የ 100% ምርጫ አቀናባሪ በሰብዓዊ መብት ዙሪያ ሪፖርት ያቀርባሉ – የሚሊዮኖች ድምጽ

1930786_981723211912613_3887250359965847240_n

ዶር አዲሱ ገብረ እግዚአብሄርን መቼም የማያውቅ አለ ብለን አናምንም። በተለይም የኢትዮጵያን ፖለቲካ የሚከታተል። የሕወሃት አባል ናቸው። በምርጫ ዘጠና ሰባት ወቅት ኢሕአዴግን ወክለው ተወዳድረው ነበር። ከዚያም የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ጸሃፊ ሆነው አገልግለዋል። የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢው ፕሮፌሰር (የእንሳሳ ሐኪሙ) መርጋ የነበሩ ቢሆንም፣ ፕሮፌሰሩ ለይስሙላ የተቀመጡና የሚሰጣቸውን መመሪያ የሚያነቡ እንጂ ፣ በቦርዱ ፈላጭ ቆራጭ የነበሩት ዶር አዲሱ ነበሩ።

በአገሪቷ በሁሉም ክልሎች ጠንካራ መዋቅር የነበረው የአንድነት ፓርቲ እንደነበረ የሚታወስ ነው። አንድነት የምርጫ ዘመቻ ከመጀመሩ በፊት በ34 ዞኖች ጽ/ቤቶች ከፍቶ 547 መቀመጫ ላለው ፓርላማ ከአምስት መቶ በላይ ተወዳዳሪዎችን አዘጋጅቶ የጨረስ ደርጅት ነበር።

በሕወሃት፣ አንድነት ፓርቲ ከጨዋታ ዉጭ እንዲሆን የፖለቲክ ዉሳኔ በመወሰኑ፣ ከሕወሃት በተሰጠ የፖለቲካ መመሪያ፣ በገንዘብ የተገዙና አስቀድሞ የሰረጉ ጥቂት ግለሰቦችን በማሰባሰብ ፣ ተለጣፊ የአንድነት አንጃ በመፍጠር፣ ሕገ ወጥ በሆነ መልኩ የአንድነት ፓርቲ ታግዷል። ይሄንን በቀዳሚነት ሲመሩና ሲያንቀሳቅሱ የነበሩት ዶር አዲሱ ነበሩ።

በዶር አዲሱ አመራር፣ የ2007 ምርጫ መቶ በመቶ የሚለውን አስቂኝ ድል፣ ምርጫ ቦርድ ለሕወሃት/ኢሕአዴግ አጎናጽፏል። ዶር አዲሱ ለተሰጣቸው የሕወሃት ተልእኮ ከሚጠበቀው በላይ ዉጤት ስላመጡም የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሃላፊ ሆነው ተሾመዋል።

በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም የተቋቋመው ዝነኛው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በኢትዮጵያ ላለፉት 4 ወራት በተነሱ ተቃዉሞውች ዙሪያ የተፈጸሙ ኢሰዓዊ የሰባአዊ መብት ረገጣዎች፣ ግድያዎችን፣ ድብደባዎችን፣ በመረጃዎች በማስደገፍ ይፋ አድርጓል።

በሕግ፣ ሃላፊነቱ የሰብአዊ መብት ጥሰት መከታተል የሆነውና ዝምታን መርጦ የነበረው በዶር አዲሱ የሚመራው የስብአዊ መብት ኮሚሽን፣ የኢሰመጉን ረፖርት ተከትሎ ፣ መመሪያ ተላልፎለት ይሁን በሌላ ምክንያት ብቅ እንዳለ እያየን ነው። ዶር አዲሱ የሚመሩት ኮሚሽን ለፓርላማ በቅርቡ ሪፖርት እንደሚያቀርብ፣ ዶር አዲሱ ራሳቸው ለሜዲያው ገልጸዋል። የዚህ ረፖርት ይዘት ምን እንደሚመስል ገና ባይታወቅም ከወዲሁ ሰዎች ያላቸውን ግመት እየሰጡ ነው።

“ዶር አዲሱ ሰዎች መገደላቸውን እና ጥፋት መድረሱን አምነው፣ የደረሰዉን ጉዳት ግን አሳንሰው ነው ያቀርባሉ። እነ ጌታቸው ረዳ ከተናገሩት የተለየ ነገር አይናገሩም” ያሉን አንድ ተንታኝ ለደረሱትም ጥፋት፣ ዶር አዲሱ ተጠያቂ ኦህድድን ሊያደረጉ እንደሚችሉ ይናገራሉ፣ በአሉታዊነት።

ሌላ ተንታኝ የተለየ አዎንታዊ አስተያየት ነው አላቸው። “እነ ኃይለማሪያም ያለዉን ችግር አውቀዋል። በዚህ መቀጠል እንደማይችሉ ገብቷቸዋል። መሰረታዊ ለዉጥ ለማምጣት ሳይፈለጉ አይቀርም። ኢሰመጉን፣ ሆነ ተቃዋሚዎች የሚሉትን መስማት፣ እዉነትም ቢሆን፣ ሽንፈት ስለሚመስላቸው እነ ኢሰመጉ ያቀረቡትን በተለየ መልክ ጠርዘው፣ በነዶር አዲሱ በኩል ፓርላማ ዉስጥ በማስቀረብ፣ የሕግ ስልጣን ያለውም ፓርላማ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ መሰረታውዊ ዉሳኔዎችን እንዲወስን ለማድረግ ሳያስቡ አይቀርም” ሲሉ አስተያየት ይሠጣሉ።

ዶር አዲሱ ገብረ እግዚአብሄር ሕዝብን ሳይሆን ህወሃትን የሚያገለግሉ፣ ሕግን ሳይሆን የሕወሃት መመሪያን የሚከተሉ ሰው እንደሆኑ እናውቃለን። የመቶ በመቶ የምርጫ ዉጤት እና የርሳቸው አሳፋሪ ሥራን መለስ ብለው የማሰብ ብስለት ካላቸው ስማቸዉን ለማደስ ይሄን አጋጥሚ ሊጠቀሙበት ይችላሉ። በሌላ ጎኑ ግን ፣ እንደ ሌሎች፣ ግትርና ሁልጊዜ እኛ ብቻ ነን የምናውቀው እንደደሚሉት፣ የሕወሃት አመራሮች፣ ስህተታቸውን መረዳት የተሳናቸው ደካም ሰው ሆኖ መቀጠሉን ሊመርጡ ይችላሉ። በቅርቡ የምናየው ይሆናል።

Advertisements
This entry was posted in Uncategorized. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s