አንዲት ወጣት የኢትዮጲያ መንግስትን ፍርድ ቤት ገተረችው!!

እንደምን አደራችሁ ጓዶች,,,, እኔ ሰላም ነኝ! ! ቢቢሲ በዛሬ ወጉ አንድ አስገራሚ ዜና አትቷል,,,, እኛም ያገራችን ጉዳይ በመሆኑ ወዲህ አምጥተነዋል! !

ያስሚን ሐሰን ትባላለች ኢትዮጲያዊት ናት,,, አያቷ ጋር ከምትኖርበት ሰፈር በ13 ዓመቷ ትጠለፍና ትደፈራለች,,, ያስሚን ከጠላፊወቿ ቤት አምልጣ ለፖሊስ ጉዳዩን አቤት አለች,,,, ደፋሪዎቿ ተያዙ,,,, ይሁንና ወዲያው በዋስ ተለቀቁ,,,, የሚገርመው ይሄ ነው,,,, ደፋሪዎቹ በዋስ እንደወጡ እንደገና ያስሚንን ጠልፈው እንደገና ደፈሯት,,, መድፈር ብቻ አይደለም ፈቅዳና ወዳ እንደገባች በማስመሰል በግድ የጋብቻ ሰነድ ላይ አስፈረሟት ,,,

ያስሚን አሁንም ካጋቾቿ ለሁለተኛ ጊዜ አምልጣ መንግስት ያድነኝ ስትል ከሰሰች,,,, ፍርድ ቤት ደረሰ ጉዳዪ,,,, ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን አይቶ ዋናው ደፋሪ ላይ 10 አመት ግብርአበሮቹን ደግሞ እያንዳንዳቸው ላይ የስምት አመት እስር ፈረደ! ያስሚንም ለጊዜው እፎይ አለች! !
ግን ምን ዋጋ አለው? ያስሚን ከመደፈሯ በፊት ድንግል እንደነበረች ማረጋገጫ አላቀረበችም በሚል የተወሳሰበ ሰበብ ደፋሪዎቹ ይግባኝ ጠይቀው በነፃ ተፈቱ,,,, ይግባኝ መጠየቁንም ሆነ መፈታታቸውን ያስሚን አልሰማችም ነበር,,,, በኋላ ይህን ነገር ስታውቅ ለይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመለከተች,,,, ከፍተኛው ፍርድ ቤት የታችኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ አፅድቆ ደፋሪዎቿን በነፃነት ኑሩ አላቸው,,,

ያስሚን ኢትዮጲያ ችሎት ላይ ያላት ተስፋ ተሟጠጠ ይሁንና እንደብዙኑ ፍትህ የተጓደለበት ኢትዮጲያዊ ከእንግዲህ ፈጣሪ በደሌን ይመልከት ብላ እንባዋን ረጭታ ቁጭ አላለችም,,,, እንደውም ዶሴዋን ይዛ በ2007 ዓ/ም ክሷን አቀረበች ለማን? ለአፍሪካ የሰብዊ መብቶች ኮሚሽን / African Commission on Human and people’s rights./ ይህ ኮሚሽን የኢትዮጲያ መንግስት በሰበአዊ መብት ጥበቃ የፈረመበት ቻርተር አለው!
እናም ያስሚን ለኮሚሽኑ አቤት ብላ የኢትዮጲያ መንግስትን ችሎት ገተረችው,,,, ያኔ ስትደፈር 13 ዓመቷ ነበር አሁን 28 ዓመቷ ነው ያስሚን (ትግላችን ረዥምና መራራ ነው እንዲል ተከሳሽ) ኮሚሽኑ ጉዳዮን ሲመረምር ሰንብቶ በ2007 የከሰሰች በ2016 ተፈረደላት! !

ውሳኔ,,,, ወሪ/ት ያስሚን በኢትዮጲያ መንግስት እና በፍትህ ስርአቱ በደረሰባት በደል ምክንያት ተከሳሽ የኢትዮጲያ መንግስት ለከሳሽ ያድሚን ያሲን 150 000 ዶላር የበደል ካሳ እንዲከፍላት,,,, ከመወሰኑም በላይ,,,, ኮምሽኑ ለኢትዮጲያ መንግስት በ180 ቀናት ውስጥ ብሩን ከፍለህ እንድታሳውቀኝ ሲል ቁርጥ ያለ ቀን አስቀምጧል!! ኮምሽኑ በእንዲህ አይነት የመደፈር ጉዳይ ላይ ብይን ሲሰጥ የመጀመሪያው ነው፡፡
ዜናውን ስሰማ ምን አሳሰበኝ መሰላችሁ,,,, ይሄ ኮሚሽን በኢትዮጲያችን የሚፈፀመውን ቁጥር ስፍር የሌለው ኢ ሰብአዊ ድርጊት ቢቀርብለት,,,,, መንግስታችን ላይ የሞት ፍርድ ፈርዶ ካለመንግስት እንዳያስቀረን ሰጋሁ:))

መልካም ቀን! !(አሌክስ አብርሃም)

 

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s