ከሞላ አስገዶም ጋር ከአስመራ የተመለሱ የተባሉ ወታደሮች በዩናይትድ ኔሽን እንደኤርትራ ስደተኛ እየተመዘገቡ መሆኑ ተሰማ

 

Mola asgedom

ከሞላ አስገዶም ጋር የትህዴን ወታደሮች ናቸው በሚል ለኢትዮጵያ መንግስት እጃቸውን እንደሰጡ ተደርገው ሲነገርላቸው የነበሩት ‘ወታደሮች’ በኢትዮጵያ በሚገኘው ዩናይትድ ኔሽን ልክ እንደኤርትራ ስደተኛ ራሳቸውን በማስመዝገብ ላይ መሆናቸው ተሰማ::

በተለይ እነዚህ ከሞላ አስገዶም ጋር ተመለሱ የተባሉት የትህዴን ወታደሮች በአዳማ ማረፊያ ተሰጥቷቸው በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የሕወሓት ሚድያዎች ሲዘግቡ የቆዩ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን አብዛኞቹ ወደ ትግራይ ክልል በማቅናት በሽሬ የተለያዩ የስደተኞች ካምፖች ውስጥ ልክ እንደኤርትራ ስደተኛ ተመዝግበው እንደሚገኙ  ምንጮች አጋልጠዋል::

በማይ ዓይኒ ወረዳ በሚገኘው የስደተኞች ካምፕ እንዲሁም ሽሬ አካባቢ በሚገኘው አዲ ሃሪሽ የስደተኞች ካምፕ ከሞላ አስገዶም ጋር ተመለሱ የተባሉት ወታደሮች ራሳቸውን እንደኤርትራ ስደተኛ አስመዝግበው እንደሚገኙ ምንጮቻችን ተናግረዋል::

በማይ ዓይኒ እና በአዲ ሃሪሽ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች በኛ ስም ሌሎች ወደ3ኛ ሃገራት እየተሻገሩ ነው በሚል በተደጋጋሚ ጸብ ያነሱ እንደነበር በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል::

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s