መብረቅ ሆኖ ወደቀ!!!

andargachew new picture

አርበኛ አንዳርጋቸው፤
ግፍ የማይመቸው፤
ልቡ እንዳሸመቀ፤
ወኔው እንደታመቀ፤
በክህደት ሴራ በድኑ የተሰረቀ፤
በባንዳዎች ዱላ በሞት እየሳቀ፤
የልቡንም ፅናት ቀድሞም ስላወቀ
በጡት ነካሽ እጆች፣
መብረቅ ሆኖ ወደቀ።
ወደቀ ሳያውቀው ሊፈ-ፀም ትንቢቱ፤
በሥም ተጠቅልሎ ያገኘው ካባቱ።
ጉድጓዶች ሊያስቆፍር በኢትዮጵያዊነቱ፤
ጠላቷን ሊያከስም ገባ ከምድሪቱ።
መርዝ ሆነ በእጃቸው፤
መብረቁ አንዳርጋቸው።
አንዳርጋቸው ፅጌ የለም-አለም ያለው፤
ይሁዳዊው የመን ዶላር ያቀለለው፤
ለጉጅሌው ቡድን በህቡህ የሸጠው፤
ዜግነቱን አውቆ እንደሸመጠጠው፤
የእግዜርን-ክንድ መምጪያ:-
ክደውታልና፤
ዛሬ አለ ብለው ላኩት ትናንትና።
ሞትን ግን ሲጠብቅ የገባ በእጃቸው፤
በታሪክ አይሞትም፣
መብረቁ አንዳርጋቸው።
እነዚህ እፉኝቶች በመንግሥት ሥም ያሉ፤
በመግደል በማፈን ዕድሜ የቀጠሉ፤
ልባቸው ጫካ ነው እንደደነቆረ፤
እሳት መስሎ ካመድ
ያኔ የተፈጠረ::
የእሳት ልጅ አመድ ነው፣
ይባላል ከጥንቱ፤
መብረቅ ግን ባለ-አመድ፣
አይደለም ዕውነቱ።
መብረቁ አንዳርጋቸው
በደም አንድ ሊያደርገን፤
በእሳት-ልጆች አመድ፣
መብረቁን ታደገን።
መብረቆች መች መጡ ገና ይታያሉ፤
እንዲህ በክፉ ቀን መብረቅ ነን እያሉ።
ያንዳርጋቸው መብረቅ በእልህ እያጫራቸው፤
በአንድነት አምርረው ነፃነት ይጥራቸው።
ይህን የሥጋ ትል፤
ሕዝብን የሚገድል፤
ቢጠፋ ባገሩ በቃችሁ የሚላቸው፤
መርዝም
መብረቅ ሆኖ፣
ወደቀ አንዳርጋቸው።
እናም
በየተራ እየመረዛቸው፤
መብረቆቹ በዝተው፤ባሉበት ፈጃቸው።
ሁሉም ወዮላቸው፤
መጥቷል አንዳርጋቸው።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s