስል። እንግዲህ ከዚህ በላይ ምን ሞት አለ? አማራው ሳትሞት ሞተሃል መባሉ አልበቃ ብሎ እና ሁሉም የአፓርታይዱን ድንበር ለማስመር ድርሻውን ወስዶ የተረፈውን የአማራ ተብሎ የተሰጠው አልበቃ ብሎ፤ ኧረ አለው አልሞትኩም ቢልም፤ የለም ሞተሃል ብለናል ሞተሃል፤ እና በቃ የተሰጠህን የመቃብር ቦታ ብቻ ተቀበል፤ ከመባል በላይ ምን ሞት አለ! ደስ የሚለው አማራው እየነቃ ነው። እንዲህ ሸፍጥ ያቀዱለት ካሁን በኃላ በፈለጉት አይነዱትም። በአማራ ደም የምትሰራ ኢትዮጵያም ይሁን እነሱ የሚያስቡት ትንንሽ ሃገሮች አይኖሩም። ወይ አብረን በሰላም እንኖራለን ወይ ስንጠፋፋ እንኖራለን!

 

ኢትዮጵያዊነትም  ይኖራል ይለመልማል ነገር ግን ይቺ በአማራ ደም ሁሌ እንደአዲስ የምትሰራውን ኢትዮጵያን  ለመስራት የሚደረገው ጥረት የትም አያደርስም። አማራንም ጨምሮ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የምትሆን አገር እንዲኖረን እንስራ እንጂ ያለ አማራ ወይንም ያለ ኦሮሞ ወይንም ያለ ትግሬ ወይንም ያለ ሌላ ነገድ ኢትዮጵያ በ2 እግሮቿ አትቆምም።

በነገድ ፖለቲካ የሚያምኑትም (ምሳሌ ትህነግ፤ኦነግ/ኦህዴድ፤ኦብነግ ወዘተ)አማራውን ጠላቴ ብለው ሃገር አሳጥተው ለማጥፋት የሚያደርጉትን ከቀጠሉ፤ እንዲሁም በአንድነት ስም ያሉትም አማራውን አብሮ ከሌላው ጋር ተባብረው ለማጥፋት እና አንገቱን ለማስጎንበስ የሚያደርጉትን ጥረት ካላቆሙ አማራው ራሱን ለማዳን ይገደዳል። ይሄ ደሞ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት የሚያመራ እንደሆነ እናምናለን ፤ግን አማራው ብቻውን ከሚያልቅ አብሮ ቢያልቅ ይሻለዋል። አማራው ደሞ ህይወትና ሞት ትርጉም ካጣለት ቆይትዋልና ሌላው ከሰላም ይልቅ በእርስ በእርስ ጦርነት ካመነ ምን እስካፍንጫቸው ቢታጠቁ ማን እንደሚጎዳ እናያለን።

ባልተሳተፍንበት ጦርነት አማራን አሸንፈንዋል አትበሉት ትህነግ እና ወዳጆቹ። አውሎንፋሱ እስኪያልፍ ብሎ አንገቱን እንደሰንበሌጥ ደፋ እንጂ ፤ነፋሱን አሳልፎ እንደገና አንገቱን ቀና ያደርጋል። አማራ አለ አልሞተም፤ አልተቀበረም ፤አከርካሪውም አልተመታም፤ አልተሸነፈም። ትህነግ ሆይ ያሸነፍሽው ደርግን ብቻ ነው ያውም የአማራ ደም ፈሶ ጭምር።

ኢትዮጵያዊነትም አልሞተም ምንም እንኳን በኢትዮጵያዊነት ስም ያሉ ቢያጭበረብሩበትም በአማራ ደም ኢትዮጵያን ሊያቆሙ ቢሞክሩም፤ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ እኩል የምታደርግ ኢትዮጵያዊነት አሁንም አልሞተችም አለች።

ፉከራ አይደለም ለውጥ እያየን ነው፤እውነት ነው አማራው ይነሳል፤ አልተሸነፈም፤አልሞተም፤ እንዳላቹት አልተቀበረም!!! ሁሉንም እኩል የምታደርግ ኢትዮጵያም አለች አልሞተችም!!!

የአማራ ልጅ ተደራጅቶ ራሱንም የአባት የእናቶቹን ሃገርም ያድናል!!!

አበበ ተድላ

ጥር 2008

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s