የኢትዮጲያ ብሄራዊ ቋንቋ በኢህዴግ ዕይታ – ብሩህ ቦጋለ

LanguagePartners5

በየትኛው የአለም ሕዝብ ዙሪያ በአንድ ሕብረ መንግስት ወይም በአንድ መንግስት ሥር የሚኖሩ ብሐር ብሔረሠቦች በእምነት፣በጎሳ፣በቋንቋ የግድ አንድ አይነት ሆነው መገኘት አይጠበቅባቸው ሊሆኑም አይችሉም፡፡ለምን የሚባል ጥያቄም አይኖረውም በሁሉም አንድ አይነት ሆነው ቢገኙም እንኳ የትውልድ ሐረግ አመጣጣቸው ከተለያዩ የግንድ ሐረግ ከተለየ ቦታ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ ለአብነት ያክል በአንድ ሕብረ ብሔር ውስጥ አንድ አይነት ቋንቋ ተናጋሪ አምስት ሚሊዮን ብሔረሠቦች ቢኖሩ አምስቱም ሚሊዮን ሕዝቦች ጥንት ከአንድ አይነት ጎሳ፣ ከአንድ አይነት ቋንቋ ተናጋሪ፣ ወንዴና ሴቴ የመጡ ናቸው ብሎ ማመን ድንቁርና ነው ምክንያቱም የሕብረተሠብ ዕድገት አመጣጥን ሥርዓት ያልተከተለ ኢሳይንሳዊ ይሆናልና፡፡

እዚህ ላይ ስለሕብረተሠብ ታሪክ አመጣጥ ለማስረዳት ሳይሆን አካሄዴ ስለብሔራዊ ቋንቋ  አንድነት ጠቀሜታ የታዬኝን አስተያየት ለማምልከት እንጂ፡፡ ምንም እንኳን ጥንት መንግስት አልባ በነበረበት የሕብረተሠብ ስብጥር አኗኗር ወክት የአናሳዎች ጎሳዎች ቋንቋ በአብላጫዎቹ ቋንቋዎች  እየተዋጡ የአንዱ ጎሳ ቋንቋ ከአንደኛው እየተወራረሰ በሐደ ቁጥር የባሕል ፣ የጋብቻ ፣ የሥነ ተዋልዶ ስብጥር በዚያው ልክ እያሠፋ መጥቶ አንድ አይነት ቋንቋ ለመናገር መንስኤ ከመሆን ውጭ እያንዳንዱ ጎሳ በያንዳንዱ ጎጥ ውስጥ ለያንዳንዱ ቋንቋ  ከመሬት  የፈለቀለት ነገር አይደለም፡፡ ይህ ማለት በህብረተሠብ ስብጥር አኗኗር አንደኛው ከሌላኛው ቋንቋ  ተወራርሶ የመጣ የጋራ ቋንቋ  አንጂ እንደ ኮምፒይተር አንድ ግለሠብ የፈጠረው ወይም ሌላይኛው በፍልስፍና ያገኘው የፈጠራ ውጤት አለመሆኑ መታወቅ ይኖርበታል፡፡

የቋንቋ ጥቅሙ ለመግባቢያ ብቻ ሆኖ ለማህበራዊ ግንኙነትም ፋይዳ አለው ይህን አካሄድ ገዥ መደቦች አይወዱትም ይህ የጎሳ ስብጥር ሕብረት አኗኗር ግንኙነት የተቋረጠው መንግስት የሚባለው ሥርዓት እምነትን  መዕከል አድርጎ በያለበት መሥፋት ከጀመረ በኃላ በየጎጥ ክልል ውስጥ የሚኖር ሕብረተሠብ በጎጥ ወይም በከል የጎሳ አለቃ ቁጥጥር ሥር ስለወደቀ የሕብረተሠብ ስብጥር ማህበራዊ ግንኙነት ተገደቦ የየጎጡ ወይም ክልል አለቆች ገዥዎች እየበዘ በሄዱ ቁጥር አንዱ ጎሳ ከንድ ጎሳ እያጋጩ የጦር ጅብደኝነት  አንዱ በአንዱ ጎሳ ላይ ጥላቻ እየፈጠሩ ቋንቋን መሠረት ያደረገ አገዛዝ ቦታውን ተረክቦ የቋንቋ መስፋፋት ለገዥ መደቦች መበራከት አስተዋፅአ አድረጎል በአንጻሩም  በቋንቋ መሰፋፋት ምክንያት  አንዱ ጎሳ በአንደኛው  ቋንቋ ተናጋሪ ላይ ያጎሪጥ በጥላቻ የመታየት ችግር ሲፈጥር ሲያናቁር እንደኖረ የሚታወቅ የታሪክ ሐቅ ነው፡፡

ይሁን እንጂ አንዱ ቋንቋ ከአንዱ የሚበልጥበት ወይም የሚያንስበት መገለጫ የለውም ሁሉም ቋንቋ  በራሱ የራሱ ምሳሌ፤ተረት ፣ቅኔ፣ ተረብ፣ ውስጠ ወይራ ቀልድና አዝናኝ ጫወታዎች አሉት አንዱም ብሔረሰብ የሌላውን ቋንቋ ያከብራል፤ያፈቅራል፡፡አንዱ ቀንቃ ከአንዱ የሚናቅ  እንዲናቅ ሌላው ቃንቃ እንዲከበር የሚያደርጉት ማንም ሆነ ማን ምን የገዥ መደቦች ናቸው አንጂ ሕብረተሰቡ እንዳይደለ እንዳልነበረም ይበልጥ የሚያውቁት ፖሊቲከኞችና የፖለቲካ አቀንቃኞች እንደሆኑም ድሮም እንደነበሩ ሠፊው ሕዝብ በውል ያውቃቸዋል በአደባባይ ላይ ለይስሙላ ሲለፈፋም ንቀቱም ጥላቻውም ከራሳቸው የሚመነጭ ለፖለቲካ መሰሪያነት ለያይተው ለማየት የሚያደርጉት የውል ጥበብ ውጠት ድምር ነው፡፡ማናቸውም ብሄርብሄረሰቦች በአፍ መፍቻ ቃንቃቸው መማር መዳኘት መመራመር ባህላቸውንና ቋንቋቸውን መንከባከብ ዕና ማሳደግ፤ለጋራ መገናኛ ቋንቋ ማደግና መጎልበት ታላቅ የማነይናቅ አስተዋፅዖ እንዳለው ሰፊው ሕዝብ ያምንበታል፡፡ምክንያቱም የያንዳንዱ ብሔረሰብ በዐፍ መፍቻ ቋንቋው  ተምሮ መመራመር መታርጎም ከቻለ ለጋራ መገናኛ ቋንቋ መግባባት መንገዱን ቀላል አመቺ ስለሚያደርገው በእጅጉ ሠፊው ብዘኃኑ ሕዝብ ይደግፈዋል ቢቻለውም በተጨማሪ ቋንቋውን አውቆ መናገር ቢችል ደስታው ነው፡፡ ይህ ሐቅ መሆኑን ብዙኃኑ ሕዝብ እርስ

በርዕሱ ይታወቃል ማናቸውም የፖለቲካ ክፍል ግን ለያይተህ ግዛ መርህ ሚስጢር በውስጥ አጀንዳ ይዞ በአደባባይ ሰፊው ህዝብ አንዱ የአንዱን ቋንቋ እንደሚንቅ አስመስሎ በተዘዋዋሪ የአባዬን ወደ እማዬ እንዲሉ ቋንቋን ተንቆ ነበር ብሎ የሚኮንነው ማንን ነው?ይህ ሁሉ ማናበብ ሰፊ የፖለቲካ ሽፋን ምስጋና ለማግኘት እንደ መሳሪያነት መጠቀሚያ ማታለያ ከማድረግ ያለፈ ልባዊ እውነታነቱ ትዝብትን ያጭራል፡፡ አናግሮ አናጋሪ ይሉኋችዋል ይህ ነው፡፡ አጥብቆ ጠያቂ የእናቱን ሞት ይረዳል እንዲሉ የሰሜን ኢትዮጲያችን ተጎራባች የሆኑትን የዋሁን ገበሬ ከነቋንቋው ለብዙ ዓመታት በጥላቻ አይን የሚያየና ቋንቋውን በጆሮው መስማት የጠላና ደንቅ የነበረውን የቅርብ ጊዜ ትዝታ ህዝብ አካል ማን ነበር? ከዚያህም አልፎ ከርሱ ቋንቋ በስተቀር የሌሎችን ቋንቋ ታሪክ የለሽ አድርጎ በንቀት ሲመለከት በአደባባይ ይታይ የነበረው የየትኛው ህብረተሰብ የፖለቲከ አቀንቃኝ እንደነበረ እራሱ አያውቀ በድፍረት ለህዝብ ቋንቋ ማስከበር ነው፡ የቆምኩት ማለት ከንቀት በላይ ንቀት መሆኑ ነው፡፡ ዳሩ ምን ያድርግ ፖለቲከኛ ማለት ለጥቅሙ ማሰከበሪ ስልጣን የቆመ የዛሬ ጊዜሃዊ ምቾቱን እንጂ ያለፈው በወገኞቹ ላይ የነበረውን የታሪክ አሻራ ጥላቻ ደንታ አይሰጠውም፡ሆዱ ከሞላ ከጠላቶቹ ጎን ያለ ይሉኝታ ይሰለፋልና ዛሬ ከዚህ ኢህሀዲግ ወያኔ ጋር የተሰለፉት የሰሜን ወያኔ አጎራባች ክልል ህዝቦች የፖለቲካ አጋሮች እና ካድሬዎች ከዚህ በላይ የተፃፈውን እውነተኛ ታሪክ ከኛ ይበልጥ ያውቁታል ዳሩ ሆዱን የወደደ ማእረጉን ይጠላል፡እንዲሉ ሆነና ነው እንጂ፡፡

ከዚህ በላይ የተሰነዘሩትን አስተያየቶች እውነታነት ለታዛቢዎች ትተን ወደ ዋናው የቋንቋ አንድነት ጠቀሜታ እንመለስ፡ቋንቋ በመንገድ ይመሰላል መንገድ ሁሉንም አገናኝ ነው፡መንገድ ከሌለ የሁልም ግንኑኝነት ይቋረጣል ታዲያ ቋንቋን ከመንገድ ጋር ካመሳሰልን እያንዳዱ ብሄረሰብ በአፍ መፍቻ ቋንቋው መማር እና ቋንቋውን ማዳበር እንደተጠበቀ ሆኖ እነዚህ ብዙሃን ህብረተሰቦች በአንድ ህብረ ብሄር ውስጥ በሚኖሩበት ጊዜ አንድ የጋራ መገናኛ ቋንቋ መኖር ግድ ይላል፡፡ ስለዚህ የጋራ ቋንቋውን የነዚህ ሁሉ መገናኛ ስለሚሆን እንደ ራሳቸው ቋንቋ ተደርጎ መታየት በራሱ እንደመብት እና ግዴታ ሆኖ ብሄርብሄረሰቦች እንደራሳቸው ቋንቋ የማወቅ ግዴታ ሊኖረው ይገባል፡፡ ለምን መብትና ጥቅሙ የጋራ ነውና እትዮጲያ በአሁኑ የኢአዴግ መንግስት የጋራ ብሄራዊ ቋንቋ አልባ ሆና ትገኛለች፡፡ የፌደራላዊ ቋንቋ ተብሎ አይታሰብም፡፡ ይህ በራሱ የብሄር ብሄረሰቦች ግኙኝነት እንዳይኖራቸው ከፋፍሎ ለመግዛት አመቺ እየሆነላቸው ሄዶ ቀስ በቀስ የጋራ የሆነ ቋንቋ እየተመናመነ ሄዶ ጠባብ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኃላ እነዚያ ብልጣ ብልጦች የፈየዱትን ቋንቋ የራሳቸው እና በራሳቸው ካቢኔዎች ብቻ እንዲነገር ለማድረግና ሌሎቸ ብዙኋን የፌዴራል ቋንቋ ተናጋሪ ብሔርብሔረሰብም ተወላጆች ውስን ይሆኑና እነሱና መሰሎቻቸው ብቻ በቋሚነት እየተለዋወጡ ለመምራት አመቺ ሁኔታ ስለሚፈጥርላቸው ሆን ተብሎ በኢህዴግ የተንኮል ክፋፍለህ ግዛ ስልት ውጤት መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ በዚህ ዓይነት የሰፊውን ህዝብ መገናኛ መንገዱን ቀስ በቀስ ከዘጉት በኋላ ብዙሃኑ በየክልሎች ውስት ተወስኖ ሲቀር የፌዴራል ቋንቋ ባለቤት እራሳቸው እና መሰል አጋሮቻቸው ብቻ ሆነው ለለሌላው ብዙሃን አማራጭ እድል ይነፍገዋል ማለት ነው፡፡ ለዚህ ነው ይህ ስውር የተንኮል አካሄድ እንዳይነቃባቸው ቋንቋን መሰረት ያደረገ የፌዴራለዊ አወቃቀር የህዝብ መብት አስመስለው 24 ሰዓት ሙሉ የሚለፍፉት፡፡ ይህ ሲባል ፖለቲከኞች በይፋ በአደባባይ ከራሳቸው ቋንቋ በስተቀር አትማሩ፣ አትናገሩ ይላሉ ማለት አይደለም፡፡ እንዲህማ በይፋ ካሉ የእነሱ ሁለቱንም ቋንቋ አጣርቶ ማወቅ ላይ ህዝባዊ አሉታዊ ተፅህኖ ስለሚያሳድርባቸው በይፋ አያወግዙም ግን በየግሉ ቋንቋ መማርና መናገር ብሎም እስከ መጨረሻው መዝለቅ መብትና ግዴታው መሆኑን ሲያሰምሩበት በአንፃሩ ደግሞ የሌላውን የብዙሃኑን የመገናኛ ቋንቋ መማርና መናገር አለመፈለግ መብት አስመስለው እየለፈፉ የብሔራዊ ቋንቋ ሰፊው ህዝብ በስፋት እንዳያውቅ ተዘዋዋሪ፣ ቁሳዊና ሰብሃዊ አገልግሎት እንዲነካም ለማድረግ ብለው ኢትዮጲያ በተለምዶ የፌዴራላዊ ቋንቋ እንጂ ብሔራዊ ቋንቋ የላትም የሚሉት ወደፊትም እንዳይኖራት ለማድረግ ድብቅ አጀንዳቸው መሆኑን በገሃዱ ያሳያል፡፡

ይህ አካሄድ የፌዴራሉ ቋንቋ ባለቤትነት ተረክበው ለጥቂት ሹማምንት ካድሬ ውስን አካላት ብቻ ተገልጋይና በአማርጭነት ተጠቃሚዎች እየሆኑ የብዙሃኑን ከሀገር ሀገር የመዘዋወር እድል መብትና ጥቅሙን ይገድቡታል፡፡ የዚያን ጊዜ ነው የብሔር ብሔረሰቦች ቋንቋ ግኑኝነት እየላላ ሄዶ እድገትና ፍቅር ሆድና ጀርባ ሆኖ በክልል የሚወሰነው፡፡ ያን ጊዜ ነው እያንዳዱ ክልል በያንዳንዱ ገዢዎች እጅ የምትወድቀው፡፡ ያን ጊዜ ነው የመጨረሳው የብዙሃን መብትና ጥቅም በጎጥ የሚወስነው፡፡ ያን ጊዜ ነው የየክልል ገዢዎች በዲፕሎማሲ ግኙኝነት ከሀገር ሀገር ሲንደላቀቁ ብዙሃን በቋንቋ ተገድበው የሚረገጡት፡፡ ይህን መሰል አሳብ አድርባዮች ጥቂት ባለጥቅሞች ገና በተስፋ የሚጋዙ ጥቂት የወግ የፖለቲካ እቀንቃኞች አይቀበሉትም፡ብዙሃኑ ደግሞ በንቃት ህሊና ክህሎት አለመዳበር የተነሳ የፖለቲካ ድብቅ አጀንዳ ሚስጢር ማወቅ ይሳነዋል ይህን ለማስፈፀም አቅምም አንድነትም አይኖረውምና፡፡

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s