ኮንሶ በተነሳው ተቃውሞ በርካታ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸው ተነገረ

Konso

የኮንሶ ህዝብ ራሱን ችሎ በዞን እንዲተዳደር ያቀረበው ጥያቄ ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ በርካታ ሰዎች ለእስር ከተዳረጉ በሁዋላ አሁንም አካባቢው በልዩ ሃይል ፖሊሶች እንደተከበበ መሆኑን ነዋሪዎች ከስፍራው ገልጸዋል። የልዩ ሃይል አባላት ከጥያቄው ጀርባ አርበኞች ግንቦት7ቶች አሉበት በማለት ቅስቀሳ ሲያደርጉ እንደነበር የገለጹት ነዋሪዎች፣ አሁን ደግሞ ” ጥያቄው የእኛ አይደለም” ብላችሁ ፈርሙ በማለት በግድ ለማስፈረም ሙከራ እያደረጉ ነው። የልዩ ሃይል አባላትና የወረዳው ሹሞች መግባባት አለመቻላቸውን፣ አስተዳዳሪዎቹ ጥያቄው የህዝብ ነው የሚል አቋም በማራመዳቸው አንዳንዶች ከሃላፊነት እንዲነሱ ተደርጓል።

የህዝቡን ጥያቄ አቅጣጫ ለማስለወጥ ሆን ብለው በማቀነባበር ቡርጂዎች ግጭት እንዲቀሰቀስ ለማድርግ የተሞከረ ቢሆንም፣ በሁለቱም ወገን የሚገኙ ነዋሪዎች ይህ ሆን ተብሎ ግጭት ለመፍጠር የተቀነባበረ ነው በማለት ወደ ግጭት አለመግባቱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከቡርጅና ከኮንሶ የሆኑ 2 ሰዎች መገደላቸውን፣ ግድያው የተፈጸመው ሆን ተብሎ ግጭት ለመቀስቀስ ታስቦ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል፤ ግድያውን የልዩ ሃይሎች እንዳቀነባበሩት ሲታወቅ ግን ህዝቡ ወደ ግጭት አለመግባቱን ነዋሪዎች አክለው ተናግረዋል።

የኮንሶ አገር ሽማግሌዎች ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያምን ለማነጋገር ወደ አዲስ አበባ መሄዳቸውና ለዛሬ ቀጠሮ ተይዞላቸው እንደነበር ቢታወቅም፣ ስለተሰጣቸው ምላሽ ይህን ዜና እስካቀናበርንበት ሰአት ድረስ ለማወቅ አልቻልም። በአካባቢው አሁንም ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉ ነው። አንዳንድ የመንግስት መስሪያቤቶችም አገልግሎት መስጠት አቁመዋል።

(ኢሳት ዜና)

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s