ሙጋቤ ለአፍሪካ ህብረት 300 ላሞችን ለገሱ – ዳዊት ሰሎሞን

Mugabe

የዚምቧቡዌው ፕሬዘዳንት ሮበርት ሙጋቤ የአፍሪካ ህብረት በውጪ ለጋሾቹ ላይ ያለውን ጥገኝነት እንዲቀንስ በማሰብ 300 ላሞችን መለገሳቸውን ህብረቱ ዛሬ አስታውቋል፡፡
በሙጋቤ ቢሮ በተዘጋጀ ስነስርዓት ከብቶቹ ትናንት ሐሙስ ለህብረቱ ምክትል ሊቀመንበር ኢራስቱስ ምዌንቻ መበርከቱን የጠቀሰው ህብረቱ በሐራሬ ደቡባዊምዕራብ በምትገኝ ቦታ ላሞቹ ይቀመጣሉ ብሏል፡፡
የህብረቱን የውጪ ጉዳይ ፓርላሜንታሪ ኮሚቴ የሚመሩት ኪንድነስ ፓራድዛ ለኤኤፍፒ በሰጡት አስተያየት ‹‹ባለፈው ዓመት የህብረቱ ሊቀመንበር ሆነው ሲመረጡ ፕሬዘዳንቱ ከብቶቹን ለመስጠት ቃል ገብተው ነበር፡፡በሐራሬ ካሮይ በሚገኝ የግብርና ስፍራ ከብቶቹን በማኖር ህብረቱ በከብቶቹ ምን ማድረግ እንደሚፈልግ የሚያሳልፈውን ውሳኔ እንጠብቃለን ››ብለዋል ፡፡
በፓራድዛ እምነት የሙጋቤ አስተዋእጾ የህብረቱን የፋይናንስ ነጻነት የሚያንጸባርቅ ይሆናል፡፡በፈረቃ በሚታደለው የአፍሪካ ህብረት ፕሬዘዳንትነት እስካሳለፍነው ወር ድረስ በመሪነት ተቀምጠው የነበሩት ሙጋቤ ‹‹ህብረቱ እንዲቀጥል የተወሰነ አስተዋእጾ ለማበርከት በመፈለጋቸው ስጦታውን ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡
የ92 ዓመቱ ሙጋቤ ‹‹ምንም እንኳን በከብቶች የምንታወቅ ቢሆንም ከዚህ ቀደም ህብረቱን ከብቶችን በስጦታ መልክ በማበርከት ለመደገፍ የሞከረ አለመኖሩን ሳውቅ በጣም ተገርሚያለሁ፡፡ለምን ለህብረቱ በከብቶች መልክ ስጦታን አናደርግም?››በማለት አግራሞታቸውን ገልጸዋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት በትዊተር ገጹ ሙጋቤን በማወደስ ‹‹አፍሪካዊያን የአፍሪካን ልማት እንዲደግፉ አርአያነት ያለው መሪነት አሳይተዋል››ብሏል፡፡
ሙጋቤ ለህብረቱ ከብቶቹን በለገሱበት ወቅት የወጡ ሪፖርቶች እንደጠቆሙት ከሆነም በኤልኒኖ ምክንያት በአገሪቱ ድርቅ እየተከሰተ በመሆኑ 3 ሚልዩን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ርዳታ ይፈልጋሉ ተብሏል፡፡

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s