በታንዛኒያ ሰው አዘዋውረዋል የተባሉ ኢትዮጵያዊያን ተያዙ

pic+human

በደቡብ አፍሪካ ታንዛኒያ ሞሮጎሮ ክልል ፖሊስ ባደረገው አሰሳ ዜግነታቸው ኢትዮጵያዊ፣ሶማሊያዊ፣ደቡብ አፍሪካዊና ታንዛኒያዊ የሆኑ ሰው በማዘዋወር ህገ ወጥ ስራ ተሰማርተው የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡
በሞሮጎሮ የአካባቢው ፖሊስ ኮሚሽነር ጆሴፍ ሙምቡ ‹‹በያዝነው ዓመት 23 ኢትዮጵያዊያንን ከያዝን ጀምሮ ሰው አዘዋዋሪዎቹን ለማግኘት ምርመራ ስናደርግ ቆይተን በመጨረሻ ተሳክቶልናል››ብለዋል፡፡
ሁለት ታንዛናዊያን ከአዘዋዋሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የጠቀሱት ኮሚሽነሩ ‹‹ወደታንዛኒያ በህገ ወጥ መንገድ የሚገቡ ሰዎች እስካልቆሙ እረፍት የሚባል ነገር አይኖረንም ማለታቸውን የታንዛኒያው ሲቲዝን ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
ኮሚሽነሩ ለአካባቢው ነዋሪዎች ባስተላለፉት መልእክትም ‹‹ለፖሊስ መረጃዎችን በመስጠት በሰዎች ዝውውር ላይ የተሰማሩ ሰዎችን ለፍርድ እናቅርብ››ብለዋል፡፡
ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሻገር በየጊዜው ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያዊያን በህገ ወጥ መንገድ ወደታንዛኒያ ሲጎርፉ ቆይተዋል፡፡ወደታንዛኒያ ለመግባት የሚጠቀሙባቸው መኪኖች የምግብ ማመለሻዎች በመሆናቸውም አየር ለመተንፈስ በሚያስቸግር ሁኔታ ተጨናንቀው ህይወታቸውን ለአደጋ ሲያጋልጡም ተስተውለዋል፡፡ደቡብ አፍሪካ ታንዛኒያ ለጀመረችው ዘመቻም የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጓ ተሰምቷል፡፡

ምንጭ ሲቲዝን ታንዛኒያ

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s