ትምክህትና ጠባብነት በኢትዮጱያ ህዝብ ቦታ የላቸውም !! – ከኣሥገደ ገብረሥላሤ መቀሌ

Asgede

ሠሙኑን ሥለ ትምህክህትና ጠባብነት  በትግራይ በኣማራ ክልል  መሪዎች  በኣጠቃላይ በህወሓት ኢህኣደግ ከፍተኛ ኣማራሮች ለሥልጣናቸው እድሜ ማራዘምያ ታሣቢ በማድረግ የራሣቸው ውሥጣዊ ብልሽው ባህሪ  ገበያ ላይ  ወጥቶ  መላው ህዝብ ሥላወቃቸው   ህዝቡን ለመደናገር ኣቅጣጫን ለመቀዮር  በትግራይ እና  ኣማራ  ህዝቦች  ቅራኔን እየፈጠሩ ይገኛሉ: ለዚሁ እኩይ ሤራቸው ኣለማ ለማሣካት ሁለቱ መሪዎች ከህዝብ በሥተጀርባ ሆነው በመግፋት ህዝቡን  ወደትርምሥ እየነዱት ይገኛሉ ::
አነዚህ መሪዎች ተልቁ ሥህተታቸው  እነሱ የሚያምኑበት ህገመንግሥትም እንኳን   በመናድ  እየሸፈጡን ይገኛሉ
ለዚሁ ኣፍራሽ ተግባራቸው ለማሥረጃነት  የ ሁለቱ ፓርቲዎች ኣመራር  ህገመንግሥ  በመናድ የዛ በምልመላ ያዳራጁት ፈደረሽን ምክር ቤት ሥልጣን በመጋፍት   የሁለቱ ሀዝቦች ግርጭት  እያባባሡት  ይገኛሉ::  ለዚሁም
1ኛ    የኣባይ ወልዱ ቡዱን ከክልል እሥከ ጎጥ እና የኣንድ ለኣምሥት ኣሥኳል ከዛ በዘለለ እሥከግለሠዎች በመሥበክ ህዝቡ ወደ ኣደገኛ ሁኔታ እየመሩት  ናቸው ::
2ኛ የደመቀ መኮነን እና ገድሉ ኣንዳርጋቸው ቡድኖች ኣማራሮች ደግሞ   የኣማራ ህዝብ  የበኣዴን ማእከላይ ኮምቴ ሥብሠባ ያደርጋል  ሢሠማ   ቡዙ የክልሉ  ህዝብ የተዋሣሠቡ ችግሮች  ሊፈቱ የሚችሉ ወሣኔዎች ይዘው ይወጣሉ ብሎ ሢጠበቅ ቆይቶ  ነበር  ውጤቱ ግን ውሃ ቢወግጡት እቡጭ ሆኖ ቀረ :: ይህም  ውሣኔው ከኣባይ ወልዱ በመፋጠጥ ሢፈጽሙት  ሢቆሠቁሥት የሠነበቱት እሣት መጠናከርያ በደርዘን የሚቆጠሩ ማእከላይ ኮምቴ  የፈደረሽን ምክር ቤት ሥልጣን በመናድ የወልቃይት ጸገዴ  ጉዳይ ከህወሃት ጋር ያለው የወረደ ንትርክ ለመፍታት በፖሊት ቢሮ የሚመራ 15   ሠዎች በመምረጥ  ሽሞ ወጣ::
ይ ጊዚያዊ ኣሥተዳደር ደርግ ግን ምን እንደሚሠራ ጦርነት ሊከፍት ነወን ?    ወይ በሠላማዊ መንገድ  መፍትሄ ሊያፈላል ነውን?
በእኔ እምነት ሁለቱ የሚከተሉት ያሉ መንገድ በታኝ እና  የሃገራችን ኣንድነት የሚበታትን ነው::
እኔ  ሁሉ ጊዜ  የምናገረው ልድገመው በወ ልቃይት ጸገደ ያው በሌሎች ክልሎች ዘኖች ያለወ የመሥተዳደር ጥያቄ  በሚመለከት ህዝቡ ነጻነት ተሠጥቶት በገለልተኛ ታዛቢ የሚመሥለው ይምረጥ:: እኔ በልቃይት ጸገድዬ ጸለምት ወደ   ጎንደር ይተዳደር ወይ ወደ ትግራይ  ይተዳደር የሚል ርካሽ ኣጀንዳ    ንትርክ  ኣይደለም የሚታዬኝ ::  የሃገራችን ወነኛው ችግር በሃገራችን ሁሉም ኣይነት ዲሞክራሢ እና ሠብኣዊ መብቶች  ኣለመከበሩ ነው
ኣሁንም  በሃገር ደረጃ መብታችን ከተከበረ የግለሠው መብት ቅድሚያ ከተከበረ ሁሉም ነገር ይፈታል ::
ባለፈው ጊዜ ሥለ የጎንደርና የትግራይ  የጎንደር  የኣሥተዳደር   የኣከላለል መሥመር በዘመነ ጃንሆይና በደርግ የነበረ ኣሥተዳደር ሃቁን ተናግሬ ነበር::
ኣንድኣንድ  ጠባቦች  ኣድር ባይ ካድሬዎች ኣሥገደ ለትግራይ ህዝብ ማንነት የከዳ የወልቃይት ጸገደ ለትምክህ ተኛች በመወገን  የኣማራና የትግራይ የሚለይ መሥመር  ተከዜ  ነበር ብለዋል በማለት ለትግራይ ህዝብ  ከድቶታል  ጭራሹም ታጋይ ነበር ወይ በማለት ኣንድ ጫፍ ኣንጠልጥለው በማዝ  በድህረገጽ ሢዘላበዱ  እመለከታለሁ
ኣሁንም ልድገመላችሁ የህዝቦች የተሟላ ነጻነት የማያከብር ህዝቦችን   በታሪካዊ ኣመጣጣቸው  በባህላቸው በቋንቋቸው    በኣሥተሣሠባቸው   በፍላጎቻቸው በነጻ ምርጫቸው ሪፍረንደም   በፈለጉት ክልል ወይ ዞን  እንዲሥተዳደሩ የማይፈቅድ ሥርኣት ከሆነ   ሥርኣቱ ጸረዲሞክራሢ ነው ማለት ነው::
በኔ ፍላጎት እነዛ ድሮ በኣማራ ይተዳደሩ  የነበሩ ወልቀይት ጸገዴ ጸለምት  ቆቦ ወደ ፈለጉት ክልል ቢተዳደሩ  ትርጉም ኣሠጠኝም::   በመሥፍናዊ የግዛት ማሥፋፋት ኣንጻር  ሢታይ  መሥፍናዊ ኣሥተሣሠብ  እና ጠባብነት ትምክህት   የተጠናወታቸው የካድሬ ሥብሥብ   ግን ህወሓት በ1968  ዓ  ም   ኣውጥትቶት የነበረ ማኒፌሥቶና ካርታ መሠረት ኣድርገው በግብታውነት እየ ተነዱ  ሢያንጨበጭቡ ይታያሉ ::ምክንያቱም ካላንጨበጨቡ ጥቅም ኣያገኙም እና:: እነዚህ ሠዎች ሆዳቸው የሚሞላ ካገኙ ጭቁን ሀዝብ እርስበእርሡ ቢባላ ደንታ የላቸውም::
እጅጉን እሚያሣዝነው ደግሞ ህወሓት ኢህኣደግ ኣሥወግደን ሓቀኛ ፈደራሊዝም እናመጣለን እያሉ ሢዘምሩ የቆዩ  የተቃዋሚ ፓርት መሪዎች ነን የሚሉ ግለሠዎች  ጠባብ ኣመለካከት በመያዝ በድህረ ገጽ  ሢለቀልቁ ይታዩ ኣሉ::
በመጨረሻ በባኣዴን ማእከላይ ኮምቴ ስብሰባ የወልቃይት ጠገዴ መሣሣብ የመፍትሄ ኣቅጣጫ ከትግራይ እና  ከኣማራ እያንዳንዳቸው 15 ሠው ወክለው እዲያጠኑ ብሎ መወሠኑም ፍትሃዊ ኣይደለም  ይጠና ከተበለ ከሁለቱ ፓርቲዎች ኣባላት ውጭ ያለኣንዳችም ተጽእኖ ገለልተኛ ወገኖች ከፓለቲካዊ ወገንተኝነት ነጻ መሆን ኣለባቸው እላለሁ :  :

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s