ብአዴንና ህውሃት ፍጥጫ ውስጥ!

ብአዴንና ህውሃት ፍጥጫ ውስጥ!

አባይ ወልዱ የአማራ ክልልን አስተዳዳሪ ገዱ አንዳርጋቸውን “አንተ የአማራን ህዝብ የጦር መሳሪያ ያስታጠከው ሆነ ብለህ በትግራይ ላይ ጦርነት ለማወጅ ነው…” በማለት ተናግሮታል፡፡
12717340_850067088462939_8071042318987831889_nገዱ አንዳርጋቸውም በበኩሉ “እኔ ህዝቡ በሀብቱ ገዝቶ ከጥንት ጀምሮ ታጥቆት የቆየውን ጦር መሳሪያ ህጋዊ ፈቃድ በመስጠት አፀናሁለት እንጂ ልክ እንዳንተ ከመንግስት ግምጃ ቤት አውጥቼ በገፍ አላስታጠቁትም፡፡ በትግራይ ህዝብ ላይ ጦርነት አወጅክ ላልከኝም የትግራይን ህዝብ ሰብስበህ በወልቃይት ህዝብ ላይ
እርምጃ እንወስዳለን ብለህ በይፋ ጦርነት ያወጅከው አንተ ነህ፡፡” በማለት ለአባይ ወልዱ መልስ ሰጥቶታል፡፡ የጦር መሳሪያን በሚመለከት ደብረ ፂዮን ገ/ሚካኤል ገዱ
አንዳርጋቸው የአማራን ህዝብ እንዳስታጠቀ ወቀሳ ሰንዝሯል፡፡

ደብረ ፂዮን ስለ ወልቃይት ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ የሚከተለውን በማለት ቁልጭ ያለ አቋሙን አስቀምጧል፡፡ “የወልቃይት ጉዳይ ክልል አንድን እንጂ ማንንም አይመለከተውም፤ ውሳኔውም ሊሆን የሚችለው የክልል አንድ ብቻና ብቻ ነው፡፡”

ለዚህ የደብረ ፂዮን ንግግር ገዱ አንዳርጋቸው ሲመልስ “እኛ ሄደን ኑ አንላቸውም፤ ከመጡ ግን የማንቀበልበት ምንም ምክንያት የለም፤ ደግሞም ውሳኔ ማስቀመጥ ያለበት ራሱ የወልቃይት ህዝብ ነው፡፡” በመሆኑም በሁለቱ ክልሎች /በትግራይና አማራ/ አስተዳዳሪዎች ማለትም በአባይ ወልዱና ገዱ አንዳርጋቸው መካከል ስብሰባው ውስጥ የተካረረ ፍጥጫ ተከስቶ ነበር፡፡

 

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s