የአባይ ግድብ ውሃ የመሙላቱ ሂደት ጥናቱ ሳያልቅ እንደማይካሄድ የግብጽ ባለስልጣናት ገለጹ

Nileriver-Dam

የአባይ ግድብ ግንባታ በታችኛው ተፋሰስ ሃገራት ላይ የሚያመጣውን ተፅዕኖ እንዲያጠኑ የተመረጡ ሁለት የፈረንሳይ ኩባንያዎች ስራቸውን እንስኪያጠናቅቁ ድረስ ግድቡን ውሃ የመሙላቱ ሂደት እንደማይካሄድ የግብጽ ባለስልጣናት ሰኞ ይፋ አደረጉ።

በተያዘው ወር ጥናታቸውን የሚጀምሩት ኩባንያዎችም በቀጣዮቹ ዘጠኝ ወራቶች ውስጥ ስራቸውን ያጠናቅቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ግብጽ አስታውቃለች።

የሃገሪቱ የመስኖ ሚኒስትር የሆኑት ሆሳም ሞግሃዚ ሁለቱ የፈረንሳይ ኩባንያዎች ስራቸውን ጀምረው እስከሚያጠናቅቁ ድረስ የአባይ ግድብን ውሃ የመሙላቱ ሂደት እንደማይካሄድ መግለጻቸውን ዘ-ካይሮ ፖልስት ጋዜጣ ሰኞ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ከሃገሪቱ ጋር የተደረሰ አዲስ ስምምነት የለም በማለት ቢያስተባብሉም የግብፅ ባለስልጣናት በቅርቡ በሱዳን መዲና ካርቱም በተካሄደው ስምምነት ይኸው አበይት ነጥብ መካተቱን ይፋ አድርገዋል።

ግድቡ የታችኛው የአባይ ተፋሰስ ሃገራት የሚያመጣውን ተፅዕኖ ለማጥናት የተመረጡ ሁለት የፈረንሳይ ኩባንያዎች ሙሉ ወጪያቸው በኢትዮጵያ ሱዳንና የግብፅ መንግስታት በኩል እንደሚሸፍን ሚኒስትር ሆሳም ሞግሃዚ ለሃገራቸው መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።

ይሁንና፣ ሶስቱ ሃገራት ለዘጠኝ ወራት ያህል ለሚካሄደው ጥናት ምን ያክል ገንዘብ እንደተመደበ ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

የሁለቱ የፈረንሳይ ኩባንያዎች የግድቡ ግንባታ በተለይ በግብፅና በሱዳን ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ተፅዕኖ ትኩረት በመስጠት ጥናታቸውን የሚያሄዱ ሲሆን የጥናታቸም ውጤት ይግባኝ የሌለው እንደሆነ ታውቋል።

ይሁንና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ግድቡ በሁለቱም ሃገራት ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ የለም በማለት የግድቡ ግንባታ እንደማይቋረጥ እና ውሃ መሙላቱም እንደሚቀጥል በመግለጽ ላይ ናቸው።

ግብፅ በበኩላ ግድቡን በውሃ የመሙላቱ ስራ የሚካሄደው ሁለቱ የፈረንሳይ ኩባንያዎች ጥናታቸውን ለሶስቱ ሃገራት ካስረከቡ በኋላ ነው በማለት በተደጋጋሚ በመግለጽ ላይ ናት።

በሁለቱ ሃገራት መካከል ለአራት አመታት ያህል ሲካሄድ የቆየው ድርድርም እስካሁን ድረስ መቋጫን ሳያገኝ ሰንብቷል።

ኢሳት (ጥር 23 ፥ 2008)

 

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s