የኢትዮጵያ ቦይንግ አውሮፕላን ያልተለመደ የተባለ አደጋ አጋጠመው

ET Airline 2

ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ ቢ787 ድሪም ላይነር አውሮፕላን ከአዲስ አበባ ለመነሳት በሚያኮበኩብበት ወቅት ችግር አጋጥሞት አንድ መንገደኛው ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል፡፡የአውሮፕላኑ ችግር በቴክኒክ ሰራተኞች ስህተት የተፈጠረ ነው በመባሉም የአየር መንገዱ ሰራተኞች ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡

በአውሮፕላኑ አምራች ኩባንያ 38754/283 የሚል ሴሪያል ቁጥር የተሰጠው አውሮፕላኑ በአየር መንገዱ ኒያላ የሚል ስም ወጥቶለታል፡፡አውሮፕላኑ ለኢትዮጵያ ተላልፎ በሚያዚያ ወር 2007 ከመሰጠቱ በፊት የሙከራ በረራ አድርጎ እንደነበር የሚጠቅሱት ምንጮች አሁን አጋጠመው የተባለው ችግር ለአምራቾቹ እንግዳ እንደሆነባቸው ጠቅሰዋል፡፡

ለ11 ወራት ያህል በአገልግሎት ላይ የቆየው አውሮፕላኑ በቦይንግ በተሰጠው ማንዋል መሰረት በመደበኛነት ጥገና ሲደረግለት ቆይቷል ተብሏል፡፡አውሮፕላኑ አርብ ዕለት ተሳፋሪዎቹን በመጫን ወደ ሮም ለመብረር ፊቱን ወደመውጫው ባዞረበት ቅጽበት የፊት ለፊት እግሩ በመሰበሩ አንድ ተሳፋሪው ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል፡፡

በቦይንግ ድሪም ላይነር ታሪክ እንዲህ አይነት አደጋ ሲያጋጥም የመጀመሪያው መሆኑን የሚጠቅሱ ባለሞያዎች የአውሮፕላኑ አፍንጫ በስርዓት ባለመከደኑ ምክንያት እንዲህ አይነት አደጋ ሊከሰት ይችላል ማለታቸውን አቪዬሽን ኒውስ ዘግቧል፡፡ መንገደኞቹ በድንጋጤ የተለያዩ የአደጋ ጊዜ መውጫ በሮችን በመጠቀም ያለችግር መውጣታቸውን የጠቀሰው ዜናው ስህተቱ የተፈጠረው በቴክኒሻኖች ቸልተኝነት ሊሆን ይችላል በመባሉም ጠንከር ያለ ምርመራ መጀመሩም ተሰምቷል፡፡
ከሁለት ዓመት በፊት በለንደን የኢትዮጵያ ቦይንግ አውሮፕላን በቆመበት በእሳት መያያዙም አይዘነጋም፡፡

ምንጭ አቪዬሽን ኒውስ

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s