በትክል ድንጋይ የትምህርት ሃላፊዎች በተማሪዎች ተደበደቡ (ከአከባቢው የደረሰን መልዕክት እንደወረደ)

ቀደም ሲል ተነስቶ በነበረው የቅማንትን የማንነት ጥያቄ መሰረት በተነሳው ብጥብጥ የሰው ሂወትና ንብረት መጥፋቱ ይታወቃል ። ይህን ተከትሎም በብዙ ግጭቱ የተነሳባቸው ወረዳዎች ት/ ቤቶች ተዘግተው ቆይተዋል። አሁን ላይ ግጭቱ በርዱዋል በሚል ከጎንደር ት/ርት መምሪያ የተላኩ ባለስልጣናት ትክል ድንጋይ በሚገኝ አንድ ት /ቤት ተገኝተው ተማሪዎች ትምህርት በሚጀምሩበት ሁኔታ ሲወያዩ ተማሪዎች ከየት መጡ ሳይባል በድንገት ሰዎቹ ከተሰበሰቡበት ክፍል በመግባት ደብድበዋቸዋል።በጉዳቱም አናቱን በዱላ የተፈነከተ የመምሪያው ባለስልጣንይገኝበታል። የተማሪዎቹ ጥያቄም ከሁለት ወር በላይ ትምህርት አቋርጠን ሳለ ምንም ባልተማርንበት ሁኔታ በዚህ አመት መፈተን አንችልም የሚል ነው። የፌደራል ፓሊስ ክቅጥር ግቢው ውጭ የነበረ ሲሆን ክግጭቱ በሁዋላ ተጎጂዎቹ የባሰ ብጥብጥ ሊከሰት ይችላል በሚል ስጋት ጉዳታቸውን ዋጥ አድርገው ያለ ስምምነት ወደ ጎንደር ተመልሰዋል።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s