ልማት ባንክ በእርሻ ስራ የተሰማሩን አላበድርም አለ

lemate

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በእርሻ ስራ ለተሰማሩ ድርጅቶች ይሰጥ ነበረውን ብድር ላልተወሰነ ጊዜ ማቆሙን ይፋ አድርጓል፡፡በባንኩ ፕሬዘዳንት ኢሳያስ በርሄ ተፈርሞ ለባንኩ ሰራተኞች የተሰራጨው ደብዳቤ ከዚህ ቀደም ከባንኩ ብድር ተፈቅዶላቸው የወሰዱ በድጋሚ የማስፋፊያ ብድር ቢጠይቁም ሆነ ወደዘርፉ የሚገቡ አዳዲስ ድርጅቶች ብድር ቢጠይቁ እንዳይሰጣቸው ማገዱ ተወስቷል፡፡

ባንኩ በተለይ በጋምቤላ አካባቢ ሰፋፊ የእርሻ መሬት ወስደው ብድር ለጠየቁት ካምፓኒዎች ብድር ቢሰጥም ካምፓኒዎቹ የወሰዱትን ብድር ሳይመልሱ ከአገር በመውጣታቸውና በተለያዩ መንገዶች ብድራቸውን መክፈል ባለመቻላቸው ብድር መስጠቱን ለማቆም እንዲወስን ሳያደርገው አልቀረም፡፡ተበዳሪዎች በአንዳንድ ቦታዎች በተመሳሳይ የእርሻ ፕሮጀክት ተደጋጋሚ ብድሮችን መውሰዳቸውም ይነገራል፡፡

ለእርሻ ስራ በኢትዮጵያ የተፈቀደ ብድር በኢትዮጵያ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚወስድ የሚጠቅሱ መረጃዎች ከ75.5 ብድር ውስጥ 17.3 ቢልዩንን ብሩን እንደሚይዝ ይጠቅሳሉ፡፡

ከልማት ባንኩ ብድር ለማግኘት ተበዳሪዎች ለሚያቀርቡት ፕሮጀክት 25% በራሳቸው እንደሚሸፍኑ ማረጋገጫ ማቅረብ ሲጠበቅባቸው ባንኩ ቀሪውን በብድር መልክ ይሸፍናል፡፡የውጪ ባለሐብቶችም የባንኩን 70% ብድር ለማግኘት ሰላሳ ከመቶውን መሸፈን እንደሚችሉ ይጠየቃሉ፡፡ባንኩ በቅርብ ጊዜ አደረግኩት ባለው ማሻሻያ ግን የውጪ ባለሐብቶች ከባንኩ የሚያገኙት ብድር 50% የፕሮጀክቱን ወጪ የሚሸፍን እንዲሆን አድርጎ ነበር፡፡

በቅርቡ 100 የሚደርሱ ኢንቨስተሮች በልዩ ሁኔታ ተይዞ በነበረ የኢኮኖሚ ዞን ላይ መሬት ተሰጥቷቸው በመገኘቱ ፈቃዳቸውን እንዲመልሱ መደረጋቸው አይዘነጋም፡፡ከዚህ ውስጥ ሰላሳዎቹ በ48.443ሄክታር መሬት በጋምቤላ ዲማ ወረዳ  ጀምረውት የነበረን ስራ አቋርጠው የወሰዱትን መሬት እንዲመልሱ በወረዳው መጠየቃቸውም ይታወሳል፡፡እንዲህ አይነት ተደጋጋሚ ውሳኔዎችም ባንኩን ለዘርፉ ያደርግ የነበረውን የብድር ድጋፍ እንዲያቆም ሳያደርገው አልቀረም፡፡

 

መንግስት ሰሞኑን ባወጣው መመሪያ መሰረትም በአገሪቱ የሚገኙ መሬቶችን ለኢንቨስተሮች መስጠቱን ማቆሙን መግለጹ አይዘነጋም፡፡

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s