የአቶ ደብረጽዮንን ማስፈራሪያ ወደኋላ ያሉ የኦህዴድ ባለስልጣናት ከስልጣናቸው ሊነሱ ነው * ሙክታር ከድር ሊሰናበቱ ይችላሉ (ሪፖርታዥ)

ከጥቂት አመታት በፊት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር የኦህዴድ ባለስልጣናት ሲያስቸግሯቸው በፓርላማ ወጥተው “ባለስልጣናት ሃብታቸውን ማስመዝገብ አለባቸው” በሚል የጸረሙስና ክስ ሊመሰርቱ እንደሚችሉ ተናገሩ:: በወቅቱ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ አባዱላ ገመዳ ነበሩ:: አባዱላ በሙስና ልታሰር እችላለው በሚል መሸማቀቅ አዲስ አበባ ላይ በሙስና የሰሩትን ቭላ ቤት ለኢህ አዴግ ጽህፈት ቤት አስረከቡ::

File Photo

ሰሞኑን ታሪክ ራሷን ደግሞ የኦሮሞ ሕዝብ ተቃውሞ በመላው ኦሮሚያ ሲናኝ አመጹን ለማስቆም የኦህ ዴድ ባለስልጣናት ምንም ሥራ አልሰሩም በሚል ሕወሃቶች በክፍተኛ ግምገማ ውስጥ ወድቀው ስንብተዋል ይላሉ የዘ-ሐበሻ ምንጮች:: አመጹ ከተቀጣጠለ በኋላ በኦህ ዴድ አመራር ላይ እምነት ያጡት ሕወሓቶች ልዩ አስተዳደር አቋቁመው ኦሮሚያን እየመሯት ይገኛሉ::

ከሁለት ሳምንት በፊት እነዚሁኑ የኦህዴድ ባለስልጣናት ለማስፈራራት የሕወሃቱ ቁልፍ ሰውና በጠቅላይ ሚኒስተር ማዕረግ ኢኮኖሚውንም ወታደሩንም የሚያዘው አቶ ደብረጽዮን ከመልካም አስተዳደር እና ከሙስና ጋር በተያያዘ የሚታሰሩ ባለስልጣናት እንደሚኖሩ በመንግስት ሚድያዎች ወጥቶ ተናገረ:: እንደዘ-ሐበሻ የውስጥ አዋቂ ምንጮች ይህ የአቶ ደብረጽዮን መግለጫ በቀጥታ የኦህዴድ ባለስልጣናትን ለምምታት ታልሞ ነው::

የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደሚሉት በተለይ የ ኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙክታር ከድር ይህን የሕዝብ ቁጣ ለማብረድ የሰሩት ስራ ደካማ ነው እንደውም ከበስተጀርባው ይህን ሕዝባዊ ቁጣ ይደግፋሉ ወይም እንዲባባስ እየሰሩ ነው በሚል በሕወሓቶች ተወንጅለዋል:: ዛሬ ከጨፌ ኦሮሚያ ምክር ቤት ለዘ-ሐበሻ የመጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የአቶ ሙክታር በስልጣን የመቆየት ነገር ያከተመለት ይመስላል:: ከቀናት በፊት አቶ ሙክታር ሃይለማርያም እና ከደመቀ መኮንን በመሩት የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ አለመገኘታቸውን የሚናገሩት የዘ-ሐበሻ ምንጮች ይህም በቀጣይ ኢላማ እርሳቸው መሆናቸውን ያሳያል ይላሉ::

በጨፌ ኦሮሚያ እየተገመገሙ የሚገኙት አቶ ሙክታር ከስልጣናቸው ተንስቶ በምትካቸው ሌላ ይሾማል ቢባልም እስካሁን ይህ ይፋ አልሆነም::

ሆኖም ግን ከኦህዴድ አካባቢ ያሉ ምንጮቻችን እንደሚሉት አቶ ደብረጽዮን በሚዲያ ወጥተው ካስፈራሩ በኋላም የሕዝቡ ቁጣ በማየል ላይ እንጂ በመብረድ ላይ ባለመሆኑ በርካታ የቀበሌና የወረዳ ጨምሮ ትንሽም ትልቅም ስልጣን ያላቸው የኦህዴድ ባለስልጣናት ተለቃቅመው በመታሰር ላይ ይገኛሉ::

ሕወሃቶች መለስ ከዚህ በፊት “ኦህዴዶች ፈጣን ሎተሪዎች ናቸው… ከላይ ሲታዩ ኦህዴድ ሲፋቁ ኦነግ ናቸው” የሚለውን በማንሳት ስልጣናችን ሳይነቃነቅ አሻንጉሊት መሪ በማስቀመጥ ክልሉን በቁጥጥራችን ስር ማዋል አለብን በሚል ሙሉ ስራቸውን ኦሮሚያ እና ኦህዴድ ላይ ማድረጋቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አጋልጠዋል::

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s