ማስጠንቀቂያ ለ24ተኛ ክፍለ ጦር የሠራዊት አባላት | ከ24ተኛ ክፍለ ጦር የዉስጥ አርበኞች የተላለፈ መልዕክት

militery

ይህ ማስጠንቀቂያ ቅሉ ለ24ተኛ ክፍለጦር ይሁን እንጂ በመላዉ ኢትዮጵያ ለሚገኘዉ የመከላከያ ሰራዊትም ጭምር ነዉ።

ጉዳዩ: የሐገርን እና የህዝብን አንድነት መከላከልን ይመለከታል>>

ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ በዚሁ በ24ተኛ ክፍለ ጦር መደበኛ ቅጥር ክልል እና ጠቅላይ ቀጠናዎች ቃኘዉና እግረኛ እንዲሁም ሜካናይዝዶች በሚገኙበት ስፍራ ሁሉ ከዉስጥ ሆነን ወረቀት ስንበትን እንደነበር ይታወቃል፡ ሆኖም የማስጠንቀቂያ መልእክታችንን አሻፈረን ባሉ አንዳንድ አመራሮችና ካድሬዎች እንዲሁም የግምገማ አባላትና መረጃ ሰራተኞች ላይ ለአመታት እርምጃ መዉሰዳችን የሚዘነጋ እንዳልሆነ ግልጽ መሆን የሚገባበት ወቅት ላይ ደርሰናል።

በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ሐገራችን እጅግ አደገኛና አጣብቂኝ ወቅት ላይ እንደምትገኝ ሁላችንም የምናዉቀዉ ሐቅ ነዉ በጎንደር በኩል ለሱዳን ሊሰጥ በተባለዉ መሬት ምክንያት እንቢኝ ለሐገሬ ባለዉ ጭቁኑ የአማራ ህዝብ ላይ የተኩስ ትእዛዝ እየሰጣችሁ ህዝብ የምታስጨርሱ የ24ተኛ ክፍለ ጦር አመራሮችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተለይም የትግራይ ተወላጅ የሆናችሁ በሙሉ ከእኩይ ተግባራችሁ እንድትቆጠቡ እያዘዝን በተጨማሪ በወልቃይት ጠገዴ ለትግራይ የመሰጠት ምክንያት በአማራዉ መሐበረሰብ ላይ እየተደረገ ያለዉን ወንጀል የመከላከያ ሰራዊቱ በመቃወም ሕዝብ ላይ የተወሰዱ የሚገኙ የግፍ እርምጃዎችና የሚወሰዱ አስከፊ ተግባራትን በእጥፉ እንዲከፍል ጥሪያችን እያስተላለፍን እኛ በ24ተኛ ክፍለ ጦር ዉስጥ የምንገኝ የህዝብ ልጆች ተመጣጣኝ ምላሽ ከመስጠት አንጻር የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እርስ በእርሱ ተደራጅቶ በትናንትናዉ እለት በሁለት የተለያዩ ስፍራዎች ላይ ወገኖቻችንን በግፍ በገደሉ አባላት ላይ እርምጃ ለመዉሰድ ተገደናል።

ዉድ የ24ተኛ ክፍለ ጦር አባላት እኛ ሁላችንም አንድ ሆነን አንድነት የሚሰማን ከሆነ የሐገራችን ዳር ድንበር በማስጠበቅ ለህዝባችን መቆም አለብን! ወታደር እንደመሆናችን መጠን ትእዝዝ የመቀበልና ተግባራዊ የማድረግ ህግ ሊያስረን ቢገባም ወደ ወንጀልና ወደ ግፍ ግን ተነድተን የምንሄድ ማሽኖች ወይም ሮቦት አይደለንም የምናመዛዝንበት አይምሮ አለንና ወደ ግፍ የሚልኩንን እና ወንጀለኞችን አሻፈረን እንበል።

ይህ ለመላዉ ኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጥሪ ይሁን!!

ከ24ተኛ ክፍለ ጦር ሰሜን እዝ የዉስጥ አርበኞች!!
በቃ!!

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s