አምባሳደር ግርማ ግድያ ይቁም ለምን አላሉም ? – አርዓያ እትስፋማርያም

አምባሳደር ግርማ ብሩ በዋሺንገትን ዲሲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ናቸው።በኢሕአዴግ ዉስጥ ከፍተኛ ተሰሚነት ያላቸው ሲሆን፣ ከባድመ ጦርነት በኋላ በሕወሃት ዉስጥ መከፋፈል በነበረ ጊዜ አቶ ግርማ ከነ ዶር ነጋሶ ጊዳዳ የተለየ አቋም በመዉሰድ፣ የመለስ ቀኝ እጅ በመሆን ኦህዴድን ከመለስ ጎን ያሰለፉ ሰው ናቸው።

አቶ ግርማ ሰይፉ የኢሕአፓ አባል የነበሩ ሲሆን፣ በደርግ ታስረው በደረሰባቸው ድብደባ በፊታቸው በአንዱ በኩል እስከአሁን ድረስ ቆዳቸው ላይ መበረዝ ይታይባቸዋል። ቀይ ሽብር ካበቃና ደርግ የሚያጠፋዉን አጥፎቶ በመሃል አገር ነገሮችን ካረጋጋ በኋላ፣ አቶ ግርማ በደርግ ውስጥ መስራት ጀመሩ። ወያኔዎች አዲስ አበባ ሲገቡ አቶ ግርማ በመከላከያ ሚኒስቴር ዉስጥ ከፍተኛ ሃላፊነት የነበራቸው ሰው ነበሩ።  ትልቅ የፖለቲክ ጅምናሲትክ በመስራት፣ ኦሮሞ ነኝ ብለው ኦህዴድ/ኢሕአዴግ ተቀላቀሉ። በዲላ አካባቢ በመወዳደርም የፓርላማ ተወካይ ሆኖ። የንግድ ሚኒስቴርም ሆነው ለብዙ አመታት አገልግለዋል።

ጦማሪ አርዓያ ተስፋማሪያም ለአቶ ግርማ መልእክት አለው። እንዲህ ስሉ ጽፏል

================

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አቶ ግርማ ብሩ ተወልደው ያደጉት ደብረ ዘይት ነው። በደርግ ዘመን የኢህአፓ አባል ተብለው ይታሰራሉ። ወደ አየር ሀይል ግቢ ተወስደው ከተሰቃዩ በኋላ ከሌሎች ጋር ሊረሸኑ ቀን ይጠብቃሉ። በአጋጣሚ የማትሪክ ውጤት ይወጣና ቤተሰብ ይወስድላቸዋል።

የግቢው ጥበቃ አዛዥ ኮሎኔል የግርማን ውጤት ሲመለከቱ 7- A ነው። ኮ/ል ” ወደፊት ለአገር የሚጠቅም ጭንቅላት ስለሆነ መሞት የለበትም” ብለው  “ውለህ ሳታድር ይህን ከተማ ጥለህ ጥፋ። ከተገኘህ ግን እኔ ራሴ. ነው የምረሽንህ.” ብለው ለቀቋቸው። ሌሎች ተገደሉ፣ ግርማ ብሩ ተርፈው እነሆ በሕይወት አሉ። ከፍተኛ የኢሕአዴግ አመራር ናቸው። በዋዚንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ አምባሳደር።

አቶ ግርማ ብሩ መልእክት አለችን።

“አቶ ግርማ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ አርጩሜ የሚበዛባቸው የ9 አመት ታዳጊዎች ጭምር ጥይት እየጎረሱ ነው። እርስዎ ያለፉበትን ህይወት ወደ ኋላ አስታውሰው ” ግድያ ይቁም! ለምን ንፁሀን ይገደላሉ!?” ብለው መጠየቅ አይገባዎትም? ምን ይሉ ይሆን!?

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s