ወይ አቶ አባይ ፀሐዬ ሸመጠጠው | ሳይወዱ በግዳቸው የጠቆሙን 2 ነገሮች

አድ አዳማ

አቶ አባይ ፀሐዬ በኦሮሚያ ውስጥ የተነሳውን ሕዝባዊ ተቁዋሞ አስምልክቶ በተደጋጋሚ የድንፋታ ቃላት ሲናገሩ መቆየታቸው ከማንም የተሸሸገ አይደለም ይሁንና ዛሬ ዛሬ ደሞ የኦሮሞ ሕዝባዊ አመፅ ተጠናክሮ መቀጠሉ ስላሰጋው ለማስተባበል የት እንደሆነ በማይታወቅ ቦታ ቃለመጠይቅ ብጤ ለማድረግ ሞክሮ ነበር። ይህ ቃለ መጠቅ ከማስተባበል ይልቅ የተባሉት የትምህከት ቃላት በትክክል አውዲኦና ቪዲዎ የታከለበት ማረጋገጫ በራሱ በአቶ አባይ ፀሐዬ የተሰጠ መግለጫ ነው።በመጀመሪያ የጠያቂውን ሁኔታ ስንመለከት ዋ ከተሰጠህ ጥያቄ ትንሽ ዝንፍ ብትል ዋጋህን ታገኛለህ ስለተባለ ከመጠየቅ ይልቅ በመርበትበትና ሕዝባዊ አመፁን በመወንጀል ግዜውን የጨረሰ ይመስላል።ታዲያ የአቶ አባይ ፀሐዬ መልስ ልክ አፈትልኮ እንደወጣው ድምፅ በድንፋታ ታጅቦ ባይሆንም ቀዝቀዝ ባለ ድምፅ ማስተር ጥፋቱን ገና ከጥንስሱ የተቃወሙት የኦህዴድ አባላት ላይ ጣታቸውን ከመጠቆም ወደሗላ አላሉም።በቃለ መጠይቁ ላይ እንደሰማሁት ከሆነ አቶ አባይ ፀሐዬ አፈትልኮ የወጣው ድምፅ የኔ አይደለም ከማለት ይልቅ እኔ ጎንደር አልነበርኩም, እስቲ ቪዲዮውን ያምጡ , እስቲ የተናገርኩትን ሙሉ አረፍተ ነገር ያሰሙ እያሉ ግዜያቸውን ጨርሰውታል። አቶ አባይ አክሎም ህወሓት ወይም የፌደራል መንግስት በኦሮሚያ የተነሳው ሕዝባዊ ተቁዋሞ ውስጥ እጁን አላስገባም ብሎ ለማስተባበል ሞክራል። ለዚህ መልስ ይሆን ዘንድ ኦህዴድ ውስጥ ያሉትን ውድ የኦሮሞ ልጆችን ማስተር ጥፋቱን ስለተቃወሙ ብቻ ከኦህዴድ ባለስልጣናት ይልቅ የህወሓትና የፌደራል መንግስቱ ቱባ ባለስልጣኖች አባይ ፀሐዬንና ጌታቸው ረዳ ነበሩ ሲደነፉባቸው የነበሩት። በተጨማሪም የኦሮሚያ ፖሊስ የሕዝቡ ጥያቄ አግባብና ተገቢ ነው ባለ ወቅት የኦሮሚያ ፖሊስን ትጥቅ አስፈትተው ኦሮሚያ ውስጥ ከፈተኛ  ጭፍጨፋ ያካሔዱት የአጋዚ ጦርና የፌደራል ፖሊስ ናቸው። ይህም ጭፍጨፋ ሲካሔድ  under direct command of TPLF መሆኑ ከማንም የተሸሸገ አይደለም። ታዲያ ከዚህ በላይ ጣልቃ ገብነት ከየት ይምጣ።

ዘንድሮ ይሁን አምና ወይም ካቻምና ጎንደር ሔጄ አንድም ስብሰባ ብቻዬንም ሆነ ከሌሎች ሰዎች ጋር  አላካሔድኩም  ሙሉ ቪዲዮዋን ከነምስሌ ከነንግሬ ያምጡዋት  ያለው የዚሕ የድምፅ ተቀርፆ መውጣት ስለተደጋገመበት ምናልባት ከቪዲዮ አቀራረጽ ማን ድምፁን ቀርፆ እንዳወጣው ማወቅ በቀላሉ ይቻላል ከሚል ግምት እንጂ ስለድምፁ የሱ መሆን ቅንጣት ታህል ጥርጣሬ እንደሌለ አባይ ፀሐዬም ሆነ መላው ሕዝብ በደንብ ያውቃል። እሱም አልካደም።

የአቶ አባይ ፀሐዬ ንግግር እኔን እንደገባኝ ከሆነ  ቢያንስ ሁለት ነገር ጠቆም አድርገውን አልፈዋል

1ኛ. ከሁከትና ግርግር ለመጠቀም ከሚያስቡ ብለው ካሉ በሗላ ጥቆማው ያነጣጠረው አንዳንድ የኦሮሚያ ልዩ ዞን አስተዳደሮችና አንዳንድ የአዲስ አበባ ሀብታሞች ብሎ ቀጠለና የኦሮሚያ ሀብታሞች አለ እዚጋ ልብ ማለት የሚያስፈልገው ሙሉ አዲስ አበባና ዙሪያዋን አፍነው በጉልበት ስለያዙት የህወሐት ቱጃሮች አንድም ነገር ያለው የለም ። ከዚህ አባባሉ የተረዳሁት ነገር ቢኖር ወያኔ ማስተር ጥፋቱን የተቃወሙትን የኦሮሚያ ልዩ ዞን  አስተዳደሮችና  የኦሮሚያ ሀብታሞች ላይ ልዩ የሆነ የማዋከብ ዘመቻ ለመጀመር እቅድ ውስጥ እንዳሉ  ነው። ለዚህም መረጃ የሚሆነው በቅርብ አፈትልኮ የወጣው የአባይ ፀሐዬ ድምፅ ውስጥ ለኦህዴድ ባለስልጣናት የተሰጣቸው ትእዛዝ ማስተር ጥፋቱን የተቃወሙትን የኦሮሚያ አስተዳደሮችን አባሩ የሚል ነው።

2ኛ. የኔንና የአንዳንድ የህወሓት ባለስልጣናት ወይም የህወሓት ስምን የሚያነሱበት ምክንያት አለና በትግራይ ሕዝብ ላይ የዘር ጥላቻ ለመቀስቀስ ነው ሲል መልሧል።  ከዚህ ደሞ የምንረዳው ልክ እንደ ልማዳቸው የትግራይን ሕዝብ እኛ ከሌለን ትጠፋለህ ስለዚህ ከኛ ጋር ሆነህ የኦሮሞን ሕዝብ ውጋ ብሎ  እራሱ የዘር ግጭትን እየቀሰቀሰ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ የሚያውቀው አንድ የፀዳ ሀቅ አለ ይኸውም ሁሉም የህወሓት አባል አባይ ፀሐዬን ጨምሮ ትግሬዎች ናቸው ነገር ግን ሁሉም ትግሬ በፍፁም የህወሓት አባል ነው ብሎ አያምንም በዚህም የተነሳ ከንፁሁ የትግራይ ህዝብ ጋር ወዳጅነት እንጂ ምንም አይነት ቅራኔ የለውም።

አቶ አባይ ፀሐዬ በንግግራቸው መሓል የኦሮሚያ ሕዝብ ማን እንደዘረፈው ማን እንደበደለው ያውቃል ብሏል እውነት ነው ድብን አድርጎ ቢያውቅማ ነው ያለው መንግስት ሳይሆን ዱርዬ ዘራፊ ነው ብሎ በአራቱም መዓዘን ለመቃውም አደባባይ የወጣው ። አንተ አባይ የምትባል ሰው የሚገባህ ከሆነ ሕዝቡ በአሁኑ ሰዓት የሚለው ያለው አንጡረ ሀብታችንን ስትዘርፉ በትግስት አለፍን, መሪዎቻችንን ለመምረጥ የሰጠነውን ድምፃችንን ስትዘርፉ ዝም አልን አሁን ግን የመኖር ህልውና በሆነው በመሬታችን ስለመጣቹ ከዚህ በሗላ ወያኔ አይመራንም ስለዚ ህወሓትና ጀሌዎቻቸው ስልጣን ልቀቁ ከእንግዲህ ለፋሺስቱ ህወሓት የሚንበረከክ አንድም የኦሮሞ ትውልድ አይኖርምነው ።

Meles and abay

አቶ አባይ ፀሐዬ ወላዋይና ከፍተኛ የመንሸራተት ባህሪ እንዳለበት እግዜር ነብሱን በሲዖል ያኑረውና ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ሳይቀር መስክሮለታል። እናም ዛሬ የተናገሩትን ነገር ከሽመጠጡን ነገ ደሞ ጭራሽ ማስተር ጥፋቱን ከተቃወሙት ስዎች መካከል ግባር ቀደሙ እኔ ንበርኩ ይሉን  ይሆናል! ማን ያውቃል?

ድል ለሕዝባችን!!!!!!

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s