ለመከላከያ ምስክርነት የተጠሩት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ‹ሊቀርቡ ባለመቻላቸው› ምስክርነታቸው ውድቅ ተደረገ

*አብርሃ ደስታ 4 ወራት፣ የሺዋስና ዳንኤል 2 ወራት እስር ይቀራቸዋል

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ አንደኛ ተከሳሽ አቶ ዘላለም ወርቃገኘሁ በቀረበበት የሽብር ክስ ላይ ከግንቦት ሰባት ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጋር ተጻጽፈሃል የሚል ማስረጃ በአቃቤ ህግ እንደቀረበበት በመግለጽ ይህን እንዲከላከሉለት አቶ አንዳርጋቸውን ለምስክርነት ቢጠራቸውም በተደጋጋሚ ቀጠሮ ሊቀርቡ ባለመቻላቸው ከፍተኛው ፍርድ ቤት ምስክሩ በተከሳሽ በኩል እንደተተው ይቆጠራል በሚል በይኗል፡፡
ፍርድ ቤቱ ዛሬ የካቲት 25/2008 ዓ.ም ብይኑን ሲያሰማ እንደገለጸው ተከሳሽ አቶ ዘላለም ወርቃገኘሁ ምስክሩን በተመለከተ በተደጋጋሚ እንዲቀርቡለት ጠይቆ እንዳልቀረቡለት በመግለጽ ‹‹ምስክሩ የማይቀርቡልኝ ከሆነ ከምስክሩ ጋር በተያያዘ የቀረበብኝ ክስ ፍሬ ነገር ከክሱ ወጥቶ ብይን ይሰጠኝ›› የሚል አቤቱታ አቅርቧል፡፡
አቃቤ ህግ በበኩሉ ተከሳሹ ምስክሩን አቅርቦ የማሰማት ግዴታ እንዳለበት በመጥቀስ ተከሳሹ የጠየቀው የፍሬ ነገር ይውጣልኝ አቤቱታ የህግ አግባብን የተከተለ ስላልሆነ ምስክሩን እንደተዋቸው ተቆጥሮ ብይን እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡
ችሎቱ በበኩሉ ለምስክሩ የተጻፈው የመጥሪያ ትዕዛዝ ደርሷቸው እንደቀሩ ማረጋገጫ ስለሌለ በተከሳሽ የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት እንደሌለው በማስረዳት ምስክሩ እንደተተው ቆጥሮ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ በመዝገቡ ላይ በተካተቱት አምስት ተከሳሾች ላይ የፍርድ ብይን ለመስጠት ለመጋቢት 29/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ከዚህ ቀጠሮ በፊት የክርክር ማቆሚያ ካላቸው ግራቀኙም በጽ/ቤት በኩል በጽሁፍ ማቅረብ እንደሚችሉ ፍርድ ቤቱ ገልጹዋል፡፡
በሌላ በኩል ነሀሴ 14/2007 ዓ.ም በዚሁ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ከተከሰሱበት የሽብር ወንጀል ነጻ ናቸው በሚል የተበየነላቸው እነ አብርሃ ደስታ በዚሁ ችሎት፣ ‹‹ችሎት ደፍራችኋል›› በሚል የተላለፈባቸው ቅጣት ከመቼ ጀምሮ እንደሚታሰብ ግልጽ አድርጓል፡፡
በዚህም አመት ከአራት ወር የተፈረደበት አቶ አብርሃ ደስታ እና እያንዳንዳቸው አንድ አመት ከሁለት ወር የተፈረደባቸው አቶ የሺዋስ አሰፋ እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ ከመጋቢት 1/2007 ዓ.ም ጀምሮ በሚታሰብ እስር መቀጣታቸውን ገልጹዋል፡፡ በመሆኑም አብርሃ አራት ወራት፣ እና እነ የሺዋስ ሁለት ወራት እስር ይቀራቸዋል ማለት ነው፡፡
እነ አብርሃ ደስታ አቃቤ ህግ በጠየቀባቸው ይግባኝ ላይ ብይን ለማግኘት ለመጋቢት 30/2008 ዓ.ም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀጠሮ እንዳላቸው ይታወሳል፡፡

Ethio Hagere's photo.

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s